2010–2019 (እ.አ.አ)
እነሆ! የንጉሳዊ ሠራዊት
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


2:3

እነሆ! የንጉሳዊ ሠራዊት

ለሁሉም የመልከ ፀዴቅ የክህነት ተሸካሚዎች ማስተማር፣ መማር፣ እና ትከሻ ለትከሻ አብሮ ማገልገል ምን ያህል ታላቅ ደስታ ይሆናል።

የተወደዳችሁ የክህነት ወንድሞቼ፣ ከእኛ ውድ ነብይ እና ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ሃላፊነት በመቀበል በዚህ ታሪካዊ ወቅት ከፊት ለፊታችሁ ስቆም በትልቅ ትህትና ነው። እኚህን ድንቅ የእግዚአብሔር ሰዎች እና የቅድሚያ አመራርን እወደዋለሁ። ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን እና ሌሎች የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ አባላቶች በዚህ ምሽት የተናገሩት ለውጦች የጌታ ፈቃድ እንደሆኑ የራሴን ምስክርነት እጨምራለሁ።

በፕሬዝዳንት ኔልሰን እንደተገለጸው ይህ ጉዳይ ለረዥም ጊዜ በቤተክርስቲያኗ ቀዳማይ ወንድማማች በጸሎት የታሰበበት እና ውይይት ተደርጎበት ነው። ምኞቱ የጌታን ፈቃድ መፈለግ እና የመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን ቡድኖችን ማጠናከር ነበር። የመንፈስ ምሪት ተገኝቷል፣ እናም በዚህ ምሽት ነቢያችን የጌታን ፈቃድ አሳወቁን። “በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።”1 ዛሬ ሕያው የሆነ ነቢይ በማግኘታችን ምን ያህል ተባርከናል!

በህይወታችን በሙሉ፣ እህት ራዝባንድ እና እኔ በተለያዩ ቤተክርስቲያን እና በተለያዩ ሙያዊ ስራዎች ላይ ተጉዘናል። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያሉ እያንዳንዱን አይነት አደረጃጀት አይቻለሁ፤ በራሻ ውስጥ የሚገኝ የመልከጸዲቅ ካህናት ቁጥር በአንድ እጅ የሚቆጠርበት፤ አዲስና እያደገ ያለ በአፍሪካ ውስጥ የሚገኝ አጥቢያ ሊቀ ካህናት እና ሽማግሌዎች በአንድ ክፍል የሚሰበሰቡበት ምክንያቱም የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች አጠቃላይ ቁጥር ዝቅተኛ ነበር፤ እና የክህነት ሽማግሌዎች ቁጥር ብዛት ምክንያት ወደ ሁለት ቡድን መከፈል ያስፈለገት በደንብ የተቋቋመ አጥቢያ!

በየትኛውም በሄድንበት ቦታ፣ የእግዙአብሔር እጅ ከአገልጋዮቹ ፊት ሲሄድ፣ እናም ሁሉም ልጆቹ እንደ ፍላጎታቸው ይባርካቸው ዘንድ ሕዝቡን እና የወደፊቱን መንገድ ሲያዘጋጅ መስክረናል። እሱ “ከፊታችን እንደሚሄድ እና በቀኛችን እና በግራችን እንደሚሆን እናም መንፈሱ [በልባችን] እንደሚሆን እና [የእርሱ] መላእክት እንደሚከቡን ቃል አልገባልንምን?”2

ሁላችሁንም በማሰብ፣ ይህ መዝሙር ትዝ የኛል “እነሆ! የንጉሳዊ ሠራዊት።”

እነሆ! የንጉሳዊ ሠራዊት፣

በባንዲራ፣ ሰይፍና ጋሻ

ድል ለማድረግ እየገሰገሰ ነው

በህይወት ባለው ታላቁ ጦርነት።

ማዕረጎቹ በወታደሮች የተሞሉ ናቸው፣

ተባባሪ፣ ደፋር እና ብርቱ

መሪያቸውን የሚከተሉ

እናም የደስታቸውን መዝሙር ይዘምሩ።3

ሽማግሌ ክሪስቶፈርሰን በማስታወቂያው ውስጥ በእርግጠኝነት ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች በክህነት ደረጃ የሚገኙ የሊቀ ካህናተ ቡድኖች እና የሽማግሌዎች ቡድን አባላት በአጥቢያ ደረጃ በአንድነት እና ብርቱ የመልከጸዲቅ ክህነት ስልጣን ወንድሞች ሆነው ስለመዋቀራቸው በርካታ መልስ ሰጥቷል።

