2010–2019 (እ.አ.አ)
የሽማግሌዎች ሸንጎ
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


2:3

የሽማግሌዎች ሸንጎ

በአጥቢያ ውስጥ አንድ የመልከ ጼዴክ ክህነት ሸንጎ መኖሩ የክህነት ተሸካሚዎች የደህንነትን ስራ በሚያከናውኑባቸው በሁሉም መንገዶች አንድ ያደርጋቸዋል።

በዚህ በመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያኗ ከተደራጀች ብዙ ጊዜ ሳያልፍ፣ ጌታ በራዕይ እንዲህ ገለጸ፣“እናም ቤተክርስቲያኔን እንዴት ማስተዳደር እንዳለባችሁ እንድታውቁ እና ነገሮችን ሁሉ በፊቴ መልካም ታደርጉ ዘንድ በእምነታችሁ ጸሎት ህጌን ትቀበላላችሁ።”1 ይህ መርሆ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስቲያኗ ትከተለዋለች—እና ያም ቃል ኪዳን በጌታ ተከብሯል። ከጊዜ ወደ ጊዜ የክህነት ሀላፊነት እና ቡድኖች በጊዜአችን ከተመሰረቱበት ከነቢዩ ጆዜፍ ስሚዝ ጀምሮ፣ የክህነት ድርጅት እና አገልግሎት ንድፍ ተገልጾ ነበር። በፕሬዘደንቶች ብሪገም ያንግ፣ ጆን ቴይለር፣ ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል፣ እና በሌሎች አመራር ስር የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎን፣ ሰባዎችን፣ ሊቀ ካህናትን፣ እና በመልከ ጼዴቅ እና በአሮናዊ ክህነት ሌሎች ሀላፊነቶችንና ሸንጎዎችን በሚመለከት ታላቅ ማስተካከያዎች በራዕይ ተቀብለውና በተግባር ውሎ ነበር።2 አሁን፣ ከጥንስ ጊዜ በፊር ባቀረቡት በዚህ ታሪካዊ ንግግር፣ ፕሬዘደንት ራስል  ኤም. ኔልሰን ተጨማሪ በጣም አስፈላጊ ለውጥን አስተማወቁ።

የእርሳቸውን ንግግር በመጥቀስም፥ “በዚህ ምሽት፣ የጌታን ስራ በውጤታማነት ለማከናወን የመልከ ጼዴቅ ክህት ሸንጎአችንን በታላቅ ማደራጀታችንን እናስተዋውቃለን። በአጥቢያ ውስጥ፣ የሊቀ ካህን ቡድን እና የሽማግሌዎች ሸንጎ ተቀላቅለው አንድ የሽማግሌዎች ሸንጎ ይሰራሉ … [እናም] [የካስማ ሊቀ ካህን] ቡድን አሁን ባሉት በክህነት ጥሪዎች ላይ የተመሰረተ ይሆናል።”

ፕሬዘደንት ኔልሰን ይህን ጨመሩ፥

“እነዚህ ለውጦች ለብዙ ወራት ሲጠኑባቸው ነበሩ። ለአባላቶቻችን የምንንከባከብበት መንገድን ማሻሻል በአስቸኳይ እንደሚያስፈልግ ተሰምቶናል። … ይህን በደንብ ለማድረግ፣ ጌታ ለቅዱሳኑ ለሚፈልገው የፍቅር አገልግሎት እና ድገፋ ዘንድ የክህነት ቡድኖቻችንን ታላቅ መመሪያዎች ለመስጠት እነርሱን ማጠናከር ያስፈልገናል።

“እነዚህ ማስተካከያዎች በጌታ የተነሳሱኡ እንደሆኑ እመሰክራለሁ። እነዚህን በተግባር ስናውል፣ ከዚህ በፊር ከነበርነው በላይ ውጤታማ እንሆናለን።”3

በቀዳሚ መሪነት ምሪት፣ ሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ እና እኔ ለሚኖሯችሁ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የምናስብባቸው አንዳንድ ተጨማሪ ዝርዝር እንሰጣለን።

