ትንሽ እና ቀላል ነገሮች
ትንሽ የሚመስሉት ነገሮች ታላቅ ነገሮችን እንደሚያስፈጽሙ በሙሉ እና ብዙ ጊዜያት እንድናስታውስ መደረግ አለበት።
፩.
ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ እንደ እናንተ፣ እኔም በሚያነሳሱት መዝሙሮች እና መልእክቶች እናም አብረን በምናሳልፍበት በዚህ ጊዜ ስሜት በጥልቅ ተነክቻለሁ። እንደ ጌታ መሳሪያነት፣ ለዚህ አብረን በነበረን ጊዜአችን ለሰጡን ጥካሬ ለወንድሞቻች እና ለእህቶቻችን ምስጋና ሳቀርብ ለእናንተም እንደምናገር እርግጠኛ ነኝ።
ለዚህ የጌታ አዳማጭ በትንሳኤ ሰንበት ለመናገር በመቻሌ ምስጋና አለኝ። ዛሬ ከሌሎች ክርስቲያናት ጋር የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤ እናከብራለን። ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የእምነታችን ምሶሶ ነው።
በመፅሐፍ ቅዱስ እና በመፅሐፈ ሞርሞን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤን ታሪክ ስለምናምን፣ በምድር ላይ ለኖሩት ለሁሉም ሟች ሰዎች እንዲህ አይነት ከሞት መነሳት እንደሚመጣ የሚያስተምሩትን ብዙ ቅዱሳት መጻህፍትን እናምናለን። ያም ትንሳኤ ሐዋሪያው ጴጥሮስ “ህያው ተስፋ” (1 ጴጥሮስ 1፥3) ብሎ የሚጠራውን ይሰጠናል። ያም ህያው ተስፋ፣ ሞት የማንነታችችን መጨረሻ ሳይሆን ነገር ግን ይህም የሰማይ አባታችን ለልጆቹ ደህነት ያለው ምህረት የተሞላበት የመዳን እቅድ ውስጥ አስፈላጊ ደረጃ ነው። ያም እቅድ ከሟችነት ወደ አለሟችነት መቀየር ያስፈልገዋል። ለዚህ ቅያሬ ዋና ክፍል ቢኖር የሞት መጥለቅ እና በዚህ በትንሳኤ ሰንበት የምናከብረው በጌታችን እና አዳኛችን ትንሳኤ ምክንያት የሚመጣው ግርማዊው ጠዋት ነው።
፪.
ቃላቱ በእላይዛ አር. ስኖው የተጻፈው ታላቅ መዝሙር ውስጥ፣ እንዲህ እንዘምራለን፥
በዚያ መለኮታዊ ንድፍ እና ስምምነት፣ በስብሰባዎች፣ በተጨማሪም በዚህ ጉባኤ፣ እርስ በራስ ለማስተማር እና ለማበረታታት እንሰበሰባለን።
በዚህ ጠዋት በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የተመዘገበው፣ አልማ ለልጁ ሔላማን ያስተማረውን እንደ አርዕሴ ለመጠቀም ስሜት ነበረኝ፥ “በትንሽና በቀላል ነገሮች ታላቅ ነገሮች ተፈፅመዋል።”(አልማ 37፥6)።
ብዙ ትንሽ እና ቀላል ነገሮችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ ተምረናል። እነዚህ ትንሽ የሚመስሉት ነገሮች ታላቅ ነገሮችን እንደሚያስፈጽሙ በሙሉ እና ብዙ ጊዜያት እንድናስታውስ መደረግ አለበት። በዚህ ርዕስ ላይ በአጠቃላይ ባለስልጣናት እና በሌሎች የተከበሩ አስተማሪዎች ብዙ ንግግሮች ተሰጥቷል። ይህ ርዕስ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ይህን እንደገና እንዳቀርብ ስሜት አለኝ።
