“ከእነርሱ ጋር ሁኑ እናም አጽናኑአቸው።”
ዛሬ ጸሎታችን እያንዳንዱ ወንድ እና ሴት ከዚህ አጠቃላይ ጉባኤ ስንመለስ እርስ በርሳችን ከልብ ለመቆርቆር ጥልቅ የሆነ ውሳኔን እንድንወስን ነው።
ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን ያለውን በአጭር በመጥቀስ፣ በህይወት በደንብ የሚታወሱት ጊዜዎች የራዕይ ፍጥነት የሚሰሙን ጊዜ ነው።1 ፕሬዘደንት ኔልሰን፣ ከነዚህ ተጨማሪ “ፍጥነቶችን” በዚህ ሳምንት ለመቀበል የምንችል አይመስለንም። አንዳንዶቻችን ደካማ ልቦች አሉን። ነገር ግን ይህን ሳስብበት፣ እርስዎ ያንንም ሊረዱት ይችላሉ። ምን አይነት ነቢይ!
በፕሬዘደንት ኔልሰን በትላንትና ምሽት እና በዚህ ጠዋት ባደረጉት አስገራሚ አዋጅ እና ምስክሮች መንፈስ፣ እነዚህ ለውጦች ይህችን ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያው ጊዜ የሚመራው ራዕይ ምሳሌ እንደሆነ እመሰክራለሁ። ጌታ ስራውን በዚህ ጊዜ እያፋጠነ እንደሆነ ተጨማሪ መረጃዎች ናቸው።2
ስለእነዚህ ጉዳዮች ተጨማሪ መረጃዎችን ለመማር፣ የዚህ ጉባኤ ስብሰባ ሲፈጸም፣ ኢሜል አድራሻ ላሉን ለእያንዳንዶቹ የቤተክርስቲያኗ አባላት ከቀዳሚ አመራር ደብዳቤ ይደርሳቸዋል። የሰባት ገጽ የጥያቄ እና መልሶች መረጃ ለሁሉም ክህነት እና ደጋፊ መሪዎች ይላካል። በመጨረሻም፣ እነዚህ መረጃዎች ministering.lds.org ላይ ወዲያው ይገኛሉ። “ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ።”3
አሁን ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ለእኔ እና ለእህት ጂን ቢ. ቢንገው ወደተሰጠው አስገራሚ ሀላፊነት እንመለስ።. ወንድሞች እና እህቶች፣ በግልጽነት የሸንጎዎች እና የደጋፊዎች ሥራ ተቋም በሆነ መልኩ እየበሰለ ሲሄድ፣ እኛም እንደግለሰብ መብሰል አለብን። በአካላዊው አገልግሎቱ ማጠቃለያ ላይ በአዳኝ የተናገራቸውን ከልብ የመነጨ ደቀመዝሙርነት፣ ከማንኛውም የሜካኒካዊ፣ ተግባራት በላይ ከፍ ያለ መሆን አለብን። ገና የዋህ እና ግራ የተጋቡትን ትንሽ የተከታዮች ስብስብ ጥሎ ለመሄድ ሲዘጋጅ፣ በስራዎች የተሞሉ ሪፖርቶችን እንዲሞሉ እና የደርዘን አስተዳደራዊ እርምጃዎችን አልዘረዘረም። አይደለም፣ እርሱ ተግባራቸውን በአንድ ዋና ትዕዛዝ ጠቅለል አድርጎ አቅርቧል። “እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። “… እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”4
ወደዚህ የወንጌል ሕይወት የበለጠ እንድንጠጋ ጥረት ለማድረግ፣ አዲሱ የክህነት እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አገልገሎት ፅንሰ-ሀሳብ የሚከተሉትን ክፍሎች ያካትታል፣ ከነዚህም መካከል ይህ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እጅግ በጣም ጥሩ ስኬት ተገኝቶበታል።5
-
ካሁን በኋላ የቤት ለቤት ትምህርት እና የጉብኝት ትምህርት የሚሉትን ቃላት አንጠቀምም። ይህ የሚሆነው በከፊል የአገልግሎታችን ጥረት ከቤት ውጪ ስለሚሆን እና በከፊል ምክኒያቱም ግንኙነታችን በተዘጋጀ ትምህርት ብቻ የማይገደብ ስላልሆነ ነው፣ ነገር ግን ካስፈለገ ትምህርት ካስፈለገ ማካፈል ይቻላል። የዚህ ሰዎችን የማገልገል ዋና አላማ፣ በአልማ ቀናት እንደነበሩት ሰዎች “በህዝባቸው ላይ ጠባቂ እንዲሆኑ እና … ከጽድቅ ጋር የተያያዙ ነገሮችን እንዲመግቡ” ነው።6
-
