2020 (እ.አ.አ)
በቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴዎች በኩል ማገልገል
ሐምሌ 2020 (እ.አ.አ)


“በቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴዎች በኩል ማገልገል፣” ሊያሆና፣ ሐምሌ 2020 (እ.አ.አ)

ምስል
አገልግሎት

ወጣት ወንዶች ድንኳን ሲያቆሙ የሚያሳይ በቡድ ኮርኪን የተነሳ ፎቶግራፍ፤ ጠረጴዛ እያስተካከለች ያለች የሴትን የሚአሳይ በሼሪ ፐራይስ ማክፋርላንድ የተነሳ ፎቶግራፍ፣ የጀርባ ምስልም ከጌቲ ኢሜጅስ

የአገልግሎት መርሆች፣ ሐምሌ 2020 (እ.አ.አ)

በቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴዎች በኩል ማገልገል

የአርታኢ ማስታወሻ፥ ይህ አንቀፅ የተፈጠረው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት ነበር፡፡ ከዚህ በታች የቀረቡት አንዳንድ ሀሳቦች ማህበራዊ ርቀትን በምንጠብቅበት ጊዜ ውስጥ ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፣ ነገር ግን የቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች እና እንቅስቃሴዎች እንደገና ከተጀመሩ በኋላ የሚተገበሩ ይሆናሉ። አስፈላጊ ከሆነም፣ እባክዎን እነዚህን ምክሮች ከወቅቱ የቤተክርስቲያኗ እና የመንግስት መመሪያዎች ጋር በማስማማት ይተግብሩ፡፡

የአጥቢያ አባላቶቻችንን፣ ጎረቤቶቻችንን እና ለጓደኞቻችንን ለማገልገል የምንችልበት አንደኛው መንገድ በቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴዎች አማካይነት ነው፡፡ በምታገለግሉት ሰው ፍላጎቶች ወይም ዝንባሌዎች ዙሪያ እንቅስቃሴን ብታቅዱም ሆነ በሌሎች እንቅስቃሴዎች ወይም የአገልግሎት ዕድሎች ላይ እንዲሳተፉ ብትጋብዟቸውም፣ በአጥቢያ፣ በካስማ ወይም በጥምር ካስማ ደረጃ ያሉ እንቅስቃሴዎች አንድነትን ለማጎልበት እና አባላትን ለማጠናከር ትርጉም ያለው እና አዝናኝ መንገዶችን ሊሰጡ ይችላሉ።

የቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴዎች ለማገልገል የሚያስችሉ ብዙ በሮችን ሊከፍቱ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴዎች ሌሎችን ለመባረክ እና በማህበረሰቡ ውስጥ ጥሩ ግንኙነቶችን ለመገንባት በሚያስችለ የአገልግሎት ፕሮጄክቶች ውስጥ ለመሳተፍ እድሎችን ሊያቀርቡ ይችላሉ። የቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴዎች በተሳታፊነት አነስተኛ ከሆኑ የቤተክርስቲያን አባላት እና የሌሎች እምነቶች አባላት ከሆኑ ጓደኞቻችን ወይም ከየትኛውም ሃይማኖት ጋር ግንኙነት ከሌላቸው ጓደኞቻችን ጋር ለመቀራረብ እድል ሊሰጡን ይችላሉ፡፡

በቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ብዙ ሰዎችን ማካተት ጌታ አጥቢያዎቻችንን እና ቅርንጫፎቻችንን፣ ሰፈሮቻችንን እና ማህበረሰባችንን የሚባርክበት እና የሚያጠናክርበት እድል ይፈጥራል።

አዎንታዊ ግንኙነቶችን መገንባት

ክረምቱ እየመጣ ነበር እናም ዴቪድ ዲክስን ቤተሰቡን እንዴት ማሞቅ እንደሚችል አያውቅም ነበር፡፡

ዴቪድ፣ ባለቤቱ፣ እና ሁለት ሴት ልጆቹ በቀይ ቋጥኞች በቁጥቋጧማ እና በአረንጎዴ የተከበበ ግዙፍ በረሃማ መልክዐምድር የገጠር ከተማ ወደሆነው ፍሬዶኒያ አሪዞና፣ ዩ.ኤስ.ኤ. ውስጥ ለመኖር በቅርብ ደርሰው ነበር፡፡

የዲክስን ቤተሰብ የተከራዩት ቤት እንደ ዋናው የሙቀት ምንጭ በምድጃ ላይ የሚነድ እንጨትን ይጠቀም ነበር፡፡ የፍሬዶኒያ ክረምት ወቅት በበረዶ የምትሞላ ስለሆነ፣ ዴቪድ የማገዶ እንጨት መሰብሰብ አስፈላጊ ክህሎት መሆኑን በፍጥነት ተገነዘበ፡፡