የትንሽ እና ቀላል ነገሮች በጊዜ ምን ሀይል እንደሚኖራቸው በየጠዋት ጉዞዬ ባየሁት ነገር እንዳስታውስ ተደርጌአለሁ። ያነሳሁት ፎቶ ይህ ነው። ወፍራሙ እና ጠንካራው የሲሚንቶ የእግረኛ መሄጃ ተሰንጥቆ ነበር። ይህ በታላቅና ሀይል የተገፋበት ውጤት ነበርን? አይደለም፣ ይህ ስንጣቄ የደረሰው በቀስታ፣ በትንች በሚያድግ በቅርብ በተገኘ ዛፍ ስር ምክንያት ነው። ይህም በሌላ መንገድ ላይ ያየሁት ምሳሌ ነው።
እነዚህን ከባድ የሲሚንቶ እግረኛ መሄጃዎቸ የሰነጠቀው የሚገፋው ሀይል በየቀኑ ወይም በየወሩ ለመመዘን በጣም ትንሽ ነበር፣ ነገር ግን በጊዜ ሂደት የነበረው ውጤት በጣም ሀይለኛ ነው።
እንዲሁም በቅዱሳት መጻህፍት እና በነቢያት የምንማራቸው ትንሽ እና ቀላል ነገሮች ከጊዜ በኋላ ሀይለኛ ውጤት አላቸው። በየቀኑ ህይወታችን ውስጥ እንድንጨምራቸው የተማርናቸውን የቅዱሳት መጻህፍት ጥናቶች አስቡባቸው። ወይም ታማኝ የኋኛው ቀን ቅዱሳን በየጊዜው በግል ጸሎት እና በቤተሰብ ጸሎት የመንበርከክ ልምምድ የሚከተሉበትን አስቡባቸው። ወጣቶች ለሰሚነሪ ወይም ወጣት ጎልማሶች ለኢንስቲትዊት የሚሄዱበትን አስቡበት። እነዚህ እያንዳንዱ ልምምዶች ትንሽ እና ቀላል ነገሮች ቢመሥሉም፣ ከጊዜ በኋላ ሀይለኛ የመንፈስ ክፍ መደረግ እና እድገት ውጤታቸው ነው። ይህም፣ ፕሬዘደንት አይሪንግ እንደገለጹት፣ የሚሆነው እነዚህ እያንዳንዱ ትንሽ እና ቀላል ነገሮች፣ የሚያብራራ እና ወደ እውነት የሚመራ መስካሪን፣ የመንፈስ ቅዱስን ጓደኝነት ስለሚጋብዙ ነው።
ሌላ የመንፈስ ከፍ መደረግ እና እድገት ምንጭ ቢኖር፣ ትንሽ መስሎ በሚታይ መተላለፍ፣ ቀጣይነት ያለው ንስሀ መግባት ነው። በመንፈስ የተነሳሳ የግል መመዘኛችን እንዴት በአጭር እንደወደቅን እና እንዴት ለመሻሻል እንደምንችል ለማየት ሊረዱን ይችላሉ። እንደዚህ አይነት ንስሀ መግባት በየሳምንቱ ከምንወስደው የቅዱስ ቁርባን በፊት ሊሆን ይገባዋል። በዚህ የንስሀ መግባት ሂደት እንድናስብባቸው አንዳንድ ርዕሶች “ምንም መልካም አድርገሀል?” በሚለው መዝሙር በሀሳብ ቀርበዋል።
ዛሬ በአለም ውስጥ ምን መልካም አድርጌአለሁ?
እርዳታ የሚያስፈልገውን እርዳታ ሰጥቻለሁን?
የከፋውን አስደስቻለሁን እና አንድ ሰውን ደስ እንዲለው አድርጌአልሁን?
ካላደርኩም፣ ወድቄአለሁና።
የሌላ ሰው ሸከም ቀለል ብሏል ዛሬ
ለመካፈል ፈቃደኛ ስለሆንኩኝ?
የታመመውና የደከመው በመንገዳቸው ተረድተዋልን?
