2020 (እ.አ.አ)
በቤተሰብ ታሪክ በኩል ማገልገል
የካቲት 2020 (እ.አ.አ)


የአገልግሎት መርሆች፣ የካቲት 2020 (እ.አ.አ.)

በቤተሰብ ታሪክ በኩል ማገልገል

ምስል
ministering

ተምሳሌተ ሰዕል በጆሽዋ ዴኒስ; የበስተጀርባ ምስል እና ፎቶግራፍ ከጌቲ ምስሎች

አንድን ሰው በቤተሰቡ ታሪክ መርዳት የአገልግሎት ታላቅ መንገድ ነው። በቤተሰብ ታሪኮች እና ዝርዝሮች አማካኝነት ሌሎችን ከአያቶቻቸው ጋር ስታገናኙ አንዳንድ ጊዜ እንደነበሩባቸው እንኳን የማያውቋቸውን በልቦቻቸው ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን ትሞላላችሁ፡፡ (ሚልኪያስ 4፤ 5–6)

የህይወት ዘመን የቤተክርስቲያን አባል ይሁን ወይም ዳግም ስለተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሰምቶ የማያውቅ ሰው የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ከየት እንደመጡ ለማወቅ ጉጉት አላቸው ፡፡

በሚቀጥሉት ታሪኮች ውስጥ እንደተመለከተው ጥልቅ እና ዘላቂ የሆነ ስሜት ለመተው ብዙ ጊዜ አይፈጅም ።

በ 30,000 ጫማ ከፍታ ላይ ቤተሰብን ማግኘት

በቅርቡ ወደ አገሬ እየበረርኩኝ ሳለሁ ፣ የግል ታሪኩን በትንሹ ካካፈለኝ ከስቲቭ አጠገብ ተቀምጬ ነበር፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ነበር በ 18 ዓመቱም በአሜሪካ ጦር ኃይል ውስጥ የግንኙነት ባለሙያ ሆነ እናም ብዙም ሳይቆይ ለአሜሪካ ፕሬዚዳንት የግንኙነት ድጋፍ በመስጠት በዋይት ሀውስ ውስጥ መሥራት ጀመረ ፡፡ ከ 18 እስከ 26 አመት ዕድሜው ሁለት የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶችን አገልግሏል ፡፡ የእሱ ታሪኮች አስገራሚ ነበሩ!

እኔም “ስቲቭ፣“አልኩት “ እነዚህን ታሪኮች ለትውልድ ትውልድህ መጻፍ አለብህ! እነዚህን ታሪኮች ከምንጩ ከአንተ እይታ አንጻር ማግኘት ያስፈልጋቸዋል።” እርሱም ተስማማ፡፡

ከዛም መንፈስ ስለ አያቶቹ ምን እንደሚያውቅ እንድጠይቀው ገፋፋኝ ፡፡ በ 1860 በአሜሪካን የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በገጠር አካባቢ ዘመቻ ያካሂድ በነበረበት ወቅት ቤተሰቡ ከአብርሃም ሊንከን ጋር አንዴ እራት እንደበሉ የሚገልጽ ታሪክን ጨምሮ ስቲቭ ስለ እናቱ ወገን ብዙ ያውቅ ነበር ፡፡

ነገር ግን ፣ስለ አባቱ ወገን ብዙም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ የበለጠ ለማወቅ በጽኑ ፈለገ ፡፡ ስልኬን አውጥቼ FamilySearch መተግበሪያን ከፈትኩ “ስቲቭ ፣ ቤተሰብህን አሁኑኑ ማግኘት እንችላለን!”