እነዚህ ማስተካከያዎች የሽማግሌዎች ቡድኖች እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስራቸውን በማጣጣም ለመተግበር ይረዳሉ። ከኤጲስ ቆጶስና ከአጥቢያ መማክርት አባላት ጋር የቡድኑን ቅንጅት ያቃላል። እናም ኤጲስ ቆጶሱ ለካህናት እና ለሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘዳንቶች ተጨማሪ ሃላፊነቶችን እንዲያስተላልፉ ይፈቅዳሉ፣ ይህም ኤጲስ ቆጶስና አማካሪዎቹ በዋና ተግባራቸው ላይ ሊያተኩሩ ይችላሉ ፣ በተለይም በወጣት ሴቶችን እና የአሮናዊ የክህነት ስልጣንን የሚሸከሙ ወጣት ወንዶችን መምራት።

በክርስቲያኗ መዋቅርና አሠራር ላይ ለውጦች መደረጉ ያልተለመደ አይደሉም። በ1883 (እ.አ.አ.)፣ ጌታ ለፕሬዝዳንት ጆን ቴይለር እንዲህ አለ፤ “የቤተክርስቲያኔ እና የክህነት ስልጣን አመራር እና አደረጃጀት በተመለከተ፣ ባስቀመጥኩት መንገድ ለወደፊቱ የቤተክርስቲያኔ እድገት እና ፍጹምነት ለመለወጥ እና ለማሻሻል አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በየጊዜው እገልጽልሃለሁ። ” 4

አሁን፣ ለእናንተ የካህናት አለቆች የምለው ጥቂት ቃላት እንደምንወዳችሁ እወቁ! የሰማይ አባታችን ይወዳችኋል! እናንተ የክህነት ስልጣን ንጉሳዊ ሰራዊት አካል ናችሁ፣ እናም ያለእናንተ መልካምነት፣ አገልግሎት፣ ልምድ፣ እና ጽድቅ ያለንን ስራ ወደፊት ልናንቀሳቅስ አንችልም። ሰዎች ሊቀ ካህን ተብለው የሚጠሩት ሌሎችን ለማስተማርና ለማገልገል ከፍ ካለ እምነታቸውና መልካም ስራቸው ምክንያት እንደሆነ አልማ አስተማረ።5 ያም አጋጣሚ አሁን ከሌሎች ጊዜዎች በሙሉ በላይ ያስፈልጋሉ።

በብዙ አጥቢያዎች ውስጥ፣ ሊቀ ካህናት አሁን በቤተክርስቲያን ሽማግሌ አማካኝነት እንደ ይቡድኑ ፕሬዚዳንት በመሆን የመመራት እድል አላቸው። ሊቀ ካህናቶችን የሚያስተዳደሩ ሽማግሌዎች አሉን፤ በአሁኑ ወቅት ሽማግሌዎች በቅርንጫፍ ውስጥ ሊቀ ካህናት በሚኖሩባቸው በአንዳንድ የአገሪቱ ክልሎች የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቶች ሆነው እያገለገሉ ናቸው እናም የሽማግሌዎች ቡድን የተደራጀ እና ከፍተኛው ሊቀ ካህናት ያሉባቸው ቅርንጫፎች አሉ።

የመልከፀዲቅ የክህነት ተሸካሚዎች እና በአጥቢያ ውስጥ ያሉ ሁሉም አባላት በማስተማር፣ በመማር፣ እና ትከሻ ለትከሻ አብሮ ማገልገል ምን ያህል ታላቅ ደስታ ይሆናል። የትም ቦታ እና በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ፣ የመምራት ወይም የመመራት አዲስ እድሎችን በጸሎት፣ በታማኝነት፣ እና በደስታ እንደ አንድ የክህነት ወንድሞች በህብረት ለማገልገል እንድትቀበሉ እንጋብዛችኋለን።

በቅዱስ ክህነት መዋቅሮች ውስጥ የጌታን ፈቃድ ለመተግበር ወደፊት በምንሄድበት ውቅት፣ ማብራሪያዎችን የሚሹ ተጨማሪ ጉዳዮችን አቀርባለሁ።