እርዳታ ሲፈልጉ በዚያ እገኛለሁን?2
በእርግጥም እነዚህ ትንሽ ነገሮች ናቸው፣ ነገር ግን እነርሱ አልማ ለልጁ ለሔላማን ላስተማረው ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው፥ “እናም ጌታ እግዚአብሔር ታላቁንና ዘለዓለማዊ አላማውን ለማምጣት በእነዚህ መንገዶች ይሰራል፤ እናም በጣም ቀላል በሆነ መንገድ ጌታ … የብዙ ሰዎችን ነፍስ ወደ ደህንነት ያመጣል” (አልማ 37፥7)።
ፕሬዘደንት ስቲቨን ሲ. ዊልራይት ስለአለማ ትምህርት ይህን የሚያነሳሳ መግለጫ በብሪገም ያንግ ዩንቨርስቲ–ሀዋዪ ለነበሩት አዳማጮች ሰጡ፥ “አልማ በጌታ በእርሱ ስናምን እና ትንሽ እና ቀላል ነገሮች ምክሩን ስንከተል እርሱ የሚከተለው ንድፍ፣ እኛን በየቀኑ በትንሽ ታዕምራት መባረክ፣ እና ከጊዜም በኋላ፣ በድንቅ ስራ መባረክ እንደሆነ ለልጁ አረጋግጧል።”3
ሽማግሌ ሀወርድ ደብሊው. ሀንተር እንዳስተማሩት “በብዛት ይህ … አለም በብዙ ጊዜ ታላው ነው ከሚላቸው ነገሮች ጋር ሲመዛዘን፣ በሌሎች ህይወቶች ላይ መልካም ውጤት ያለው ተራ ስራ ነው።”4
የዚህ አይነት መርሆ የሚያሳምን አለማዊ ትምህርትም ከድሮ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ከነበሩት ዳን ኮትስም መጥቷል፣ እንዲህ ጻፉ፥ “ህይወትን፣ እንዲሁም አገርን፣ ለሚለውጥ አንድ ታላቅ ውሳኔ ብቸኛ ዝግጅት ቢኖር፣ በነኛ መቶዎች እና በሺዎች ግማሽ በደንብ ያልታሰበበት፣ ራሱን የሚተረጉም፣ ታላቅ የማይመስሉ ውሳኔዎችን በግል በማድረግ ብቻ ነው።”5
እነዚያ “ታላቅ የማይመስሉ” የግል ውሳኔዎችም ጊዜአችንን እንዴት እንደምንጠቀምባቸው፣ በቴሌቪዥን እና በኢንተርኔት ምን እንደምንመለከት፣ ምን እንደምናነብ፣ በስራና በቤት ራሳችንን በምን ስዕሎች እና ሙዚቃዎች እንደምንከብ፣ ለመዝናናት ምንን እንደምንሻ፣ እና ታማኝ እና እውነተኛ የመሆን የልብ ውሳኔአችንን እንዴት እንደምንጠቀምባቸው ያካትታል። ሌላ ትንሽ እና ቀላል ነገር የሚመስለውም በግል ግንኙነቶቻችን ትሁት እና ደስተኛ መሆን ነው።
ማንኛውም እነዚህ የሚፈለጉት ትንሽ እና ቀላል ነገሮች ሁልጊዜ እና በየጊዜው የምንለማመድባቸው ካልሆኑ በስተቀር ወደ ከፍተኛ ነገሮች ከፍ ሊያደርጉን አይችሉም። ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ እንዳሉት፥ “ህይወቶቻችን አብረው ሲመቱ፣ እና የወንድ እና ሴት ህይወትን በሙሉ ሲያዳምሩ ታላቅ ከሚሆኑ ትንሽ እና ቀላል ጉዳዮች የተሰሩ ናቸው።”6
ሁልጊዜ የምንቋቋማቸው ካልሆንን በስተቀር የእኛን ዋጋ በሚቀንሱ በመተላለፊያ ተጽዕኖ እና በባህል መሰባበር ተከብበናል። ወደ ዘለአለም አላማችን ለመድረስ፣ ሁልጊዜው ወደፊት መግፋት አልብን። በዚህ የምንሰራ እና ወደፊት አብረን የምንገፋ ቡድን አባል መሆን ይረዳል። ያን ምሳሌ በተጨማሪም ለመጠቀም፣ በባህል የሚገፉን በጣም ጠንካራ ሆነው ወደፊት መሄድን ብናቆም፣ ወደፊት ለመግፋት በመሞከር ካልቀጠልን መሄዳችን ወደማይቀረው ወደማንፈልገው ቦታ ተጎትተን እንወሰዳለን።