“ምንም የማገዶ እንጨት ወይም በሞተር የሚሰራ መጋዝም ሆነ እንዴት መጠቀም እንኳን እንደሚቻል ዕውቀት አልነበረኝም!” አለ ዴቪድ። “ምን እንደማደርግ አላውቅም ነበር፡፡”

አንዳንድ የአጥቢያው አባላት ቤተሰቡ ክረምቱን ለማለፍ በቂ እንጨት እንዳለው ዴቪድን ጠየቁት፡፡ ዴቪድም “እንደሌለኝ ለመገንዘብ ረጅም ጊዜ አልወሰደባቸውም” አለ። “የሽማግሌዎች ሸንጎ ወዲያው እንጨቱን ለመሰብሰብ ሊረዱኝ መጡ። በከፍተኛ የምስጋና ስሜት፣ እርዳታችውን ተቀበልኩ።”

ዴቪድ ብዙም ሳይቆይ ይህ እንጨት-የመሰብሰብ ጉዞ በደንብ የታቀዱ፣ በደንብ የተደራጁ እና በደንብ የተለማመዱ የአጥቢያ እንቅስቃሴ መሆናቸውን ተረዳ፡፡ አንድ ቅዳሜ ጠዋት፣ ዴቪድ ፣ የሽማግሌዎች ቡድን እና ሌሎች የአጥቢያ አባላት በየጭነት መኪናዎች እና ተጎታቾች ገጥመው ወደ ተራሮች ተጓዙ።

ዴቪድም እንዲህ አለ፣ “በአንድ ከሰዓት በኋላ፣ በእነርሱ መሣሪያዎች እና እውቀት ምክንያት፣ የአጥቢያው አባላት ለሁለት ክረምት በቂ የሆነ የእንጨት ክምር ሰጡኝ። ከሁሉም ይበልጥ፣ እኔ በራሴ እንጨት ለመሰብሰብ ማወቅ የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ ተማርኩኝ። ፍሬዶኒያን ለቅቄ በወጣሁበት ጊዜ በሞተር የሚሰራ መጋዝ እንዴት እንደሚያዝ አውቅ ነበር፣ እናም መቁጠር ከምችለው በላይ ብዙ በአጥቢያ እንጨት-የመሰብሰብ እንቅስቃሴዎች አግዣለሁ።”

እንደእነዚህ ያሉት የአጥቢያ እንቅስቃሴዎች በቤተክርስቲያኗ አባላት መካከል መልካም ግንኙነቶችን መገንባት ብቻ ሳይሆን ከእያንዳንዱ የማህበረሰቡ አባል ሁሉ ጋር መልካም ግንኙነቶችንም ይገነባል።

ዴቪድ እንዲህ አለ፣ “ለአካባቢው አዲስ የነበረችን የቤተክርስቲያን አባል ያልሆነችን ሴት አስታውሳለሁ።” “እሷም ሙቀትን ለማግኘት ከቤቷ የእንጨት ጣውላን እየነቀለች ታቃጥል ነበር። ስለ እርሷ አስቸጋሪ ሁኔታ ካወቅን በኋላ፣ ክረምቱን ለማለፍ በቂ የሚሆን እንጨት እንዲኖራት በማድረግ አረጋገጥረጋን፡፡ በጣም አመስጋኝ ከመሆኗ ብዛት መናገር አልቻለችም ነበር።”

ፍሬዶኒያ ውስጥ የነበሩት የአገልግሎት ጥረቶች ሁሉም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እና በክረምቱ ወቅት ሙቀት ውስጥ እንዲቆይ አስችሏል።

ለሌሎች መድረስ

ሜግ ዮስት እና ጓደኛዋ በሮሜንያ ሚስዮን እያገለገሉ ሳሉ ለረጅም ግዜ ቤተክርስቲያን መምጣት ያቆሙትን ቤተሰቦች አዘውትረው ይጎበኙ ነበር። “የስታኒካ ቤተሰብ በሮሜንያ ውስጥ ከሚገኙት የመጀመሪያዎቹ የቤተክርስቲያን አባላት መካከል ነበሩ፣ እናም እኛ እነወዳቸው ነበር፣” አለች ሜግ።

የቅርንጫፍ እንቅስቃሴን ለማቀድ እና ለማደራጀት ጊዜው ሲደርስ፣ መሪዎች ቅርንጫፉ “የፈር ቀዳጆች ምሽት” እንዲሆን ወሰኑ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስን አቋርጠው ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ የሄዱትን ጀግና ፈር ቀዳጆች የሚዘከሩበት ምሽት ይሆናል። እንዲሁም በሮማንያ ውስጥ ያሉትን የቤተክርስቲያኗ ፈር ቀዳጆችን ለማክበርም እድል ይሆን ነበር።