በካስማ ሊቀ ካህናቱ ቡድን ውስጥ የሚደረጉት ማስተካከያዎች ምንድን ናቸው? የካስማ ሊቀ ካህን ቡድኖች ባሉበት ይቀጥላሉ የካስማ አመራሮች የካስማው ሊቀ ካህናት መሪ በመሆን አገልግሎታቸውን ይቀጥላሉ። ሆኖም ግን፣ ሽማግሌ ክሪስቶፈርሰን እንደገለጹት፣ የካስማው ሊቀ ካህናት ቡድን አባል የሚያካትቱት በአሁኑ ጊዜ በካስማ አመራር ውስጥ የሚያገለግሉ፣ የአጥቢያ አመራር አባሎች፣ የካስማው ከፍተኛ መማክርት አባላት እና ፓትሪያርኩ ናቸው። የአጥቢያና የካስማ ጸሃፊዎች እና አስፈፃሚ ጸሐፊዎች የካስማው ሊቀ ካህን ቡድን አባል አይሆኑም። ሊቀ ካህናት፣ ፓትርያርክ፣ ከሰባዎቹየሆነ ወይም ሃዋሪያ በአሁኑ ጊዜ እያገለገለ ያለው ሰው በክህነት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ሲፈልግ ከሽማግሌዎች የክህነት ስብሰባ ላይ ይሳተፋል።

በእነዚህ ጥሪዎች ያሉ ወንድሞች ከጥሪያቸው በሚወርዱበት ጊዜ፣ እንደ ሽማግሌዎች የክህነት ቡድን አባል ወደ ቀድሞው አጥቢያቸው ይመለሳሉ።

የካስማው ሊቀ ካህን የክህነት ቡድን ሚና ምንድን ነው? የካስማ አመራሮች ከሊቀ ካህናት መማክርት ቡድን አባላት ጋር በመገናኘት፣ ለመመስከር፣ እና ስልጠና ለመስጠት ይገናኛሉ። በመመሪያ መጽሐፍ ውስጥ እንደተገለጸው መሰረት የካስማ ስብሰባዎች ሁለት ማስተካከያዎችን በማድረግ ይቀጥላሉ፤

አንደኛ፣ አጥቢያዎች እና ካስማዎች የክህነት ስልጣን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባዎችን ከአሁን በኋላ አያደርጉም። ልዩ ትኩረት የሚያስፈልገው የቤተሰብ ጉዳይ ወይም ያልተለመደ የደህንነት ስጋትን የመሳሰሉ ልዩ የድንገተኛ ችግር ሲነሳ፣ በተስፋፋ የኤጲስ ቆጶስ ስብሰባ ውስጥ ሊገለጽ ይችላል። ሌሎች አስቸኳይ ያልሆኑ ጉዳዮች በአጥቢያ መማክርት ስብሰባ ውስጥ ሊቀርቡ ይችላሉ። የካስማ የክህነት ስልጣን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በመባል የሚታወቀው አሁን “ሊቀ መማክርት ስብሰባ” ይባላል።

ሁለተኛ፣ ሁሉም የተሾሙት ሊቀ ካህናቶች የሚገኙበት ዓመታዊ ስብሰባቸውን ከአሁን በኋላ አያደርጉም። ይሁን እንጂ፣ ዛሬ በተዋወቁት የካስማ ፕሬዘዳንቱ የተመሰረተውን የካስማ ሊቀ ካህናት ዓመታዊ ስብሰባ ማድረጉን ይቀጥላል።

አንድ አጥቢያ ከአንድ በላይ የክህነት ሽማግሌዎች ቡድን ሊኖር ይችላል? መልሱ አዎን ነው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል  107፣ ቁትር  89 መንፈስ፣ አንድ አጥቢያ እጅግ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው ተሳታፊ የመልከጸዲቅ የክህነት ተሸካሚዎች ሲኖሩት፣ መሪዎች ከአንድ በላይ የሽማግሌዎች ቡድንን ሊያደራጁ ይችላሉ። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ፣ እያንዳንዱ ቡድን በዕድሜ፣ በተሞክሮ እና በክህነት አገልግሎት ቢሮ እና ጥንካሬ የተመጣጠነ መሆን ይገባዋል።

በነዚህ በመንፈስ በተመሩ የአጥቢያ እና የካስማ አደረጃጀት ወደፊት ከተጓዝን ወደፊት ብዙ በረከቶችን እንደምናይ እመሰክራለሁ። አንዳንድ ምሳሌዎች ላጠቁም።

በኤጲስ ቆጶስ አመራር ስር ብዙ የክህነት ሀብቶች በማዳን ሥራ ላይ ሊረዱ ይችላሉ። ይህም እስራኤላውያንን በሰባሰብ በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራዎች፣ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች እና ግለሰቦች ጋር በመስራት እና ሚስዮኖች ነፍሳትን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያመጡ መርዳትን ያካትታል።

