መንፈስ ቅዱስን እንደ መሪህ አድርገህ ውሰድ
እምነታቸውን በኢየሱስ ክስቶስ ላይ ለሚያደርጉ ሰዎች ምን ዓይነት ሊወዳደር የማይችል ስጦታ ነው! ያም ስጦታ መንፈስ ቅዱስ ነው።
በዚህ በፋሲካ ሰንበት፣ ሃሳቦቻችን ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ እና ለሁሉም አማኞች በክርስቶስ ድል ላይ ተስፋን ወደሰጠው የባዶው መቃብር ይመለሳሉ። ሐዋርያ ጳውሎስ እንዳለው እግዚአብሔር “ኢየሱስን ከሞት እንዳስነሳው እርሱ በእኛ በሚኖረው በመንፈሱ፣ ለሚሞተው ሰውነታችን ሕይወት እንደሚሰጠን” የተናገረውን አምናለሁ።1
ማደስ ማለት ሕይወት መስጠት ማለት ነው። ልክ ክርስቶስ በእርሱ ትንሳኤ ኃይል አማካኝነት ከአካላዊ ሞት በኋላ አካላችንን ወደ ሕይወት መልሶ እንደሚያመጣው ሁሉ፣ እኛንም ሊያስነሳን ወይም በአዳም ውድቀት አማካኝነት ከመጣው ከመንፈሳዊ ሞት ሕያው እንድንሆን ማድረግ ይችላል።2 በመጽሐፈ ሙሴ ውስጥ፣ አዳም በእንደዚህ አይነት መታደስ ውስጥ ማለፉን እናነባለን፥ “አዳም ተጠመቀ፣ እናም የእግዚአብሄር መንፈስ በላዩ ላይ ወረደ፣ ስለዚህም በመንፈስ ተወለደ እና ከውስጡ የታደሰ ሆነ።”3
እምነታቸውን በኢየሱስ ክስቶስ ላይ ለሚያደርጉ ሰዎች ምን ዓይነት ሊወዳደር የማይችል ስጦታ ነው! አዲስ ኪዳን “በክርስቶስ ውስጥ ህይወት”4 ብሎ የሚጠራውን የሚሰጠን ይህም ስጦታ መንፈስ ቅዱስነው። ነገር ግን እንደዚህ አይነት ስጦታዎችን ችላ እንላለንን?
ወንድሞችና እህቶች፣ በሚከተለው አጋጣሚ ውስጥ እንደሚታየው “… መንፈስ ቅዱስ እንደ መሪያችን መሆኑ”5 ለየት ያለ እድል ነው።
በኮሪያ ጦርነት ጊዜ፣ ኢንዛይን ፈራንክ በሌር ጃፓን በሚገኘው ሰራዊት ማመላለሻ ውስጥ አገለገለ።6 መደበኛ የሃይማኖት ተወካይ ሊኖረው መርከቡ ትልቅ አልነበረም፣ ስለሆነም የመርከብ አለቃው ወንድም ብሌር የእምነትና የመርሆ ሰው እንዲሁም በመላው ሰራተኞች የተከበረ እንደሆነ በመገንዘቡ የመርከቡ መደበኛ ያልሆነ የሃይማኖት ተወካይ እንዲሆን ጠየቀው።
ኢንዛየን ብሌር እንዲህ ብሎ ፃፈ፤ “መርከባችን በታላቅ አውሎ ንፋስ ተያዘች። ሞገዱ 14 ሜትር ከፍታ ነበረው። ጥበቃ ላይ ነበርኩኝ --- በዛም ሰዓት ከሶስቱ አንዱ ሞተራችን ስራውን አቆመ እና በመርከቡ መካከላዊ ቦታ ላይ መሰንጠቁ ተነገረን። ሁለት ሞተሮች ነበሩን፣ አንዱ በግማሽ ኃይል ነበር ሲሰራ የነበረው። በጣም በከፋ ችግር ውስጥ ነበርን።”
የመርከቡ አለቃ በሩን ሲያንኳኳ ኢንዛይን ብሌር ጥበቃውን ጨርሶ ወደ አልጋው እየሄደ ነበር። እንዲህም በማለት ጠየቀ፣ “እባክህን ስለዚህ መርከብ ትጸልያለህን?” በእርግጥ ኢንዛይን ብሌር እንዲሁ ለማድረግ ተስማማ።
በዛን ወቅት፣ ኢንዛይን ብሌር “እግዚአብሔር አባት ሆይ፣ እባክህን መርከባችንን ባርካት እንዲሁም ከአደጋ ጠብቀን” ብሎ በመጸለይ ወደ አልጋው መሄድ ይችል ነበር። ነገር ግን፣ በዛን ሰዓት የመርከቧ ደህንነት ለመጠበቅ እንዴት መርዳት እንደሚችል ለማወቅ ጸለየ። ለወንድም ብሌር ጸሎት ምላሽ መንፈስ ቅዱስ ወደ ድልድዩ እንዲሄድ እና ከካፕቴኑ ጋር በመነጋገር የበለጠ እንዲያውቅ አነሳሳው። ካፕቴኑ የቀሩትን ሞተርች በምን ያህል ፍጥነት ማሽከርከር እንዳለበት ለማወቅ እየጣረ እንደነበረ አወቀ። ኢንዛይን ብሌር ለመጸለይ ወደ ክፍሉ ተመለሰ።
እንዲህ በማለት ጸለየ፣ “ሞተሮቹ ያላቸውን ችግር ለመቅረፍ ምን ማድረግ እችላለሁ?”
