2023 (እ.አ.አ)
ሰባት የማካፈል ቀናት
ሐምሌ 2023 (እ.አ.አ)


“ሰባት የማካፈል ቀናት፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሐምሌ 2023 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሐምሌ 2023 (እ.አ.አ)

ሰባት የማካፈል ቀናት

ወንጌልን ተቀባይነት ባለው እና በተለመደ መልኩ ልታካፍሉ ትችላላቹ። ለዚህ የተግባር ጥያቄ ዝግጁ ናችሁ?

ምስክርነታችንን ስለማካፈል ስንነጋገር፣ አብዛኛውን ጊዜ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ወይም በሌላ መደበኛ መቼት ምስክርነታችንን ስለማካፈል እናስባለን። ነገር ግን“እምነታችሁን ተቀባይነት ባለው እና በተለመደው መንገድ ለማሳደግ እድሎችን ፈልጉ” በሚል ተበረታተናል።1

ከታች ባለው የሰባት ቀን የስራ ተግባር፣ በየቀኑ በተለየ መንገድ ለአንድ ሳምንት ያህል ምስክርነታችሁን ማካፈል ትችላላችሁ። እነዚህን ነገሮች በማንኛውም ቅደም ተከተል ማድረግ ወይም ደግሞ የራሳችሁን ሃሳብ ማመንጨት ትችላላችሁ! ለዚህ የተግባር ጥያቄ ዝግጁ ናችሁ?

ምስል
የመሰብሰቢያ አዳራሽ

ምስል በኤምሊ ኢ.ዴቪስ

ቀን 1 ቤተ-ክርስቲያን

ምስክርነትን ማካፈል በጾም እና በምስክርነት ስብሰባ ላይ የሚመቻችሁ ከሆነ ምስክርነታችሁን ለማካፈል አስቡ። ካልሆነም፣ በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ በሰንበት ክፍላችሁ ውስጥ ወይም በሴሚኔሪ ላይ በመሳተፍ ምስክርነታችሁን ማካፈል ትችላላችሁ። እዚያ የምታካፍሉት አስተያየቶች እናንተንም ጨምሮ ሌሎችን ሊያነሳሳ እና ምስክርነታቸውን ሊያጠነክር ይችላል።

ምስል
ጓደኞች

ቀን 2 ጓደኞች

እሁድ እለት ቤተ-ክርስቲያን ምን ተማራችሁ? በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ንግግር ወይም ደግሞ በክፍላችሁ ውይይት ጊዜ አንድ ሰው ያካፈለውን ወዳችኋል? ምናልባት መክፈቻ መዝሙሩ ከምትወዱት መዝሙር መሃል አንዱ ነው። ስለዚህ ነገር ለጓደኛችሁ ንገሩ! ከዚያም ስለ ሳምንቱ የመጨረሻ ቀናቸው ጠይቁ።

ምስል
ማህበራዊ ሚዲያን የያዘ ስልክ

ቀን 3 ማህበራዊ ሚዲያ

ማህበራዊ ሚዲያ መንፈሳዊ ነገሮችን በተለመደው እና ተቀባይነት ባለው መልኩ ለማካፈል እጅግ በጣም ጥሩ ቦታ ነው። ለዚህ የተግባር ጥያቄ ቀን ስለሚከተለው አንድ ነገር መለጠፍን አስቡ።