ታላቅ ውጤታ ያለውን ትንሽ የሚመስለውን ድርጊት ከገለጸ በኋላ፣ ኔፊ እንዲህ ጻፈ፣ “በዚህም እኛ በቀላል ዘዴ ጌታ ትላልቅ ነገሮችን ለማምጣት እንደሚችል እናያለን” (1 ኔፊ 16፥29)። ብሉይ ኪዳን ስለዚህ የማይረሳ ምሳሌ አካትቷል፥ በዚያም እስራኤላውያን በመርዛማ እባቦች እንደሚሰቃዩ እናነባለን። ብዙ ሰዎች ተነድፈው ሞቱ (ዘኁልቁ 21፥6 ተመልከቱ)። ሙሴ ለእርዳታ ሲጸልይ፣ “የናስ እባብ ሰርቶ፣ በአላማ ላይ እንዲሰቅል” በመንፈስ ተነሳሳ። ከዚያም፣ “እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ” (ቁጥር 9)። እንደዚህ ያለ ትንሽ ነገር ለዚህ ታዕምራታዊ ውጤት! ግን፣ ኔፊ ለመፈወስ ቀላል መንገድ ቢያዘጋጅላቸውም በጌታ ላይ ያምጹ ለነበሩት ይህን ምሳሌ በማስተማር ገለጸ፣ “እናም በድርጊቱ ቀላልነት የተነሳ ብዙዎች የጠፉ ነበሩ” (1 ኔፊ 17፥41)።
ያም ምሳሌ እና ትምህርት የመንገዱ ተራነትና የታዘዘው ስራ ቀላልነት ይህ ጻድቃዊ ፍላጎታችንን ለማግኘት አስፈላጊ አይደለም ማለት አይደለም።
በዚህም አይንት፣ ትንሽ የሆኑ ያለመታዘዝ ስራ ወይም ትንሽ ጻድቅ የሆነ ልምምድን አለመከተል እንድናስወግደው ማስጠንቀቂያ ወደተሰጠን ውጤት ጎትቶ ይወስደናል። የጥበብ ቃል ለዚህ ምሳሌ ይሰጣል። የአንድ ሲጋራ ወይም የአንድ መጠጥ ወይም አንድ የአደንዛዥ እጽ መውሰድ ውጤት ለመመዘን አይቻልም። ነገር ግን ከጊዜ በኋላ፣ ውጤቱ ሀይለኛ ነው እናም መልሶ ለመቀየር አይቻልም። በዛፍ ስር በቀስታ መወጠር ምክንያት የተሰነጠቀውን የእግረንኛ መሄጃን አስታውሱ። አንድ ነገር እርግጥ ነው፣ ሰውነታችንን እንደሚጎዳው አደንዛዥ እጽ ወይም ሀሳቦታችንን የሚያዋርደው የወሲብ ድርጊት የሚያሳየው ሱስ የሚያመጣ ምንም ነገርን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ካልወሰድን በሙሉ ለመወገድ የሚቻል ነው።
ከብዙ አመታት በፊት፣ ፕሬዘደንት ኤም. ራስል ባለርድ ለአጠቃላይ ጉባኤ አዳማጮች “ትንሽ እና ቀላል ነገሮች በሰው ደህንነት ላይ መጥፎ እና የሚያጠፋ ውጤት እንዴት እንዳለው” ገልጸዋል። እንዲህ አስተማሩ፥ “ክርን እና በመጨረሻም ገመድን እንደሚሰራ ደካማ ድር፣ እነዚህ ትትንሽ ነገሮች ተደባብረው ለመስበር ጠንካራ የሆኑ ይሆናሉ። ትንሽ እና ቀላል ነገሮች በመንፈሳዊነት ግንባታ ውስጥ ሀይል እንደሚኖራቸው ሁልጊዜም ማወቅ ይገባናል” አሉ። በተመሳሳይ ሰአት፣ ሰይጣን ትንሽ እና ቀላል ነገሮችን ወደ ስቃይ እና ወደ ተስፋ መቁረጥ ውስቶ ለመምራት እንደሚጠቀምም ማወቅ አለብን።”7
ፕሬዘደንት ዊልራይትም እንደዚህ አይነት ማስጠንቀቂያ በቢዋዩ–አይደሆ ሰጥተው ነበር። “ትንሽ እና ቀላል ነገሮችን ባለማድረግ ነው እምነት የሚነቃነቀው፣ ታዕምራት የሚቆሙት፣ እና ከዚያም የእግዚአብሔር መንግስትን መፈለግ በአለማዊ ፍላጎቶች እና አለማዊ ጉጉቶች ሲተኩ፣ ወደ ጌታ እና ወደ መንግስቱ የመሄድ ጉዞ በመጀመሪያ ይቆማል ከዚያም ይፈርሳል።”8
