2010 (እ.አ.አ)
ክርስቶስን ለማየት እንችላለን?
ዲሴምበር 2010


የቀዳሚ አመራ መልእክት፣ ታህሳስ 2010

ክርስቶስን ለማየት እንችላለን?

አንድ ማታ አንድ አያት አራት አመት ለሆናት የልጅ ልጁ ታሪክ እያነበብላት እያለ ወደላይ ተመለከተችና፣ “አያቴ፣ ኮኮቦቹን ተመልከት!” አለችው። ሽማግሌውም ሰው በደግነት ፈገግ አለና እንዲህ አላት፣ “ውዴ፣ በቤት ውስጥ ነን ያለነው። በዚህ ውስጥ ምንም ኮኮቦች የሉም።” ነገር ግን ልጅቷ ችክ ብላ፣ “በክፍልህ ውስጥ ኮኮቦች አሉ! ተመልከት!” አለች።

አያቷ ወደላይ ተመለከተ እናም ኮርኒሱ በሚያንጸባርቁ ብረቶች የተሸፈነ እንደሆነ በመደነቅ ተመለከተ። በአብዛኛው ጊዜ የማይታይ ነበር፣ ነገር ግን ብርሀን የሚያንጸባርቀውን በአንድ በኩል ሲነካው፣ የኮኮቦች ስፍራ ይመስል ነበር። ለመታየት የትንሽ ልጅ አይኖች ነበር ያስፈለጉት፣ ነገር ግን በእዛ ነበሩ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ፣ አያቷ ወደ ዚያ ክፍል ሲገባ እና ወደላይ ሲመለከት፣ ከዚያ በፊት ሊመለከተው ያልቻለውን ለማየት ይችላል።

አሁን በሙዚቃና በብርሀን ፣ በግብዣና በስጦታ ወደ ተሞሉ ወደሌላ አስደሳች የገና ዘመን ውስጥ ደርሰናል። ነገር ግን ከሁሉ ህዝቦች ሁሉ እኛ የአዳኝን ስም የያዘችው ቤተክርስቲያን አባላት ከዚህ ዘመን የውጪ ገፅታው አሳልፈን ለመመልከት እና የዚህ አመትን ልብ የሚማርክ እውነትን እና ወብትን መመልከት ያስፈልገናል።

በቤተልሔም ውስጥ ከነበሩት ስንቶቹ አዳኝ በእዚያው በቅርባቸውእንደተወለደ አውቀው ነበር። ከረጅም ጊዜ በፊት ቃል ተገብቶበት የነበረው መሲሕ፣ የእግዚአብሔር ልጅ በመካከላቸው ነበር!

መላእክቶቹ ለእረኞቹ ምን እንዳሉአቸው ታስታውሳላችሁ? “ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።” እናም ለእራሳቸው እንዲህ አሉ፣ “እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ” (ሉቃስ 2፧11, 15)።

እንደ ድሮው እረኞችም፣ በልቦቻችን እንዲህ ማለት ያስፈልገናል፣ “የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ።” በልቦቻችን ይህን መፈለግ ያስፈልገናል። የእስራኤል ቅዱስን በግርግም ውስጥ፣ በቤተመቅደስ ውስጥ፣ በተራራዎች፣ እና በመስቀል ላይ እንየው። እንደ እረኞችም፣ ለታላቅ ደስታ የምሥራች እግዚአብሔርን እናመስግን እናም እናሞግስ።

አንዳንዴ ለማየት ከምንችላቸው ነገሮች ሁሉ በጣም አስቸጋሪ የሆነው ከፊት ለፊታችን በሁሉም ጊዜ የሚገኙትን ናቸው። በኮርኒሱ ላይ ያሉትን ኮኮቦች ለማየት እንዳልቻለው አያት፣ እኛም በግልፅ በፊታችን ያለውን ለማየት አንችልም።

እኛ የእግዚአብሔርን ልጅ መምጣት ግርማዊ መልእክትን የሰማነው፣ ስሙን በእራሳችን ላይ የወሰድነውና እንደ ደቀመዛሙርቱ የእርሱን መንገድ ለመራመድ ቃል የገባነው—ልቦቻችንን እና አዕምሮአችንን እርሲን ለማየት ሳንከፍት መቅረት አይገባንም።

የገና ዘመን በብዙ መንገዶች አስደናቂ ነው። ይህም የደግነት የልግስና ስራ እና የወንድማዊ ፍቅር ዘመን ነው። ይህም ስለህይወታችን እና የ እኛ ስለሆኑት ብዙ በረከቶች በጥልቅ የምናሰላስልበት ዘመን ነው። ይህም የይቅርታ የምንሰጥበት እና የምናቀርብበት ዘመን ነው። ሙዚቃንና ብርሀንን፣ ግብዣንና ስጦታዎችን የምንደሰትበት ዘመን ነው። ነገር ግን የዘመኑ መንጸባረቅ የሰላም ልዑልን በግርማው ለማየት እንዳንችል የሚያስቆመን እና የምናይበትን የሚያስጨልም አይሁን።

ሁላችንም የዚህ አመት የገና ዘመንን የመደሰቻ እና የመከበሪያ ጊዜ፣ የሁሉን ቻይ እግዚአብሔር እና የአንድያ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ያዳኑበት ታምራትን የምንረዳበት ጊዜ እናድርገው!

ለየቤት ለቤት አስትማሪዎች ሀሳቦች

  1. “የሚያስተኩር ስራዎች ፍላጎትን ለማንቀሳቀስ እና የሚማሩት በትምህርቱ ርዕስ ላይ ትኩረት ለማግኘት እንዲረዳቸው ለመጠቀም ይቻላል። … ስዕሎች የትምህርቱን ዋና መልእክት የሚያጠናክሩ እና የሚማሩትን እንዲያተኩሩ የሚረዱ አስፈላጊ መሳሪያዎች ናቸው (Teaching, No Greater Call [1999],160, 176)። ይህን መልእክት ለመካፈል ስትጀምሩ፣ እንደ ስዕል ማሳየት ወይም ቅዱስ መጻህፍትን የመካፈል አይነት የሚያስተኩር ስራዎችን ለመጠቀም እና ይህ እንዴት ከመልእክቱ ጋር እንደሚገናኝ ቤተሰብን ለመጠየቅ አስቡበት።

  2. “ከዋና አላማዎቻችሁ በጣም አስፈላጊ ከሆነው አንዱ እያንዳንዱን የወንጌል መሰረትን በየቀኑ ጉዳዮች እንዲጠቀሙ ለመርዳት ነው። … ወንጌሉን ሲኖሩበት የሚመጡት በረከቶችን እንዲያገኙአቸው የሚማሩትን እርዱ” (Teaching, No Greater Call, 159)። ይህን መልእክት ከተካፈላችሁ በኋላ፣ በገና ዘመን በአዳኝ ላይ ትኩረት ሲያደርጉ ያጋጠማቸውን ነገሮች የቤተሰብ አባላት እንዲካፈሉ ለመጋበዝ አስቡባቸው።

አትም