2010–2019 (እ.አ.አ)
ማገልገል
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


2:3

ማገልገል

አዲስ፣ ቅዱስ የሆነ ሌሎችን የመንከባከብ እና የማገልገል ዘዴዎችን እንጠቀማለን።

ሽማግሌ ጎንግ እና ሽማግሌ ሶሬስ፣ ከልብ ለመጣው የእምነት መግለጫዎቻችሁ እናመሰግናለን። ለእናንተ እና ለውድ ባለቤቶቻችሁ ታላቅ ምስጋና አለን።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ አባላቶቻችን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት፣ በልዩም እግዚአብሔርን እና ጎረቤቶቻችንን ማፍቀር የሆኑትን እነዚያን ሁለት ታላቅ ትእዛዛት፣1 እንዲከተሉ እንዴት ለመርዳት እንደምንችል መመሪያ ከጌታ ለማግኘት ሁል ጊዜም እንፈልጋለን።

ለብዙ ወራት በአዳኝ መንገድ የህዝቦቻችንን መንፈሳዊ እና ጊዜአዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ለማገልገል የምንችችልበት የተሻለ መንገድ እንፈልጋለን።

የቤት ለቤት ጉብኝት እና የሴቶች የቤት ለቢት ትምህርት እንደምናውቃቸው ለማቆም ውሳኔ ላይ ደርሰናል። በእነርሱ ምትክ፣ አዲስ፣ ቅዱስ የሆነ ሌሎችን የመንከባከብ እና የማገልገል ዘዴዎችን እንጠቀማለን። ለእነዚህ ጥረቶች “ማገልገል”ብለን እንጠራቸዋለን።

ውጤታማ የአገልግሎት ጥረቶች ውስጥ ባላቸው የእህቶ ስጦታዎች እና ለመመዛዘን በማይቻለው የክህነት ሀይል የሚከናወኑ ናቸው። ሁላችንም እንደዚህ አይነት ጥበቃዎች ከጠላት ማታለል ያስፈልጉናል።

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ዘንጎ አባል ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት እህት ጂን ቢ. ቢንገም የተመደቡት የክህነት ወንድሞች እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች እናም ወጣት ሴቶች አሁን በአለም አቀፍ ያሉትን አባላት በማገልገል እና በመጠበቅ እንደሚሰሩ ይገልጻሉ።

ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንግጎ የእነርሱን መልእክቶች በመደገፍ በአንድ ድምፅ ይናገራሉ። በምስጋና እና በጸሎት ይህን አዲስ የቤተክርስቲያኗን የታሪክ ምእራፍ እንከፍታለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።