በምላሹ፣ መንፈስ ቅዱስ በመርከቡ ዙሪያ እንዲሄድና የበለጠ መረጃ እንዲሰበስብ አንሸኳሸኮለት። በድጋሜ ወደ ካፕቴኑ ተመለሶ በመርከቡ ዙሪያ መራመድ ይችል ዘንድ ፍቃድ ጠየቀ። ከዛ፣ የደህንነት ገመድ በወገቡ ላይ በመታጠቅ በወጀቡ ውስጥ ገባ።
በመርከቧ ኋላ በመቆም መርከቧ ከምትፈጥረው ሞገድ ወደ ላይ ስትወጣ ታላላቅ መቅዘፊያዎቹን ተመለከተ። አንዱ ብቻ ነበር በሙሉ አቅም የሚሰራው እናም በፍጥነት ነበር የሚሽከረከረው። ከዚህ ምልከታ በኋላ፣ እንዛይን ብሌር በድጋሜ ጸለየ። የተቀበለው ግልፅ መልስ በስራ ላይ ያለው ሞተር በከፍተኛ ጫና ላይ እንዳለና ትንሽ መቀዝቀዝ እንዳለበት ነበር። ስለዚህ ወደ ካፕቴኑ በመመለስ መፍትሄውን አቀረበ። የመርከብ አለቃው በመገረም የመርከቡ ኢንጂነሮች መዓበሉን ለማሸነፍ ተቃራኒ የሆነ መፍትሄ በማቅረብ ደህና የሆነውን ሞተር ፍጥነት እንዲጨምሩ ነገረው። ይሁን እንጂ፣ ካፕቴኑ የኢንዛይን ብሌርን ሃሳብ ተቀብሎ ሞተሩን አቀዘቀዘው። በንጋታው መርከቧ በተረጋጋ ውኃች ላይ በደህንነት ተገኘች።
ከሁለት ሰዓታት በኋላ፣ ደህና የሆነው ሞተር ስራውን በአጠቃላይ አቆመ። በቀሪው ሞተር ግማሽ ኃይል መርከቧ ወደ ወደቡ አመራች።
የመርከብ አለቃው ለኢንዛይን ብሌር እንዲህ አለው፣ “ያንን ሞተር ባናቀዘቅዘው ኖር፣ በመአበሉ ውስጥ እናጣው ነበር።”
ካለዛ ሞተር መርከቧን ማሽከርከር ከቶ አይቻልም ነበር። መርከቧ ትገለበጥ እና ትሰምጥ ነበር። ካፕቴኑ ወጣት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሰራተኛን አመሰገነው እናም የኢንዛይን ብሌርን መንፈስዊ ምሪት መከተሉ መርከቧንና ሰራተኞቹን ማዳኑን እንዳመነ ነገረው።
አሁን፣ ይህ ታሪክ በጣም ድራማዊ ነው። እንደዚህ አይነት አስፈሪ ሁኔታ ሊገጥመን ባይችልም፣ ይህ ታሪክ እንዴት መንፈሳዊ ምሪቶችን በበለጠ ሁኔታ መቀበል እንደምንችል ጠቃሚ መረጃዎችን ይዟል።
መጀመሪያ፣ ራዕይን በተመለከተ፣ መቀበያችንን በተገቢ ሁኔታ ቅኝቱን ወደ ሰማይ ማድረግ ይኖርብናል። ኢንዛይን ብሌር ንፁ እና እምት የሞላበት ሕይወት ነበር የሚኖረው። ታዛዥ ባይሆን ኖሮ ለመርከቧ ደህንነት ለመጸለይ እና ለየት ያለ ምሪት ለመቀበል መንፈሳዊ መተማመን አይኖረውም ነበር። እያንዳንዳችን በእርሱ ለመመራት ሕይወታችንን ከእግዚአብሔር ትዕዛዛት ጋር ለማስተካከል ሙከራውን ማድረግ ይኖርብናል።
