2012 (እ.አ.አ)
ለጊዜአችን ትምህርቶች
ኖቬምበር 2012


ለጊዜአችን ትምህርቶች

የመልከጸዴቅ ክህነትና የሴቶች መረዳጃ ማህበር የአራተኛው እሁዶች ትምህርቶች “ለጊዜአችን ትምህርቶች” የተወከሉ ይሆናሉ። እያንዳንድ ትምህርትም በቅርብ ከነበረው የአጠቃላይ ጉባኤ አንድ ወይም ተጨማሪ ንግግሮች መምረጥ ይቻላል። የካስማ እና የዲስትሪክት ፕሬዘደንቶች የትኛዎቹ ንግግሮች መጠቀም እንደሚገባቸው መምረጥ ይችላሉ፣ ወይም ይህን ሀላፊነት ለኤጲስ ቆጶስ እና ለቅርንጫፍ ፕሬዘደንቶች ለመስጠት ይችላሉ። የመልከጼደቅ የክህነት ስልጣን ወንድሞች እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች አንድ አይነት ንግግሮችን በአንድ እሁድ ቀን ማጥናታቸው አስፈላጊነትን መሪዎች ደጋግመው ማሳሰብ ይገባቸዋል።

በአራተኛው ሰንበት ትምህርት ተሳታፊዎች የቅርቡን የአጠቃላይ ጉባኤ ጋዜጣን እንዲያጠኑ እና ወደ ክፍል እንዲያመጡ ይበረታቱ።

ከእነዚህ ንግግሮች ትምህርትን የማዘጋጃ ሀሳቦች

ንግግሮችን ስታጠኑ እና ስታስተምሩ መንፈስ ቅዱስ ከእናንተ ጋር እንዲሆን ጸልዩ። ሌሎች መፅሀፎችን በመጠቀም ትምህርትን ለማዘጋጀት ሀሳብ ይመጣላችሁ ይሆናል፣ ነገር ግን የጉባኤ ንግግሮች የትምህርት መረጃ እንዲሆን ፈቃድ የተሰጠበት ነው። የተመደባችሁትም በቤተክርስትያኗ የቅርብ አጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ እንደሚገኙት ሌሎችን ወንጌሉን ለመኖር እና ለመማር እንድትረዱአቸው ነው።

የክፍል አባሎች ፍላጎትን የሚያሟሉ መሰረታዊ መርሆችን እና ትምህርቶችን በመፈለግ ንግግሮችን አጥኑ። ደግሞም ታሪኮችን፣ ቅዱስ መጻህፍት የተጠቀሱበትን፣ እና እነዚህን እውነቶች ለማስተማር የሚረዷችሁን ቃላቶች ፈልጉ።

መሰረታዊ መርሆችን እና ትምህርቶችን እንዴት እንደምታስተምሩም ዘርዝራችሁ ጻፉ። የክፍል አባላትን የሚረጡ ጥያቄዎችን አስቡባቸው።

  • በንግግሮች ውስጥ መሰረታዊ መርሆችን እና ትምህርቶችን ፈልጉ።

  • ስለትርጉማቸው አስቡበት።

  • የተረዱትን፣ ሀሳባቸውን፣ አጋጣሚያቸውን፣ እና ምስክሮችን ይካፈሉ።

  • እነዚህን መሰረታዊ መርሆች እና ትምህርቶች በህይወታቸው ይጠቀሙባቸው።

ትምህርቶቹ የሚማሩበት ወራት

የአራተኛው እሁድ የትምህርት ማስረጃዎች

ጥቅምት 2012 (እ.ኤ.አ)–ሚያዝያ 2013 (እ.ኤ.አ)

በጥቅምት 2012 (እ.ኤ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ የተሰጠ ንግግር*

ሚያዝያ 2012 (እ.ኤ.አ)–ጥቅምት 2012 (እ.ኤ.አ)

በሚያዝያ 2013 (እ.ኤ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ የተሰጠ ንግግር*

  • ለሚያዝያ እና ለጥቅምት የአራተኛ ሰንበት ትምህርቶች፣ ወደፊት ከነበሩት ወይም በቅርብ ከነበሩት የጉባኤ ንግግሮች መምረጥ ይቻላል። እነዚህ ንግግሮች (በብዙ ቋንቋዎች) በ conference.lds.org ውስጥ ይገኛሉ።

አትም