ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
አባሪ መ፦ ለአሮናዊ ክህነት ቡድን እና ለወጣት ሴቶች ክፍሎች—የስብሰባ አጀንዳዎች


አባሪ መ፦ ለአሮናዊ ክህነት ቡድን እና ለወጣት ሴቶች ክፍሎች—የስብሰባ አጀንዳዎች ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስትኢያን ፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2023 ( እ.አ.አ)]

“አባሪ መ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ)

አባሪ መ

ለአሮናዊ ክህነት ቡድን እና ለወጣት ሴቶች ክፍሎች—የስብሰባ አጀንዳዎች

የሥብሰባ ቀን፦

የሥብሰባው አስተባባሪ (የክፍል ወይም የቡድን አመራር አባል)።

መክፈቻ

መዝሙር (እንደ አስፈላጊነቱ)፦

ጸሎት፦

የወጣት ሴቶችን ወይም የአሮናዊ ክህነት ቡድን ጭብጥን ከልሱ።

አብራችሁ ተመካከሩ።

ሥብሰባውን በሚያስተባብረው ሰው በመመራት ክፍሉ ወይም ቡድኑ ከ5 እስከ 10 ለሚሆኑ ደቂቃዎች በደህንነት እና በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግ ሥራ ላይ ስላላቸው ሀላፊነት በጋራ ይመክራል። ይህ በክፍል ወይም በቡድን የአመራር ስብሰባ ወይም የአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ውይይት በተደረገባቸው ነገሮች ላይ ክትትል ለማድረግ መልካም አጋጣሚ ነው።

ስብሰባውን የሚያስተባብረው ግለሰብ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ወይም ከአንድ በላይ ጥያቄዎችን ሊጠቀምም ይችላል።

ወንጌልን መኖር

  • ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ወንጌሉ ያለንን ምስክርነት ያጠናከሩልን የቅርብ ጊዜ ተሞክሮዎች የትኞቹ ናቸው?

  • ወደ አዳኙ ለመቅረብ ምን እያደረግን ነው? የበለጠ እርሱን ለመምሰል እየሞከርን ያለነው እንዴት ነው?

  • የጌታ ምሪት በህይወታችን ውስጥ የተሰማን እንዴት ነው?

እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መንከባከብ።

  • ማንን የመርዳት እና የማገልገል ምሪት ተሰምቶናል? እርዳታ የሚፈልግን ለመርዳት ከኤጲስ ቆጶስ አመራሩ ምን የሥራ ድርሻ ተስጥቶናል?

  • በምናደርጋቸው ነገሮች እርስ በእርስ መደጋገፍ የምንችለው እንዴት ነው?

  • በቅርቡ ወደ አጥቢያችን የተዛወረ ወይም ቤተክርስቲያኗን የተቀላቀለ ሰው አለ? መልካም አቀባበል እንደሚደረግላቸው እንዲሰማቸው እንዴት መርዳት እንችላለን?

ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ

  • ሌሎች የእግዚአብሄር ፍቅር እንዲሰማቸው ለመርዳት ምን ልናደርግ እንችላለን?

  • ጓደኞቻችን እንዲሳተፉ የምንጋብዝባቸው ምን ዓይነት አክቲቪቲዎችን እያሰብን ነው?

  • በአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ ወንጌልን ማካፈልን የተመለከቱ ምን እቅዶች ውይይት ተደርጎባቸዋል? ክፍላችን ወይም ቡድናችን መሳተፍ የሚችለው እንዴት ነው?

ቤተሰቦችን ለዘላለም ማጣመር

  • ከአያቶቻቸን እንዲሁም ከአክስቶቻችን እና ከአጎቶቻቸን ልጆች ጋር ጨምሮ ከቤተሰብ አባላት ጋር በተሻለ ሁኔታ የምንገናኝባቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ምን ናቸው?

  • የቤተመቅደስ ሥርዓቶች የሚያስፈልጓቸው ቅድመ ዓያቶቻቸንን ሥም ለመፈለግ ምን እያደረግን ነው? ሌሎች የቅድመ አያቶቻቸውን ሥም እንዲያገኙ ለመርዳት ምን ልናደርግ እንችላለን?

  • በግለሰብ እንዲሁም በክፍል ወይም በቡድን ደረጃ በቤተመቀደስ ሥራ የበለጠ መሳተፍ የምንችለው እንዴት ነው?

አንድ ላይ ተማሩ።

አንድ ጎልማሳ መሪ ወይም የቡድን ወይም የክፍል አባል የዚህን ሳምንት የኑ፤ ተከተሉኝ ንባብ ይመራል። እርሱ ወይም እርሷ በኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ይጥናት ሃሳቦች ይጠቀማሉ። በዚህ ምልክት ጋር ያለው የጥናት ሃሳብ ከሴሚናሪ ጋር የተያያዘ ነው ስለዚህ በተለይ ለወጣቶች የሚሆን ነው። ሆኖም የትኛውንም የጥናት ሃሳብ መጠቀም ይቻላል። ይህ የስብሰባው ክፍል በአጠቃላይ ከ35 እስከ 40 ደቂቃዎችን ይወስዳል።

መዝጊያ

ስብሰባውን የሚያስተባብረው ግለሰብ

  • ስለ መርሆዎቹ በተሰጠው ትምህርት ላይ ምስክርነቱን ይሰጣል።

  • ክፍሉ ወይም ቡድኑ የተማሩትን ነገር በቡድን ወይም በግል እንዴት በስራ ላይ እንደሚያውሉ ይወያያል።

ጸሎት፦

አትም