አንዳንድ ጊዜ ብቁ ባለመሆናችን የሰማይን ምልክት ልንሰማ አንችልም። በድጋሚ ንፁህ የሆነ ንግግርን ለማድረግ ንስሃ እና ታዛዥነት መንገዶች ናቸው። የብሉይ ኪዳን ንስሃ የሚለው ቃል ትርጉም “መታጠፍ” ወይም “ዞሮ መመለስ” ማለት ነው።7 ከእግዚአብሔር የራቃችሁ ሲመስላችሁ፣ በመዞርና ወደ አዳኙ በመመልከት ከሃጢያት ለመመለስ መወሰን አለባችሁ። እናም እጆቹ ተዘርግተው እናንተን እየጠበቀ ታገኙታላችሁ። እናንተን ለመምራት በጣም ጉጉ ነው፣ እናም ያንን ምሪት በድጋሚ ለመቀበል አንድ ጸሎት ነው የሚቀራችሁ።8
ሁለተኛ፣ ኢንዛይን ብሌር ችግሩን እንዲቀርፍለት ጌታን አልጠየቀም። የመምፍትሄው ክፍል ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀ። እኛም እንደዚህ እንጠይቅ ይሆናል፣ “ጌታ የመምፍትሄው ክፍል ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለኝ?” በጸሎት ችግሮቻችንን ከመዘርዘር እና ጌታ መፍትሄ እንዲሰጠን ከመጠየቅ፣ የጌታን እርዳታ የምናገኝበት መንገድን እፈለግ እናም መንፈስ በሚመራበት ለመስራት ወስኑ።
በዚህ ኤንሳይን የብሌር ታሪክ ውስጥ ሶስተኛ ጠቃሚ ትምህርት አለ። ከዚህ ቀደም ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ እርሱ ከመንፈስ ምሪቶችን ባይቀበል ኖሮ በእንደዚህ ዓይነት በተረጋጋ ማረጋገጫ ይጸልይ ነበርን? የአውሎ ንፋስ መድረስ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች በማንሳት አራግፈን ምን ማድረግ እንዳለብን የማሰቢያ ጊዜ አይሰጠንም። ይህ ወጣት የበሐር ኃይል ግልፅ በሆነ ሁኔታ ከዚ ቀደም ሚስዮን በነበረበት ወቅት የተማረውን ደጋግሞ የተጠቀመበትን ስልት እየተከተለ ነበር። በአስፈሪ ወጀብ ውስጥ ድምፁ የተሳሳተ እንዳይሆን ለማወቅ መንፈስ ቅዱስን በተረጋጋ ውኃ ላይ እንደ ምሪታችን አድርገን ልንወስደው ይገባናል።
አንዳንዶች ከመንፈስ የቀን ተቀን ምሪትን መጠበቅ እንደሌለብን ሊደመድሙ ይችላሉ ምክንያቱም ሰነፍ አገልጋዮች ካልሆንን በስተቀር፣ “እግዚአብሔር በሁሉም ነገሮች ላይ ማዘዝ የለበትም።”9 ይህ ጥቅስ ጆሴፍ ስሚዝ የጉዞ ዕቅድ ራዕይ እንዲቀበልላቸው ለፈለጉ ለተወሰኑ የቀድሞ ሚስዮኖች ተሰጥቶ ነበር። በሚቀጥለውም ቁጥር ጌታ ወደ ሚስዮን እንዲመጡ ነገራቸው “እርስ በራሳቸው እና ከእኔም ጋር እንደሚመክሩት።”10
እነዚህ ሚስዮኖች ስለጉዞአቸው እቅድ ልዩ ራዕይ ፈለጉ። የራሳቸውን መመሪያ በግል ጉዳያቸው መፈለግ እንዳለባቸው አልተማሩም ነበር። ጌታ ይህንን አመለካከታቸውን ስንፈት ብሎ ጠራው። የቀድሞ የቤተክርስቲያን አባሎች ራዕይ ለራሳቸው እንዴት መቀበል እንዳለባቸው መማር ባለመቻላቸው አደጋ ውስጥ በመሆናቸው እውነተኛ ነብይ ስላላቸው ደስተኛ ሆነው ይሆናል። በመንፈስ ራስን መቻል ማለት የጌታን ድምፅ በመንፈሱ ከማካኝነት ለግል ሕይወት መስማት መቻል ማለት ነው።
