2022 (እ.አ.አ)
ውድቀት የእግዚአብሔር ዕቅድ አካል ነበር
ጥር 2022 (እ.አ.አ)


“ውድቀት የእግዚአብሔር ዕቅድ አካል ነበር፣” ሊያሆና፣ ጥር 2022 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ጥር 2022 (እ.አ.አ)

ውድቀት የእግዚአብሔር ዕቅድ አካል ነበር

በውድቀት ምክንያት ወደ ምድር መጣን እናም አንድ ቀን ከአባታችን ጋር በሰማይ ለመኖር መመለስ እንችላለን።

ምስል
አዳም እና ሔዋን

አዳም እና ሔዋን በኤደን የአትክልት ስፍራ ውስጥ፣ በሮበርት ቲ. ባሬት

በኤደን የአትክልት ስፍራ ውስጥ፣ እግዚአብሔር አዳምን እና ሔዋንን የመልካምን እና ክፉን የሚያሳውቀውን ፍሬ እንዳይበሉ አዘዘ። ከዚያም በኋላ እርሱ እንዲህ አላቸው፣ “ለራስህ መምረጥ አለብህ፣ … ነገር ግን እንደከለከልኩህ አስታውስ” (ሙሴ 3፥17)። ሰይጣን የዛፉን ፍሬ እንድትበላ ሔዋንን ፈተናት። እንዲህም ብሎ ነገራት፣ “እንደ እግዚአብሔርም መልካምን እና ክፉን [ታውቂያለሽ]” (ሙሴ 4፥11)። ፍሬውን በላች እና ከዛም ለአዳም አካፈለችው። እግዚአብሔር ከኤደን የአትክልት ስፍራ ውስጥ አባረራቸው።

ውድቀት

ምስል
አዳም እና ሔዋን

አዳም እና ሔዋን ከኤደን የአትክልት ስፍራ ተባረሩ፣ በጋሪ ኤል ካፕ፣ ሊቀዳ አይችልም

አዳም እና ሔዋን የኤደን የአትክልት ስፍራን ለቀው ሲሄዱ፣ ከዚያም ጊዜ በኋልአ በእግዚአብሔር ፊት መገኘት አልቻሉም ነበር። ይህ ከእግዚአብሔር መለየት የመንፈስ ሞት ተብሎ ይጠራል። የኤደንን የአትክልት ስፍራ ለቆ መሄድ ማለት አዳም እና ሔዋን ሟች ሆኑ እናም በዚህ ምክንያት መሞት ይችላሉ ማለት ነበር። አዳም እና ሔዋን ከእግዚአብሔር ጋር ባይሆኑም እና አሁን ሟች ቢሆኑም እንኳን፣ መሻሻል እንደሚችሉ ሲያውቁ ደስተኛ መሆን እና ተስፋ ማድረግ ቻሉ (ሙሴ 5፥10–11ን ይመልከቱ)። “ሰዎች እንዲኖሩ፣ አዳም ወደቀ፤ እና ሰዎች የሚኖሩትም ደስታም እንዲኖራቸው ዘንድ ነው” (2 ኔፊ 2፥25)።

የፈተና ጊዜ

ስንወለድ፣ ከእግዚአብሔር ተለይተን እንኖራልን፣ ልክ አዳም እና ሔዋን ከውድቀት በኋላ እንዳደረጉት። ሰይጣን መጥፎ ምርጫዎችን እንድናደርግ ይፈትነናል። እነዚህ ፈተናዎች እንድንፈተን እና በትክክል እና በስህተት መካከል እንድንመርጥ ይፈቅዱልናል (አልማ 12፥24ን ይመልከቱ)። ኃጢያት በሠራንና ንስሐ ባልገባን ቁጥር፣ ከሰማይ አባት የበለጠ እየራቅን እንሄዳለን። ነገር ግን ንስሃ ከገባን፣ ወደ ሰማይ አባታችን የበለጠ እየቀረብን እንሄዳለን።

ስጋዊ ሞት

ምስል
የመቃብር ቦታ

ምድር ለእኛ ነው የተፈጠረችው (1 ኔፊ 17፥36ን ይመልከቱ)። ውድቀቱ አዳም እና ሔዋን ልጆች እንዲኖራቸው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንዲጠብቁ አስችሏቸዋል፣ ይህም በአካላዊ ሰውነት ወደ ምድር እንድንመጣ አስችሎናል። አካላቶቻችን አንድ ቀን ይሞታሉ፣ ነገር ግን ነፍሶቻችን መኖራቸውን ይቀጥላሉ። ትንሳኤ ስናደርግ አካላቶቻችን እና ነፍሶቻችን በድጋሜ ይዋሃዳሉ።

በኢየሱስ ክርስቶስ መዳን

ምስል
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ

ትንሳኤው፣ በሃሪ አንደርሰን

በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ኃይል አማካኝነት፣ አካላዊ እና መንፈሳዊ ሞትን ማሸነፍ እንችላለን። ክርስቶስ ከሞት በመነሳቱ ምክንያት፣ በዚህ ምድር ላይ የተወለደ እያንዳንዱ ሰው ከሞት በመነሳት ለዘለአለም ይኖራል። እናም ክርስቶስ ለኃጢያቶቻችን ስለተሰቃየልን፣ ከሰማይ አባታችን ጋር በድጋሜ ለመኖር እንድንችል ንስሃ መግባት እና ይቅርታን ማግኘት እንችላለን።

አትም