“አትፍራ—ጌታ ካንተ ጋር ነው፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሐምሌ 2022 (እ.አ.አ) ።
ወርሀዊ የ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሐምሌ 2022 (እ.አ.አ)
አትፍራ—ጌታ ካንተ ጋር ነው
ፍርሃት አዲስ ነገር አይደለም። ከጥንት ጊዜያት ጀምሮ፣ ፍርሃት የእግዚአብሔር ልጆችን አመለካከት ወስኖት ነበር። በ2ኛ ነገሥት፣ የሶርያ ንጉስ ነብዩ ኤልሳዕን ለመያዝ እና ለመግደል ሠራዊት ልኮ ነበር።
“የ[ኤልሳዕ] ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። የ[ኤልሳዕ] ሎሌም እንዲህ አለው፣ ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናደርጋለን? አለው።”” (2 ነገሥት 6፥15)።
ያ የፍራቻ ንግግር ነበር።
“[ኤልሳዕም] ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው።
“ኤልሳዕም፣ አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም፤ እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር” (2 ነገሥት 6፥16-17)።
ፍርሃታችንን ለማስወገድ እና ጋኔኖችን ለማሸነፍ የእሳት ሰረገላዎች ሊኖሩን ወይም ላይኖሩን ይችላል፣ ነገር ግን ትምህርቱ ግልጽ ነው። ጌታ ከእኛ ጋር ነው፣ ስለእኛ ያውቃል፣ እና እርሱ ብቻ መባረክ በሚችልበት መልኩ ይባርከናል።
በጌታ እና በመንገዱ በንቃት ከታመንን፣ በእርሱ ስራ ላይ ከተሰማራን፣ የአለምን አዝማሚያ አንፈራም ወይም በእነሱ አንጨነቅም። ጌታ ይጠብቀናል፣ ይንከባከበናል እና ከጎናችን ይቆማል።
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly For the Strength of Youth Message, July 2022ትርጉም። Amharic። 18298 506