የሽማግሌዎች እና የሊቀ ካህናት ቡድኖች።

መጀመሪያ፣ በድጋም ለመግለፅ፣ ለዎርድ ሊቀ ካህናት ቡድን እና ለሽማግሌዎች ሸንጎ ምን ለውጦች አሉ? በዎርድ ውስጥ፣ የዎርድ ሽማግሌዎች ሸንጎ እና የሊቀ ካህናት ቡድን አሁን በአንድ የመልከ ጼዲቅ ክህነት ሸንጎ አንድ አመራር እያላቸው ይቀላቀላሉ። ይህ ሸንጎ፣ በቁጥር እና በአንድነት አድጎ፣ “የሽማግሌዎች ሸንጎ” ተብሎ ይጠራል። የሊቀ ካህናት ቡድን ይፈርሳል። የሽማግሌዎች ሸንጎ በተጨማሪም ሁሉን ሽማግሌዎች እና ሽማግሌ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቁ እና አሁን በኤጲስ ቆጶስ አመራር፣ በካስማ አመራር፣ ወይም በሊቀ ካህን ሸንጎ፣ ወይም እንደ ፓትሪያርክ የማያገለግሎትን የያዘ ነው። የካስማ የሊቀ ካህናት ሸንጎም በኤጲስ ቆጶስ አመራር፣ በካስማ አመራር፣ ወይም በሊቀ ካህን ሸንጎ፣ ወይም እንደ ፓትሪያርክ የተቀናበሩ ናቸው

የሽማግሌዎች ሸንጎ አመራር።.

የሽማግሌዎች ሸንጎ አመራር እንዴት ነው የሚደራጀው? የካስማ አመራር አሁን ያሉትን የሊቀ ካህናት ቡድን መሪዎች እና የሽማግሌዎች ቡድን አመራር ከጥሪያቸው ይለቃሉ እናም አዲስ የሽማግሌዎች ሸንጎ አመራር እና አማካሪዎችን በእያንዳንዱ ዎርድ ይጠራሉ። በአዲሱ የሽማግሌዎች ሸንጎ አመራር ውስጥ፣ የተለያዩ እድሜዎች እና አጋጣሚዎች ያሏቸው፣ ሽማግሌዎችና ሊቀ ካህናት አብረው በአንድ አመራር ያገለግላሉ። ሽማግሌ ወይም ሊቀ ካህን እንደ ሸንጎው ፕሬዘደንት ወይም እንደ አማካሪዎች በአመራር ውስጥ ለማገልገል ይችላሉ። ይህም የሽማግሌዎች ሸንጎ በሊቀ ካህናት መወረር አይደለም። ሽማግሌዎች እና ሊቀ ካህናት በዘንጎ አመራር እና በሸንጎ አገልግሎት በተለያዩ ሀላፊነቶች አብረው ይሰራሉ። እነዚህ የሸንጎ ለውጦች በተቻለበት ወዲያው በተግባር መዋል ይገባቸዋል።

በሽማግሊዎች ሸንጎ ውስጥ ያሉት የክህነት ሀላፊነቶች።

የሸንጎ መሰረት መስተካከሉ በሸንጎ አባላት የተያዙትን የክህነት ሀላፊነቶች ይቀይራልን? አይደለም፣ ይህ ስራ ማንኛውም የሸንጎ አባል በፊት የተሾመበትን የክህነት ሀላፊነት መልሶ አይወስድም። እንደምታውቁት፣ አንድ ሰው በህይወቱ በተለያዩ የክህነት ሀላፊነቶች ሊሾም ይችላል፣ እናም አዲሱን ሲቀበል በፊት የተሾመበትን አያጣም ወይም አይወሰድበትም። ለምሳሌ ሰው ሊቀ ካህን እንደ ፓትሪያርክ ወይም ኤጲስ ቆጶስ ሲያገለግል፣ በአንዳንድ ሁኔታዎች የክህነት ተሸካሚ ከአንድ በላይ ሀላፊነት ቢያገለግልም፣ በሁሉም የክህነት ሀለፊነቶች በአንድ ጊዜ አያገለግልም ይሆናል። ኤጴ ቆጶሶች እና ሰባዎች፣ ለምሳሌ፣ ከጥሪያቸው ከተለቀቁ በኋላ በነዚያ ሀላፊነቶች አያገለግሉም። ስለዚህ፣ ሰው ምንም ሌላ ሀላፊነት ወይም ሀላፊነቶች ቢኖረውም፣ እንደ ሽማግሌ ሸንጎ አባል እያለ፣ እንደ ሽማግሌ ያገለግላል።

