2020 (እ.አ.አ)
በልጆች እና ወጣቶች ፕሮግራም በኩል ማገልገል
ጥቅምት 2020 (እ.አ.አ)


“በልጆችና በወጣቶች ፕሮግራም በኩል ማገልገል፣” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2020 (እ.አ.አ.)

ምስል
የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች

ፎቶግራፎች በቶማስ ጋርነር፣ በአይዛክ ዳርኮ-አቼምፖንግ፣ በአሌክሳንደር ኬ. ቦትንግ እና በጆናስ ሬቢኪ

የአገልግሎት መሰረታዊ መርሆች፣ ጥቅምት 2020 (እ.አ.አ.)

በልጆች እና ወጣቶች ፕሮግራም በኩል ማገልገል

ሌሎች እንዲያድጉ መጋበዝ እና በእድገት ጎዳናቸው ላይም መርዳት የአገልግሎት ዋና መሰረታዊ ነጥብ ነው።

በልጆች እና በወጣቶች ፕሮግራም ውስጥ ለማገልገል ያሉ እድሎች በብዛት ይገኛሉ። ምናልባት በቤት ውስጥ የግል ልጆች ወይም ወጣቶች ሊኖርዎት ይችላሉ። ምናልባት በፕሮግራሙ ውስጥ መሪ ሊሆኑ ወይም ልጆች እና ወጣቶች ላሏቸው ቤተሰቦች የሚያገለግሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ወይም ምናልባት አንዳንድ ልጆችን እና ወጣቶችን ያውቁ ይሆናል (ያም እኛ ሁላችንንም ይሸፍናል)። ሁኔታዎ ምንም ይሁን ምን፣ ፕሮግራሙን ወይም መሠረታዊ መርሆቹን በመጠቀም የሌሎችን ሕይወት ለመባረክ የሚችሉባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።

ራሳችንን በህብረት መገንባት

የልጆች እና የወጣቶች ፕሮግራም ትኩረት ማእከላዊ እምብርትም ያለእንከን እንዳገለገለው እንደ አዳኙ ለመሆን በየቀኑ ይበልጥ መጣር ነው። በፕሮግራሙ ውስጥ ተሳትፈው የነበሩ.ብዙዎች በተለያዩ የህይወታችሁ ዘርፎች ባደጋችሁ ቁጥር ሌሎችን ለመርዳት ወይም ለማገልገል የተሻለ ብቁ እንደምትሆኑ ተምረዋል።

ነገር ግን በልጆች እና በወጣቶች ፕሮግራም ውስጥ፣ ሌሎችን ለመባረክ አንድ ነገር እስክትማሩ ድረስ መጠበቅ የሚያስፈልጋችሁ አይደለም። የመማር ተግባር እራሱ ለማገልገል እድሎችን ይሰጣል።

በጋና ለሚኖረው ፕሮፌት ለተባለው አንድ ወጣት፣ በልጆችና ወጣቶች ፕሮግራም ውስጥ ፒያኖ ለመጫወት የመማርን ግብ ማስቀመጡ ጅማሬ ብቻ ነበር። ፕሮፌትም “እኔ የምማራውን ሌሎች ሰዎች እንዲያውቁ መርዳትም ግቤ ነው” ብሏል።

ምንም እንኳን ገና አስተማሪ ባይሆንም፣ ግቡ እሱ ከጠበቀው በላይ ትልቅ ነገር ሆኖ አድጓል። አሁን በስብሰባው ቤት ውስጥ ፒያኖ ትምህርቶችን የሚወስዱ 50 ተማሪዎች ከፕሮፌት ጋር አሉ። ታዲያ ፕሮፌትን እና እነዚያን ሌሎች 50 ተማሪዎች የሚያስተምረው ማነው? አሌክሳንደር ኤም እና ኬልቪን ኤም፣ ሁለቱም ዕድሜያቸው 13 ነው። ኬልቪንም “ለሌሎች ሰዎች ደግነት ማሳየት እንፈልጋለን” ብሏል።

ሁለቱ ወጣቶች ለመማር ለሚመጡት ሁሉ መሰረታዊ የፒያኖ ትምህርቶችን በሳምንት ለሦስት ቀናት በነጻ ያስተምራሉ። የፒያኖ ትምህርቶቹ ተጨማሪ ጥቅምም አላቸው። በፒያኖ ትምህርቶች አማካኝነት ከቤተክርስቲያኗ ጋር ከተዋወቁት ተማሪዎች በርከት ያሉተት በኋላ ላይ ወንጌልን አጥንተው ለመጠመቅ ወሰኑ።

እራሳችንን ለማሻሻል ጥረት ስናደርግ፣ ከእኛ ጋር እንዲቀላቀሉ በመጋበዝ ሌሎችን ማገልገል እንችላለን።

የአገልግሎት ውጤታማ ዘዴ

የኩሪቲባ፣ ብራዚል ነዋሪዋ ሳብሪና ሲሞኤስ ዱስ አውጉስቶ እንደ ካስማ የመጀመሪያ ክፍል ፕሬዝዳንትነቷ፣ የፕሮግራሙ ግላዊ የልማት ገጽታዎች እድገት ልጆችን እና ወጣቶችን እንዴት እንደሚባርክ ተመልክታለች። ነገር ግን በአገልጋይ እህትነት በተመደበችበትም ስለ ግል እድገት የተማረችውን የምትጠቀምባቸው ብዙ መንገዶችንም አይታለች።

እህት አውጉስቶ እንዲህ ብላለች፣ “አንድ ችሎታን ባዳበርኩ ጊዜ፣ ያንን ችሎታ የማገለግለውን ሰው ለመባረክ መጠቀም እችለሁ።”

እህት አውጉስቶ ከተመደቡላት እህቶች ለአንዷ ቾኮሌት እንዴት እንደሚሠራ አስተማረቻት። ያቺም እህት አሁን የቤተሰቧን ገቢ ለመደጎም ቾኮሌቶችን እየሰራች ትሸጣለች። እህት አውጉስቶም “ከወራት በኋላ፣ መሸጥ የምችለው የማር እንጀራ ዳቦ እንዴት መሥራት እንደምችል ሌላ እህት እኔን በማስተማሯ ተባርኬያለሁ” ብላለች። “ችሎታችንን ማዳበራችን እና ማጋራታችን አንዳችን የሌላውን ህይወት ሊባርክልን እና እንደ አገልግሎት እህቶች ግንኙነታችንን ይበልጥ ጥልቅ ሊያደርግልን ይችላል።”

አትም