  • ከምትወዷቸው የቅዱሳት መጽሃፍት ጥቅሶች መሃከል አንዱን።

  • አንድ የአጠቃላይ ጉባኤ አበረታታች ጥቅስ።

  • አንድ መንፈሳዊ አስተምሮ ወይም ተሞክሮ

  • ስለአዳኙ የምትወዱትን ወይም የምታደንቁትን አንድ ነገር።

  • በቅርቡ እናንተን የረዳበትን አንድ መንገድ ወይንም ስለእርሱ የምታደንቁት አንድ ባህርይ እንዲሁም ለምን እንደምታደንቁት።

ምስል
ቪዲዮ እና ጽሁፍ የያዘ ስልክ።

ቀን 4 ጽሁፍ ወይም ቪዲዮ

በጽሁፍ ወይም በቪዲዮ አነሳሽ የሆነ መልክት ላኩ። ሊወዱት ይችላሉ ብላችሁ የምታስቡትን የጉባኤ ንግግር፣ ስለ እነሱ የምታደንቁትን ነገር ወይም ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስላላችሁ እምነት ልታካፍሏቸው ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ የሰማይ አባት ለእነሱ ስላለው ፍቅር ማወቅ ያስፈልጋቸው ይሆናል። ሁሌም በአካል ልትነግሯቸውም ትችላላችሁ።

ምስል
ወጣት ሴት የልብ ቅርጽ ያለው ፊኛ ይዛ

ቀን 5 አገልግሎት

ሌሎችን ማገልገል ምስክርነታችሁን የምታካፍሉበት መንገድ እንዴት ሊሆን እንደሚችል እያሰባችሁ ይሆናል ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንዲህ ሲል ነግሮታል፣ “በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑት ምሳሌ ሁን።” (1ኛጢሞቲዎስ 4:12) ስለዚህ ሌሎችን አዳኙ እንደሚያገለግላቸው በማገልገል እምነታችሁን በምሳሌነት ማሳየት ትችላላችሁ።

ምስል
የጥበብ መሳሪያዎች

ቀን 6 ጥበብ

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ጥበብ ሃሳባቸውን እና ስሜታቸውን ሊገልጹ የሚችሉበት የተለየ መንገድ አድርገው ይጠቀሙታል። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ወንጌሉ ያላችሁን ስሜት ለማካፈል ሥዕሎችን፣ ቅርጻ ቅርጾችን፣ ግጥምን፣ ሙዚቃን፣ ወይም ማንኛውንም ዓይነት ጥበብን መጠቀም ትችላላችሁ።

ምስል
ወጣቶች እየተነጋገሩ

ቀን 7 የተለመዱ ንግግሮች

ስለ አንድ ርዕስ ያላችሁን ማንኛውንም ሀሳብ እንደምታካፍሉ ሁሉ እምነታችሁን በተለመዱ መቼቶች ውስጥ ለማንሳት አትፍሩ።

በእርግጥ ስለ ቤተ-ክርስቲያን አክቲቪቲዎች ወይም በቅርቡ ስላነበባችሁት ጥቅስ ማውራት ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ከዚህም የበለጠ የተለመደ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፦

  • በተፈጥሮ መነሳሳት ከተሰማችሁ፣ ለእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራዎች ያላችሁን አድናቆት ለሌላ ሰው ግለጹ።

  • ምናልባት በቅርቡ ምርጥ የሆነ ተሞክሮ አጋጥሟችሁ ይሆናል። በጣም የግል ካልሆነ፣ ስለዚህ ነገር ለጓደኛችሁ ንገሩ።

  • የምትወዱት መጽሐፍ ወይም ፊልም ውስጥ የወንጌል ምሳሌዎችን ፈልጉና ግንዛቤዎቻችሁን አካፍሉ።

ተቀባይነት ያለው እና የተለመደ

እምነቶቻችሁን ለመካፈል የተለያዩ መንገዶችን ስታገኙ፣ ይህን ማድረጋ ለናንተ ይበልጥ የተለመደ ይሆናል። በመጀመሪያ ግራ የሚያጋባ ሊመስል ይችላል፣ ነገር ግን ችግር የለውም! ምስክርነታችሁ በራሱ ለእናንተ የተለመደ መሆኑን አስታውሱ- የማንነታችሁ ክፍል ነው። እሱን ማካፈልም የተለመደ ሊሆን ይችላል። የሚጠይቀው በየቀኑ ይበልጥ ማካፈልን ብቻ ነው።

ዛሬ ምስክርነታችሁን እንዴት ነው የምታካፍሉት?

ማስታወሻ

  1. ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣የሚያዚያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ፣ (ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 17)

አትም