ሜግ እንዲህ አለች፣ “አንዳንድ አባላት ስለመለወጣቸው ምስክርነት የሚሰጡበት እና ቤተክርስቲያኗ በሮማንያ ውስጥ እንዴት እንዳደገች ለመመስከር ጥሩ መንገድ እንደሚሆናቸው አስበን ነበር። የነስታኒካ ቤተሰብ መሳተፍ እንዳለበት ወዲያውኑ አሰብን። እንዲሳተፉ ጋበዝናቸው፣ እናም እነሱ በጣም ተደሰቱ!”

በእንቅስቃሴው ምሽት እንቅስቃሴው የሚጀመርበት ሰአት ቢደርስም እነስታኒካ ገና አልደረሱም ነበር።

ሜግ እንዳስታወሰችውም፣ “አይመጡም የሚል ስጋት አደሮብን ነበር። ነገር ግን ልክ በሰአቱ በበሩ አልፈው ገቡ፡፡ የስታኒካ ቤተሰብ ስለወንጌል እና ሰለቤተክርስቲያኗ ቆንጆ ምስክርነት ሰጡ፡፡ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ ካላዩዋቸው ሌሎች አባላት ጋር መስተጋብር ሊፈጥሩ ችለው ነበር፡፡”

የቅርንጫፉ አባላት እጆቻቸውን ከፍተው እነስታኒካን ተቀበሏቸው፡፡ በቀጣዩ እሁድም፣ ሜግ እኅት ስታኒካ በቤተክርስቲያን በመገኘቷ በደስታ ተገረመች።

“ከጥቂት ወራት በኋላ ቅርንጫፍን ስጎበኝ፣ አሁንም ተሳታፊ ነበረች!” አለች ሜግ። “ምስክርነቷን ለመስጠት እና በቅርንጫፍ ውስጥ ተሳታፊ እና የምትፈለግ እንደሆነች እንዲሰማት እድል ማግኘቷ በእውነት ረድቷታል።”

በቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴዎች በኩል ለማገልገል የሚቀርቡ 4 ሀሳቦች

  • ፍላጎቶችን የሚያሟሉ ተግባሮችን ያቅዱ፥ እንቅስቃሴዎች ብዙ የተለያዩ ፍላጎቶችን ለማሟላት ጥሩ መንገድ ናቸው። የግለሰቦችን ወይም የቡድንን የተወሰኑ ፍላጎቶችን ለማሟላት የታቀዱ ሊሆኑ ይችላሉ። ፍላጎቱ እርስ በእርስ ለመተዋወቅም፣ ስለ ወንጌል የበለጠ ለመማር፣ ወይም መንፈስ እንዲማ ለማድረግ ቢሆንም፣ እነዚህም የተሳተፊዎችን ፍላጎቶችን ማሟላት ይገባቸዋል፡፡

  • ሁሉንም ይጋብዙ፥ እንቅስቃሴዎችን ሲታቅዱ፣ በመሳተፋቸው ተጠቃሚ የሚሆኑትን ለመጋበዝ ልዩ ጥረት ያድርጉ። አዳዲስ አባላትን፣ ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑ አባላትን፣ ወጣቶችን፣ ያላገቡ ጎልማሶችን፣ የአካል ጉዳተኞችን እና የሌሎች እምነት ተከታዮችን ያስተውሉ፡፡ ግብዣውንም ፍላጎታቸውን ከግምት በማስገባት ያስተላልፉ፣ እና እነርሱ እንዲገኙ ምን ያህል እንደምትወዱ አስረዷቸው።

  • ተሳትፎን አበረታቱ፥ የጋበዛችኋቸው ሰዎች የመሳተፍ እድል ካገኙ ከእነዚያ እንቅስቃሴዎች ብዙ ይጠቀማሉ፡፡ ተሳትፎን ለማበረታታት አንዱ መንገድ በእንቅስቃሴው ወቅት ግለሰቦች ስጦታቸውን፣ ችሎታቸውን እና ክህሎታቸውን እንዲጠቀሙ ማድረግ ነው፡፡

  • ለሁሉም ተቀባይነት እንዲሰማቸው አድርጉ፥ ጓደኞቻችሁ በአንድ እንቅስቃሴ ላይ ከተሳተፉ፣ ተቀባይነት እንዳላቸው ለማሳየት የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡ በተመሳሳይም፣ የማታውቋቸውን ሰዎች ካያችሁ፣ ተግባቢ ሁኑ እና ተቀባይነት እንዲሰማቸው አድርጉ!

አትም