አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ዳቦ ለሚቋደሱት ነፍሳት ሁሉ የልጅህን አካል በማስታወስ እንዲበሉት እና፣ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ እነርሱ የልጅህን ስም በላያቸው ላይ ለመውሰድ ፈቃደኞች መሆናቸውን፣ እና ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱና እርሱ የሰጣቸውን ትእዛዛት እንደሚጠብቁ ለአንተም ይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ መንፈስ ሁልጊዜ እንዲኖራቸው ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሃለን። አሜን።