መንፈሳዊ እድገታችንን ከሚያጠፉት ከሚከማቹት መጥፎ ውጤቶች ራሳችንን ለመከላከል፣ የትንሽ እና ቀላል ነገሮች መንፈሳዊ ንድፍን መከተል ያስፈልገናል። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር በቢዋዩ ሴቶች ጉባኤ ላይ እንደገለጹት፥ “ስለዚህ መንፈሳዊ ንድፍ … ውሀን በቀስታ በአፈር ላይ ጠብ ጠብ ከማድረግ ዜዴ ለመማር እንችላለን፣” ይህንንም ብዙ ውሀ ወደማያስፈልግበት ከማጥለቅለቅ ወይም ከመርጨት ጋር በማነጻጸር ነው።
እንዲህም አብራሩ፥ “ጠብ ጠብ ብሎ የሚፈሰው ውሀ ወደ ምድር ይሰምጣል እናም ብዙ ውሀ በአፈሩ ውስጥ እንዲገኝና በዚያም አትክልቶች በደንብ እንዲያድጉ ያደርጋል። እንደዚህም፣ እናንተ እና እኔ መንፈሳዊ ምግብ በዘላቂ የምናተኩት እና የምንከስት ከሆንን፣ ከዚያም የወንጌል ርስ በነፍሳችን በጥልቅ ይሰመጣል፣ በፅኑነት ይመሰረታል እና ይተከላል፣ እናም አስደናቂና ጣፋጭ ፍሬዎችን ይሰራል።
“ታላቅ ነገሮችን የሚያመጣው የትንሽ እና ቀላል ነገሮች መንፈሳዊ ንድፍ ፍጹምነትን እና አለመነቃነቅን ይሰራል፣ መለኮታዊነትን ዝልቅ ያደርጋል፣ እናም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌሉ በፍጹም ወደመቀየር ያመጣል።”9
ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ይህን መሰረታዊ መርሆ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ አሁን በተጨመሩት ቃላት በኩል አስተምሯል፥ “ማንም ሰው እነዚህን እንደትንሽ ነገሮች አይቁጠራቸው፤ ቅዱሳኑን በሚመለከት፣ በእነዚህ ላይ የሚመኩ፣ በወደፊት የሚኖሩ ብዙዎች አሉና” (ት. እና ቃ. 123፥15)።
በምዙሪ ቤተክርስቲያኗን ለመመስረት ከተደረገው ሙከራ ጋር በማያያዝም፣ ጌታ እንዲህ ስለ ትእግስት መክሯል “ነገር ግን ሁሉም ነገሮች በጊዜአቸው ይከናወኑ” (ት. እና ቃ. 64፥32)። ከዚያም ይህን ታላቅ ትምህርት ሰጠ፥ “ስለዚህ መልካም በማድረግ ላይ አትዛሉ፣ የታላቁን ስራ መሰረት እየጣላችሁ ነውና። እናም ከትንንሾቹ ነገሮች ታላቅ የሆነው ይወጣል።” (ት. እና ቃ. 64፥33)።
ሁላችንም በፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “በቃል ኪዳን መንገድ”10 ወደፊት እንድንገፋ ያበረታቱንን ለመከተል ፍላጎት እንዳለን አምናለሁ። ይህን ለማድረግ ያለን የልብ ውሳኔ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እና በቤተክርስቲያኑ መሪዎች የምንማራቸውን “ትንሽ ነገሮች” በዝልቅ በመከተል ይጠናከራል። ስለእርሱ እመሰክራልሁ እናም የእርሱን በረከቶች በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ለመቆየት ለሚፈልጉት ሁሉ እሰጣለሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።