አልማ ልጁን እንዲህ ብሎ መከረው፣“በሁሉም ነገርህ ከጌታ ጋር ተማከር።”11 “በመንፈስ መኖር” ብለን በምንጠራው በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ መኖር ከፍተኛ ዕድል ነው። የመረጋጋትና የእርግጠኝነትን ስሜት እንዲሁም ፍቅር፣ ደስታ እና ሰላም የመሳሰሉትን የመንፈስ ፍሬዎችን ያመጣል።12
የኢንዛይን ብሌር ራዕይን የመቀበል ችሎታ እሱንና የስራ አጋሮቹን ከከባድ ሞገድ አዳነ። በዛሬ ቀን ሌላ ዓይነት ከባድ ሞገዶች አሉ። የመጽሐፈ ሞርሞን የሕይወት ዛፍ ፍሬ13 ምሳሌ በዚህ ዓለም ውስጥ መንፈሳዊ ደህንነትን እንዴት ማግኘት እንደምንችል ኃይለኛ የሆነ ምስል ያቀርባል። ይህ ሕልም ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በመንገድ ላይ እየተራመዱ ላሉ ለቤተክርስቲያን አባሎች መንፈሳዊ ውድቀትን ስለሚያመጣ ድንገተኛ የጨለማ ጭጋግ ይናገራል።14
ይህን ምስል በማሰላሰል፣ በአዕምሮዬ ዓይን በብዙ የሚጠጉ ህዝቦች ያንን መንገድ ሲጓዙ፣ ሌሎች የብረት ዘንጉን በእጃቸው አጥብቀው ይዘው ሲጓዙ፣ ነገር ግን ሌሎች ደግሞ ከፊታቸው ያሉትን ሰዎች እግር እያዩ ሲጓዙ እመለከታለው። ይህ የመጨረሻው ስልት ትንሽ የሆነ ሃሳብን ወይም ሙከራን ይጠይቃል። ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትንና የሚያስቡትን ነገር ለማድረግና ለማሰብ ቀላል ነው። ይህ ስራ በጸሀይ ጊዜ ቀላል ነው። ነገር ግን የማታለል ሞገዶች እና የሃሰት ጭጋጎች ካለማስጠንቀቂያ ይነሳሉ። በእነዚህ ሰዓት፣ ከመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ጋር እራስን ማለማመድ የመንፈሳዊ ሕይወት ወይም ሞት ጉዳይ ነው።
የኔፊ ኃይለኛ ቃልኪዳን እንዲህ ይላል፣ “የእግዚአብሔርን ቃል ለሚሰሙ ሁሉ፣ …እናም እርሱን አጥብቆ የያዘ …በፍጹም አይጠፋም፤ ፈተናዎችና የጠላት ክፉ ፍላፃ እነሱን በማሳወር አሸንፈው ወይም ወደ ጥፋት ለመውሰድ አይችሉም።”15
በመንገድ ላይ ከፊታችሁ ያሉትን ሰዎች እግር በማየት መከተል በቂ አይደለም። ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን እና የሚያስቡትን ማድረግና ማሰብ አንችልም። የሚመራ ኑሮ መኖር አለብን። እያንዳንዳችን እጃችንን በብረት ዘንጉ ላይ ማድረግ አለብን። ከዛ “እጃችንን ይዞ እንደሚመራን እና ለጸሎታችን መልስ እንደሚሰጠን” በማወቅ ወደ ጌታ ትሁት በሆነ መተማመን መሄድ እንችላለን፣ 16 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።