“የቀዳሚ አመራር መልእክት”፡- ወንጌሌን ስበኩ፡- የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የማካፈል መመርያ (2023 (እ.አ.አ))
“የቀዳሚ አመራር መልእክት” ወንጌሌን ስበኩ
የቀዳሚ አመራር መልእክት
ውድ ሚስዮናውያን፡-
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሚስዮናዊ ለመሆን ስላገኛችሁት ታላቅ እድል እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን። እስራኤልን ከመሰብሰብ የበለጠ ግድ የሚል ወይም ጠቃሚ ሥራ የለም።
ወንጌሌን ስበኩ የተሻለ እንድትዘጋጁ እና በመንፈሳዊነት የበሰላችሁ ሚስዮናዊ እንድትሆኑ እንዲረዳችሁ የታሰበ ነው። እንዲሁም የበለጠ ውጤታማ አስተማሪ እንድትሆኑ እንዲረዳችሁ የታሰበ ነው። በግል እና ከሚስዮናዊ ጓደኛችሁ ጋር በምታደርጉት ጥናት በየቀኑ እንድትጠቀሙበት እናሳስባለን። በአውራጃ የምክር ቤት ስብሰባዎቻችሁ እና በዞን ኮንፈረንሳችሁ ላይ እንድትጠቀሙት እናበረታታለን። የተጠቀሱ ቅዱሳት መጻህፍትን አጥኑ እንዲሁም ትምህርቱን እና መርሆዎቹን ተማሩ።
የሰማይ አባታችንን በክቡር ስራው ለመርዳት ወደ አዲስ የቁርጠኝነት ስሜት እንድትነሳሱ እንጋብዛቹኋለን። እያንዳንዱ ሚስዮናዊ ጌታ “የሰውን ህያውነት እና ዘላለማዊ ህይወት [በማምጣት]” (ሙሴ 1፡39) ስራው ለመርዳት ትልቅ ሚና አለው።
እርሱን ለማገልገል በትህትና ራሳችሁን ስትሰጡ ጌታ ይባርካችኋል። የሰማይ አባት ልጆችን በማገልገል በምትደክሙበት ጊዜ ታላቅ ደስታን አግኙ።
ቀዳሚ አመራር