የበላይ አመራር ለይ የነበሩ መሪዎች ልምዳቸውን ከሽማግሌዎች ቡድን ጋር ለማካፈል ሲመለሱ፣ ጠንካራ የቡድኑ አባላት ይፈጠራሉ።

በቡድኑ ውስጥም ብዙ የተለያዩ ስጦታዎች እና አቅም ይኖራል።

በአጥቢያው እና በቡድኖች ውስጥ የጊዜያዊ እና አፋጣኝ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና የተለያዩ የአገልግሎት ሃላፊነቶችን ለማሟላት የበለጠ ተጣጣፊነት እና ተገኝነት ይኖራቸዋል።

አዲስ የክህነት ሽማግሌ እና ልምድ ያለው ሊቀ ካህን ጎን ለጎን በቡድኑ ስብሰባዎች እና ሃላፊነቶች ሲካፈሉ፣ መማማር እና የሙሉ ስምምነት ብዛት ይጨምራል።

ኤጲስ ቆጶሶች እና የቅርንጫፍ ፕሬዘዳንቶች መንጎቻቸውን ለመጠበቅ እና እርዳታ የሚፈልጉትን ለማገልገል ጥሪዎቻቸውን ከፍ እንዲያደርጉ ነጻ ይሆኑ ዘንድ ተስፋ ይደረጋል።

እያንዳንዱ አጥቢያ እና ካስማ የተለያየ እንደሆነ እንረዳለን። እነዚህን ልዩነቶች በመረዳት፣ እነዚህን አጠቃላይ ለውጦችን በፈቃደኝነት ከጉባዬው ቀጥሎ እንደምትከተሉ ተስፋ እናደርጋለን እናደርጋለን። በእግዚአብሔር ነብይ መመሪያ ተሰጥቶናል! ምን አይነት ትልቅ በረከት እና ሀላፊነት ነው። በሙሉ ፅድቅ እና ትጋት እናሟላው!

የክህነት ስልጣን በመለየት እና በመሾም እንደሚመጣ አስታውሱ፣ ነገር ግን እውነተኛው የክህነት ሃይለ፣ ማለትም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ላይ ለመተግበር የሚያስችል ኃይል የሚመጣው በጽድቅ ኑሮ ብቻ ነው።

ጌታ ለዳግም የተመለሰው ነቢይ ለነበረው፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ ሲል አወጀለት፥

“እነሆ፣ እናም አዎ በጎችህን እጠብቃለሁ፣ ሽማግሌዎችንም አስነሳለሁ እናም ወደነሱ እልካለሁ።

“እነሆ፣ ሥራዬን በጊዜው አፋጥናለሁ።”6

በእርግጥም፣ ይህ እግዚአብሔር ሥራውን የሚያፋጥንበት ጊዜ ነው።

እያንዳንዳችንን ከእሱ ፈቃድ ጋር ለመስማማት እና እውነተኛ እና ታማኝ ለሆኑት ቃል የተገባላቸውን ብዙ በረከቶች ለመቀበል እንድንችል ህይወታችንን ለማንጸባረቅ እና ለማሻሻል የተሰጠንን እድል እንጠቀምበት።

ወንድሞች፣ ለዚህ አስደናቂ ሥራ አካል ለመሆን እያደረጋችሁት ስላላችሁት ሁሉ አመሰግናለሁ። በዚህ ታላቅና የተከበረ አላማ ወደ ፊት እንሂድ።

ኦው፣ ጦርነቱ ሲጠናቀቅ፣

ሁከትና ግጭቶች ሲወገዱ፣

ሁሉም በደህንነት ሲሰበሰቡ

በሰላም ሸለቆ ውስጥ፣

ዘላለማዊ ከንጉሱ በፊት፣

ያ ሰፊና ኃያል ህዝብ

ስሙን ለዘላለም ያወድሱታል፣

ይህ ዝማሬያቸው ይሆናል፤

ድል፣ ድል፣

በእርሱ በቤዛችን!

ድል፣ ድል፣

ድል፣ ድል፣ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ ጌታችን!

ድል፣ ድል፣ ድል፣

Tበኢየሱስ ክርስቶስ፣ ጌታችን!7

ዛሬ ጌታ ፍቃዱን በነቢዩ አማካይኝነት በፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን ሲገልጽ ሁላችንም ለመመስከር ቆመናል። እሳቸው በዚህ ምድር ላይ ያሉ የእግዚአብሔር ነቢይ መሆናቸውን እመሰክራለሁ። የእኛ ታላቁ የተዋጀን እና አዳኛችን የሆነው ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነቴን እሰጣለው። ይህ የእሱ ሥራ ነው፤ የእርሱ ፈቃድም ነው፣ ክቡር ምስክሬን የምሰጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።