ቅዱሳት መጻህፍት
መግቢያ


መግቢያ

የታላቅ ዋጋ ዕንቁ መፅሐፍ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እምነትና ትምህርትን የሚዳስሱ ተመራጭ መረጃዎችን የያዘ ነው። እነዚህ መረጃዎች በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ተተርጉመውና ተሰርተው፣ እናም አብዛኛዎቹ በጊዜው በቤተክርስቲያኗ ጋዜጣዎች ታትመው ነበር።

የታላቅ ዋጋ ዕንቁ የሚለውን ርዕስ የያዙት የመጀመሪያዎቹ ክምችቶች የታተሙት በ፲፰፻፶፩ (እ.አ.አ.) በዚያን ጊዜ የኢንግሊዝ ሚስዮን ፕሬዘደንትና የአስራ ሁለቱ ቡድን አባል በነበረው ካህን ፍራንክሊን ዲ ሪቻርድስ ነበር። የዚህም አላማ በጆሴፍ ስሚዝ ጊዜ የተወሰነ ስርጭት የነበራቸውን አስፈላጊ አንቀጾችን በቀላሉ እንዲገኙ ለማድረግ ነበር። የቤተክርስቲያኗ አባላት ቁጥር በአውሮፓና በአሜሪካ እያደገ ሲመጣም፣ እነዚህ ነገሮች እንዲገኙ ማድረግ ተፈላጊም ነበር። የታላቅ ዋጋ ዕንቁ መፅሃፍም ታላቅ ጥቅም ነበረው እና በዚህም ምክንያት በ ቤተክርስቲያኗ ቀዳሚ አመራር ስራና የጥቅምት ፲፣ ፲፰፻፹ (እ.አ.አ.) በሶልት ሌክ ስቲ ውስጥ በነበረው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ በወሰዱት እርምጃ ምክንያት ይፋ ከሆኑት የቤተክርስቲያኗ ጽሁፎች አንዱ ሆነ።

የቤተክርስቲያኗ ፍላጎት ባስፈለገበት ጊዜ በውስጡ ባሉት ነገሮች ላይ አንዳንድ ግምገማዎች ተደርገዋል። በ፲፰፻፸፰ (እ.አ.አ.) በመጀመሪያው ቅጂ ላይ ያልነበሩት የመፅሐፈ ሙሴ ክፍሎች ተጨምረዋል። በ፲፱፻፪ (እ.አ.አ.) በትምህርትና ቃል ኪዳን ውስጥ ከታተሙት ጋር አንድ አይነት የነበሩት አንዳንድ ክፍሎች ከታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ ወጥተዋል። በ፲፱፻፪ (እ.አ.አ.) ከግርጌ ማስታወሻ ጋር በምእራፎችና አንቀጾች ተከፋፍለው ተዘጋጅተው ነበር። ሁለት አምድ ገጾችና በመፅሀፉ መጨረሻ ላይ በፊደል ተራ የሚደረድር የተጨመሩበትም በ፲፱፻፳፩ (እ.አ.አ.) ነበር። በሚያዝያ ፲፱፻፸፮ (እ.አ.አ.) ከተጨመሩት ሁለት የራዕይ ነገሮች በስተቀር ሌላ ምንም ለውጦች አልተደረጉም። በ፲፱፻፸፱ (እ.አ.አ.) እነዚህ ሁለት ነገሮች ከየታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ ወጥተው በትምህርትና ቃል ኪዳን ውስጥ ተጨምረዋል፣ በዚያም ውስጥ እንደ ክፍል ፻፴፯ና ፻፴፰ ይገኛሉ። በአሁኑ ቅጂ ውስጥም ፅሁፎቹን ከቀድሞዎቹ ሰነዶች ጋር እንዲስማሙ ለማድረግ አንዳንድ ለውጦች ተደርገዋል።

የሚከተለው በአሁኑ መፅሐፍ አምዶች ውስጥ ያሉትን የሚያስተዋውቅ ነው፥

  1. ከመፅሐፈ ሙሴ የተመረጡ ምንባቦች። በሰኔ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) ጆሴፍ ስሚዝ ከጀመረው የመፅሀፍ ቅዱሱ ትርጉም፣ ከኦሪት ዘፍጥረት መፅሐፍ ውስጥ የተወሰደ ልዩ እትም።

  2. መፅሐፈ አብርሐም። በመነሳሳት የተተረጎሙ የአብርሐም ጽሁፎች። ጆሴፍ ስሚዝ ፔትርያርክ አብርሐም የጻፋቸውን የያዙ አንዳንድ የግብፅ ፓፓይሪ ካገኘ በኋላ በ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) ይተረጉማቸው ጀመረ። ይህ ትርጓሜ ከመጋቢት ፩፣ ፲፰፻፵፪ (እ.አ.አ.) ጀምሮ በናቩ፣ ኢለኖይ ውስጥ በTimes and Seasons ውስጥ በተከታታይነት ታትሞ ነበር።

  3. ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ። ከጆሴፍ ስሚዝ መፅሀፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውስጥ ከማቴዎስ ምስክር የተወሰደ ልዩ እትም። (አዲስ ኪዳንን ለመተርጎም እንዲጀመር የተሰጠውን መለኮታዊ ማገጃን በትምህርትና ቃል ኪዳን ፵፭፥፷–፷፩ ተመልከቱ።)

  4. የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ። በ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) እርሱ እና ጸሀፊው በ፲፰፻፴፰–፲፰፻፴፱ (እ.አ.አ.) ውስጥ ካዘጋጁት እና በመጋቢት ፲፭፣ ፲፰፻፵፪ (እ.አ.አ.) በናቩ ኢለኖይ በTimes and Seasons ውስጥ በተከታታይነት ከታተመው ከጆሴፍ ስሚዝ ህጋዊ ምስክርና ታሪክ ውስጥ የተወሰደ ምንባብ።

  5. የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የእምነት ሐተታ።Times and Seasons ውስጥ በህዳር ፩፣ ፲፰፻፵፪ (እ.አ.አ.)የወንትዎርዝ ደብዳቤ ተብሎ ከሚታወቀው ከቤተክርስቲያኗ አጭር ታሪክ ጋር አብሮ የታተመው የጆሴፍ ስሚዝ መግለጫ።