ከብዙ አመቶች በፊት፣ ፕሬዘደንት ቦይድ ኬ. ፓከር እንዳስመለከቱት “ክህነት ከማንኛውም ሀላፊነቶች በላይ ታላቅ ነው። … ክህነት የሚከፋፈል አይደለም። ሽማግሌ እንደ ሐዋሪያ ያህል ክህነትን የሚዘ ነው። (ት. እና ቃ. 20፥38።) ሰው [ክህነት በእርሱ ላይ ሲያርፍ]፣ ሁሉንም ይቀበላል። ይህም ቢሆን፣ በክህነት ውስጥ ሀላፊነቶች አሉ—የስልጣን እና ሀላፊነት ክፍፍል። … አንዳንዴ አንድ ሀላፊነት ከሌላው “ከፍተኛ” ወይም “አነስተኛ” ነው ተብሎ ይናገርበታል። ‘ከፍተኛ’ ወይም ‘አነስተኛ’ በማለት ስይሆን በመልከ ጼዴቅ ክህነት ውስጥ ያሉ ሀላፊነቶች የተለያዩ የአገልግሎት ክፍሎችን የሚወክሉ ናቸው።”4 በመልከ ጼዴቅ ክህነት ሀላፊነት ውስጥ አንዱ ከሌለኛው በላይ “ከፍተኛ” ነው ተብሎ እንደማይነገርበት ተስፋ አለኝ።

ሽማግሌዎች በካስማ አመራር፣ በሊቀ ካህን ሸንጎ፣ ወይም በኤጲስ ቆጶስ አመራር ውስጥ እንዲያገለግሉ—ወይም በሌላ ጊዜ በጸሎት አስተሳሰብ እና በመንፈስ መነሳሳት በካስማ ፕሬዘደንት በሚወሰንበት—ለመሾም ይቀጥላሉ። በካስማ አመራር፣ በሊቀ ካህን ሸንጎ፣ ወይም በኤጲስ ቆጶስ አመራር የሚያገለግሉበት ጊዜ ሲያልቅ፣ ሊቀ ካህናት ወደ ዎርዳቸው የሽማግሌዎች ሸንጎ ይመለሳሉ።

ለሽማግሌዎች ሸንጎ ፕሬዘደንት የሚሰጥ መመሪያ።

የሽማግሌዎች ሸንጎ ፕሬዘደንትን ስራ ማን ይመራል? የካስማ ፕሬዘደንት በካስማው ውስት የሚገኑትን የመልከ ጼዴቅ ክህነት ይመራል። ስለዚህ፣ የሽማግሌዎች ሸንጎ ፕሬዘደንት፣ ከካስማ አመራር እና በሊቀ ካህን ሸንጎ በኩል ማሰልጠኛና መመሪያዎችን ለሚሰጠው፣ ለካስማ ፕሬዘደንት ሀላፊነትን አለው። ኤጲስ ቆጶስ፣ እንደ ዎርድ መሪ ሊቀ ካህን፣ ደግሞም በየጊዜው ከሽማግሌ ሸንጎ ፕሬዘደንት ጋር ይገናኛል። ኤጲስ ቆጶስ ከእርሱ ጋር ይማከራል እናም ከዎርድ ድርጅቶች ሁሉ ጋር በስምምት በመስራት እንዴት በተሻለ መንገድ የዎርድ አባላትን ለማገልገል እና ለመባረክ፣ እንደሚቻል ትክክለኛ መመሪያ ይሰጠዋል።5

