2010 (እ.አ.አ)
የሚስዮን ገና
ዲሴምበር 2010


ወጣቶች

የሚስዮን ገና

የሙሉ ጊዜ ሚስዮን በነበርኩበት በሁለተኛው ገና፣ እኔና የሚስዮን ጓደኛዬ በቅርብ ጊዜ የተጠመቀችውንና ቤተሰቧን ጎበኘን። ከጥሩ የገና እራት በኋላ፣ የገና መልእክት አቀረብንላቸው።

ስለዘመኑ እንዲያስታውሱ የሚያደርጋቸውም እንደ ኮኮቦች፣ ስጦታዎች፣ የክርስቶስ ልደት፣ እና የገና ዛፍ አይነት ነገሮችን እንዲስሉ ቤተሰብን ጠየቅናቸው። ከ2 ኔፊ 19፧6 በተጨማሪ አንዳንድ ቅዱስ መጻህፍትን አነበብንላቸው፧ “ህፃንም ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ፣ መካር፣ ሀያል አምላክ፣ የዘለአለም አባት፣ የሠላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።” “Once in Royal David’s City” (Hymns, no. 205) የሚባለውም መዝሙር ዘመርን፣ ስለክርስቶስ ልደት ቪድዮ አየን፣ እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ መሰከርን።

ይህም ብዙ ነገሮች የሌሉበት፣ ከቤተሰባችን ከለመድነው የገና ግብዣ የተለየንበት ገና ነበር፣ ነገር ግን ስለአዳኝ ስንመሰክር፣ ለእርሱና ለመወለዱ ከዚህ በፊት ከነበረኝ በላይ ጥልቅ ፍቅርና ምስጋና ተሰማኝ። የሰማይ አባቴን በሙሉ ሚስዮን አገልግሎት የማገለግልበት ጊዜ የመጨረሻው ገናዬ እንደነበረ ተረዳሁ፣ ነገር ግን የትም ብሆን መንፈሱ ስለልጁ ሊመሰክርልኝ እንደሚችል ገባኝ።

አትም