ከአውሮፕላኑ የበረራ ላይ Wi-Fi ጋር ተገናኘሁ።። ሁለታችንም ማየት እንድንችል ስልኬን ከፊት ለፊቴ ባለው የመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጥኩት ፡፡ በFamilyTree መተግበሪያ ውስጥ ፈለግን፡፡ ከጥቂተ ደቂቃዎች በኃላም ሁለታችንም የወንድ አያቱን እና የሴት አያቱን የጋብቻ ምስክር ወረቀት በትኩረት እያየን ነበር።

“ እነሱ ናቸው!” አለ ፡፡ “የመጨረሻ ስሟን አሁን አስታወስኩት! ”

ሁለታችንም ላይ የደስታ መንፈስ ፈሰሰ። ለሚቀጥሉት 45 ደቂቃዎች ጥቂት ለሚያውቃቸው አያቶቹ መገለጫዎችን መገንባት ላይ ስንሰራ ቆየን ፡፡ በኮሎራዶ ውስጥ አብረን መፈለጋችንን እንደምንቀጥል ቃል እንድገባለት ጠየቀኝ፡፡ አውሮፕላኑ በማረፍ ላይ በነበረበት ወቅት አድራሻችንን ተለዋወጥን ፡፡

እኛ አሁን በ30 000 ጫማ (9,145 ሜትር)በአየር ላይ እየበረርን ነበር ፤ እጄን ከምታክል ትንሽ መሳሪያ ጋር፤ ከ 100 ዓመታት በፊት ተጋብተው የነበሩ ከእርሱ እና ከቤተሰቡ የጠፉ አንድ ወንድን እና አንዲት ሴትን እየፈለግን ፡፡ የማይታመን ነበር! እኛ ግን አገኘናቸው ፡፡ ቤተሰቦች ተገናኙ ፡፡ ታሪኮች ወደትውስታ መጡ፡፡ ለቴክኖሎጂው እና ለመሳሪያዎቹ የአመስጋኝነት ስሜት ተሰምቶን ነበር። ይህ ተአምር ከመሆን ያነሰ አልነበረም።

ዮናታን ፔቲ ፣ ኮሎራዶ ፣ አሜሪካ

በአዲስ ቤተሰብ ተከቦ

ማሪያ ከ20 ዓመት በላይ ንቁ ተሳታፊ አልነበረችም። ከጥቂት ወራት በፊት በቤተሰብ ቆጠራ እና በሌሎች መዝገቦች ውስጥ ቤተሰቧን እየፈለግን ከእሷ ጋር በእኛ ቤት ለሁለት ሰዓታት አሳለፍን ፡፡ በአንድ ወቅት ፣ ”በሕይወቴ በሙሉ ከማውቀው በላይ በሁለት ሰዓታት ውስጥ ስለ ቤተሰቤ የበለጠ ተምሬያለሁ! ” ስትል ጮክ ብላ አለቀሰች፡፡

የነበረን ቆይታ ሲያበቃ እኛ በ FamilyTree መተግበሪያ ላይ Relatives Around Me የሚለውን ገጽታ አስተዋውቅናት። ባሌ እና እኔ ከማሪያ ጋር ራቅ ያለ ዝምደና ያለን ሆኖ ተገኘ ፡፡ ብቻዋን እንደሆነች ይሰማት እንደነበር በመናገር እንደገናጮክ ብላ አነባች ፡፡ በአካባቢው ቤተሰብ እንዳላት አታውቅም ነበር ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ማሪያ ከኤጰስ ቆጶሳችን ጋር ተገናኘች። አሁን ለቤተመቅደስ በመዘጋጀት ላይ እየሰራች ነው እንዲሁም በእኛ አጥቢያ ውስጥ ብዙ “አዳዲስ” መሰሎችዋን አግኝታለች!