የእነዚህ ለውጦች አላማ።

በመልከ ጼዴቅ ክህነት ሸንጎ ለውጥ ምን አላማዎች አሉት? አንድ የመልከጼዴቅ ክህነት ሸንጎ በዎድ ውስጥ መገኘቱ የክህነት ተሸካሚዎች የደህንነት ስራን ሁሉ፣ በተጨማሪምከዚህ በፊር በሊቀ ካህናት ቡድኖች ያቀናጁት የነበረው የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራን ለማከናወን አንድ ያደርጋቸዋል። ሁሉም እድሜዎች እና ልምምዶች ያሏቸው የሸንጎ አባላት ከእርስ በራስ አስተያየቶች እና አጋጣሚዎች እናም የተለያዩ እድሜዎች ካሏቸው ጥቅም እንዲያገኙ ይረዷቸዋል። ልምምድ ያላቸው ክህነት ተሸካሚዎችም ሌሎችን፣ በተጨማሪም ሽማግሌ ለመሆን የሚችሉትን፣ አድስ አባላትን፣ ወጣት ጎልማሳዎችን፣ እና ወደቤተክርስቲያን ተሳታፊነት የሚመለሱትን እንዲያማክሩ ተጨማሪ እድል ይሰጣቸዋል። ወደፊት የሽማግሌዎች ሸንጎዎች ተጨማሪ አስፈላጊ ስራዎች ስለሚያከናውኑት ሳስብበት እንዴት ያህል ደስ እንደሚለኝ በብቁ ለመግለጽ አልችልም። በእነዚህ ሸንጎዎች ውስጥ የሚገኙ ጥበብ፣ አጋጣሚ፣ ችሎታ፣ እና ጥንካሬ በቤተክርስቲያኗ በሙሉ የሚገኝን አዲስ ቀን እና አዲስ መሰረት አስቀድሞ ያሳያል።

ከሀያ አመት በፊት በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ፣ በሰባዎች አባል ሽማግሌ ቯን ጄ. ፈዘርስቶን ተነግሮ የነበረውን ታሪክ የነገርኩበት፣ አሁንም በዚህ መደገም እንደሚያስፈልገው ይሰማኛል።

በ1918 (እ.አ.አ) ወንድም ጆርጅ ጎትስ በሊሀይ፣ ዩታ ውስጥ ስኳር ድንች የሚያሳድጉ ገበሬ ነበሩ። ክረምት ከጊዜ በፊት መጣ እና የስኳር ድንች አትክልቶችን አቀዘቀዘ። ለጅርጅ እና ለወጣት ልጁ ፍራንሲስ፣ አዝመራው አስቸጋሪና በፍጥነት የሚከናወን አልነበረም። በዚያም ጊዜ፣ ኢንፍሉዌንዛ በሽታ በብዛት ነበረ። ይህም አሰቃቂ በሽታም የጆርጅን ልጅ ቻርልስ እና ሶስቱን የቻርልስ ልጆች—ሁለት ሴቶች እና አንድ ወንድ—ሞተው ነበር። በስድስት ቀን ውስጥ፣ የሚያዝነው ጆርጅ ጎትስ ከኦግደን፣ ዩታ አስካሬኖችን ለመቀበር ሶስት የተለያዩ ጉዞዎች አደረገ። በዚህ መጥፎ ጊዜ መጨረሻ ላይ፣ ጆርጅ እና ፍራንሲስ ጋሪያቸውን አዘጋጁ እና ወደ ስኳር ድንች እርሻ ቦታ ተመለሰ።

“‘[ወደዚያ በሚጓዝበት] በሽኳር ድንች የተሞሉ ብዙ ጋሪዎች ወደ ፋብሪካ እየተወሰዱ እና ጋሪዎችን በጎረቤት ገረቤዎች ሲነዱ ተመለከተ። እርሱን ሲያልፉ፣ እያንዳንዱ የጋሪ ነጂ ሰላም ይሉት ነበር፥ ‘ጤና ይስጥልኝ፣ አጎት ጆርጅ፣’ ‘ይቅርታ፣ ጆርጅ፣’ ‘መጥፎ እድል ነው፣ ጆርጅ፣’ ‘ብዙ ጓደኞች ነው ያሉህ፣ ጆርጅ።’

“በመጨረሻው ጋሪ ላይ … ጆሴፍ ሮልፍ ነበር። ደስተኛ ሰላምታ በመስጠት እጁናውለበለበና እንዲህ አለ፥ ‘ያም ሁሉም ናቸው፣ አጎት ጆርጅ።’

“[ወንድም ጎተስ] ወደ ፍራንሲስ ዞር ብሎ እንዲህ አለ፥ ‘ይህ የእኛ ሁሉ ቢሆን ምኞቴ ነው።’

“ወደ እርሻቸው መግቢያ ሲደርሱ፣ ፍራንሲስ ከጋሪው ዘለለና አባቱ ወደ እርሻው እንዲነዳ ዘንድ በሩን ከፈተ። [ጆርጅ] ገባ፣ ፈረሶቹን አስቆማቸው … እናም እርሻውን ተመለከተ። … በእርሻው በሙሉ ምንም የስኳር ድንች አልነበረም። በዚያም ጊዜ ጃስፐር ሮል ያለው ምን እንደሆነ ተረዳ። ‘ያም ሁሉም ናቸው፣ አጎት ጆርጅ።’