ካሮል ራይን ኤቨሬት ፣ ሰሜን ካሮላይና ፣ አሜሪካ

ለአገልጋይነት የአዘገጃጀት መመሪያ

አሽሊ የተባለች የማገለግላት እህት እና እኔ ሁለታችንም ከአያቶቻችን ያገኘናቸው ስለምግብ አዘገጃጀት የሚያወሱ መጽሐፍት አሉን ፡፡ የእርሷ ከሴት ቅድመ አያቷ የኔ ደግሞ አያቴ ከሞተች በኋላ ከእሷ ከወረስኩት የግሪንውድ የምግብ አዘገጃጀት መመሪያ ሳጥን ውስጥ ካገኝሁት ያዘጋጅሁት መጽሐፍ ነው ፡፡

አሽሊ እና እኔ ሁለታችንም የምግብ አዘገጃጀት መመሪያችን ከምግብ ማብሰያ መጽሀፎቻችን ውስጥ መረጥን እናም እነሱን ለመሞከር አንድ ሌሊት ከስራ በኋላ ተሰብስበን ነበር ፡፡ አሷ የጣፋጭ ምግብ አዘገጃጀት መረጠች፤ ስለዚህ የመጀመሪያው አደረግነው እና የምግብ ማብሰያ ማሽኑ ውስጥ ከተት ነው። እኔ ቺፕ ዲፕ መረጥኩኝ —በእያንዳንዱ የግሪንውድ የቤተሰብ ድግስ ላይ የሚቀርብ ሰቴፕል ። የአሽሊ ሴት ልጅ አሊስ ምግቡን በቅምሻ እንድንሞክር ረዳችን። ከዚያ አሽሊ ልጆችዋ ሁሉንም ጣፋጮች እንዲበሉ ስላልፈለገች ፤ የተወሰነውን እሷ ለምታገለግላቸው እህቶች ሰጠች።

ከምግብ አዘገጃጀት ምሽታችን በጣም የወደድኩት ነገር ቢኖር ምግብ እያብሰልን እና እየጋገርን ሳለን ስለ መደበኛ የአገልግሎት ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉ — የእርሷን እና የእኔን ፈተናዎቸ ተነጋገርን ፡፡ እናም ደግሞ ለሁለታችንም ሩህሩህ ስለነበሩት ስለ አያቶቻችን እና ስለእናቶቻችን አወራን ፡፡

ጄኒፈር ግሪንውድ ፣ ዩታ ፣ አሜሪካ

ለመርዳት ልዩ መንገዶች

ሌላ ምንም አጋጣሚ የሌለ በሚመስልበት ጊዜ የቤተሰብ ታሪክ ለአገልግሎት አጋጣሚዎች በር ሊከፍት ይችላል ፡፡ ሊሞክሯቸው የሚችሉ ጥቂት ሀሳቦች እነሆ።።

  • የቤተሰብ ታሪክ ትረካዎችን በድምፅ እንዲቀዱ እና ወደመተግበሪያው እንዲጭኑ ይርዷቸው ፣ በተለይም ከፎቶግራፎች ጋር የሚዛመዱትን ፡፡

  • እንደ ስጦታ ሊሰጡት የሚችሏቸውን የአድናቂ ገበታ ወይም ሌላ ሊታተም የሚችል የቤተሰብ ታሪክ ሰነድ ይፍጠሩ ፡፡

  • በሚያስደስታቸው መንገድ ጆርናላቸውን በመያዝ የራሳቸውን ታሪክ የመመዝገብ መንገዶችን ያስተምሩ፡፡ የድምፅ ጆርናል? የፎቶ መጽሔት? የቪዲዮ ምዝግብ ማስታወሻዎች? የተለመዱ የጆርናል አይነቶችን ለማይወዱ ብዙ አማራጮች አሉ ፡፡

  • ለቅድመአያቶች ስርዓቶችን ለመስራት አብረው ወደ ቤተመቅደስ ይሂዱ። ወይም ሊሰሩ ከሚችሉት በላይ የቤተሰባቸውን ስሞች ከያዙ ለቤተሰቦቻቸው ስርዓቶችን ለመስራት ግብዣ አቅርቡላቸው ፡፡

  • የቤተሰብ ባህሎችን ለማካፈል ተሰባሰቡ ፡፡

  • የቤተሰብ ታሪክ ትምህርት አንድ ላይ ተማሩ፡፡

አትም