“[ጆርጅ ከጋሪው ወረደ፣ የሚያፈቅረውን በእጅ ሙሉ የሚሆን አፈር አነሳ፣ ከዛም … የስኳር ድንች ቅጠል፣ እናም ለትንሽ ጊዜ፣ እይኑን ለማመን እንደማይችል ያህል፣ እነዚህን የስራው ውጤቶችን ተመለከተ።

“ከዚያም [እርሱ] በተሰበሰቡት የስኳር ድንሽ ቅጠሎች ላይ ተቀመጠ … በስድስ ቀናትት ውስጥ አራት የሚያፈቅራቸውን ለመቅበር ወደ ቤት ያመጣ፤ የአስከሬን ሳንጣ የሰራ፣ መቃብር የቆፈረ፣ እና በመቀበሪያው ልብስም የረዳ ሰው … ይህ በምንም የማይደናቀፈው፣ የማይሸማቀቅ፣ ወይም በዚህ አሰቃይ ችግር ምንም ያልተነቃነቀው አስደናቂ ሰው፣ በስኳር ድንች ቅጠሎች ላይ ተቀመጠና እንደ ትንች ልጅ አለቀሰ።

“ከዚያምም ተነሳ፣ አይኑን ዓበሰ፣ … ወደ ሰማይ ተመለከተ፣ እናም እንዲህ አለ፥ ‘አባት ሆይ፣ ለዎርዳችን ሽማግሌዎች አመሰግናለሁ።’” 6

አዎን፣ ለክህነት ወንዶች እና ለግለሰቦች እና ቤተሰቦች እናም ፅዮንን በመመስረት ወደፊት ለሚሰጡት አገልግሎቶች እግዚአብሔር ይመስገን።

ቀዳሚ አመራር፣ የአስራ ኁለት ሐዋሪያት ሸንጎ፣ እና የሰባዎች አመራር እነዚህን ለውጦች ለረጅም ጊዜ አስበውበት እበር። በብዙ ጸሎቶች፣ የክህነት ሸንጎን የቅዱሳት መጻህፍት መሰረቶችን በጥቃቄ በማጥናት፣ እና ይህ የጌታ ፍላጎት እንደሆነ በማረጋገጥ፣ በአንድ ድምፅ በእውነት ዳግም መመለስን ለመክፈት ተጨማሪ እርምጃ በሚሆነው ወደፊት እንገፋለን። ስለእርሱ፣ ስለክህነቱ፣ እና በዚህ ክህነት የእናንተን ሹመት ስመሰክር፣ የጌታ አመርር ግልፅነው፣ እናም በዚህም እደሰታለሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 41፥3

  2. See, for example, William G. Hartley, “The Priesthood Reorganization of 1877: Brigham Young’s Last Achievement,” in My Fellow Servants: Essays on the History of the Priesthood (2010), 227–64; “To the Seventies,” in James R. Clark, comp., Messages of the First Presidency of The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints (1965), 352–54; Hartley, “The Seventies in the 1880s: Revelations and Reorganizing, in My Fellow Servants, 265–300; Edward L. Kimball, Lengthen Your Stride: The Presidency of Spencer W. Kimball (2005), 254–58; Susan Easton Black, “Early Quorums of the Seventies,” in David J. Whittaker and Arnold K. Garr, eds., A Firm Foundation: Church Organization and Administration (2011), 139–60; Richard O. Cowan, “The Seventies’ Role in the Worldwide Church Administration,” in A Firm Foundation, 573–93.

  3. ራስል ኤም. ሌልሰን፣ “ማስተዋወቂያ ንግግሮች፣” Liahona፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 54።

  4. ቦይድ ኬ. ፓከር፣ “What Every Elder Should Know—and Every Sister as Well: A Primer on Principles of Priesthood Government,” Tambuli, Nov. 1994, 17, 19.

  5. See Handbook 2: Administering the Church (2010), 7.3.1 ተመልከቱ።

  6. ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን፣ “The Priesthood Quorum,” Liahona, Jan. 1999; see also Vaughn J. Featherstone, “Now Abideth Faith, Hope, and Charity,” Ensign, July 1973, 36–37.