በተቻለ መጠን ቤቶችን መጎብኘታችንን እንቀጥላለን፣ ነገር ግን እንደ ትልቅ ቁጥር፣ ረጅም ርቀት፣ የግል ደህንነት፣ እና ሌሎች አስቸጋሪ ሁኔታዎች በየወሩ ወደ እያንዳንዱ ቤት ጉብኝት ለማድረግ ያስቸግራል። ከዓመታት በፊት የመጀመሪያ አመራር እንደመከሩት፣ የተቻላችሁን ያህል ጥረት አድርጉ።7 የመደበኛ ጉብኝት ለማድረግ ካላችሁ እቅድ በተጨማሪ፣ በስልክ ጥሪ፣ በጽሁፍ ማስታወሻዎች፣ በቴክስት፣ በኢሜል፣ በቪዲዮ ውይይቶች፣ በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ውይይቶች፣ በጋራ አገልግሎቶች ፔሮጀክቶች፣ በማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እና በብዛት እየተስፋፋ ካለው በዘመናዊ የማህበራዊ ማህደረ መረጃ ያ ቀን መደገፍ ይችላል። ሆኖም ግን፣ ይህ ሰፋ ያለ የመገናኛ መንገዶች የሚከተለውን በመኪና ተለጣፊ ወረቀት ላይ በቅርቡ ያየሁትን የይቅርታ ቃላት አያካትትም። “የመኪና ጥሩንባዬን ከነፋኁ የቤት ለቤት ትምህርትን ተምረሃል” ይላል። እባካችሁ፣ እባካችሁ፣ ወንድሞች (እህቶች በዚህ ጥፋተኞች አይሆኑም፣ ስለወንድሞች ነው የምናገረው)፣ ከእነዚህ ለውጦች ጋር ተጨማሪ እንክብካቤ እና ሀሳቦች እንጂ ታናሾች አንፈልግም።
-
በዚህ አዲሱ፣ የበለጠ በወንጌል ላይ የተመሠረተ የአስተሳሰብ ጽንሰ-ሀሳብ፣ በሪፖርቱ ውስጥ ምን እንደሚቆጠር መደናገጥ እንደጀመራችሁ ይሰማኛል። መልካም እንግዲ፣ ተረጋጉ፣ ምክንያቱም ምንም ሪፖርት የለም፤ ቢያንስ ቢያንስ በ31ኛው ቀን “በጥርሴ ቆዳ በር ላይ ደረስኩኝ የሚል” ሪፓርት አይነት አይደለም። በዚህም መንገድ እየበሰልን ነው። የሚቀርበው ብቸኛ ሪፖርት ቢኖር በአጥቢያ ውስጥ ከአገልግሎት ሰጪ ጓደኞች ጋር የተደረጉ ቃለመጠይቆች ቁጥር ነው። ይህም ቀላል ቢዝመስልም፣ ጓደኞቼ፣ እነዚያ የቃል ጥያቄዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው። ያለነዚያ መረጃዎች ኤጲስ ቆጶስ የህዝቡን መንፈሳዊ እና ጊዜአዊ ሁኔታን ለማወቅ የሚፈልግበትን መረጃ ለማግኘት አይችልም። አስታውሱ፥ የሚያገለግሉ ወንድሞች ኤጲስ ቆጶስ አመራርን እና የሽማግሌዎ ሸንጎ አመራርን የሚወክሉ ናቸው። የኤጲስ ቆጶስ እና የሸንጎ ፕሬዘደንት ቁልፎች ከዚህ የአገልግሎት ሀሳብ በላይ የሚሄድ ነው።
-
ይህ ሀተታ ከዚህ በፊት ካስገባችሁት ምንም ነገር ሁሉ የተለየ ስለሆነ፣ እኛ በቤተክርስቲያኗ ዋና ቢሮ እንዴት ወይም የት ወይም መቼ ከሰዎቻችሁ ጋር እንደምትገናኙ ለማወቅ እንደማንፈልድ ላረጋግጥላችሁ፤ እናንተ ይህን ማድረጋችሁን እና በዚህና በብዙ መንገዶች እንደባረካችኋቸው ማወቅን ብቻ ነው የምንፈልገው።
ወንድምች እና እህቶች፣ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ንጹህ ሃይማኖትን ለማንፀባረቅ የሚያስችል ከላይ የተሰጠ እድል አለን፣ ለመበለቶችና አባት ለሌላቸው ልጆች ለማገልገል፣8—“አንዳችሁ የአንዳችሁን ሸክም ቀላል እንዲሆኑ ዘንድ ለመሸከም ፈቃደኞች በመሆን”9 የተጋቡ እና በብቸኝነት ላሉ፣ ለጠንካሮች እና ተስፋ ለቆረጡ፣ የተጨቆኑ እና ለንቁዎች፣ ለደስተኞች እና አዛኝ ለሆኑ፣ምክንያቱም የጓደኛማማነት ሞቃት እጅን መሰማት እና የጽኑ እምነት አዋጅን ሁላችንም እና እያንዳንዳችን መስማት አለብን። ሆኖም ግን፣ ፕረኢዘደንት ኔልሰን እንዳሉት፣ ይህን ደፋር፣ አዲስ እና ቅዱስ መስሪያ መንገድ እርስ በርሳችን ለመንከባከብ እንደ ግብዣ ካላየን፣ አዲስ ስም፣ አዲስ አመቺነት፣ እና ያነሱ ሪፖርቶች በአገልግሎታችን ውስጥ አንድም ለውጥ አያመጡም። መንፈሳዊ ዓይኖቻችንን በፍቅር እና ባለማቀፋዊነት ህጎች ላይ ለመኖር ከፍ ስናደርግ፣ ለብዙ አመታት ለዚያ ትውሌድ መንገድ ላዘጋጁ ትውልዶች ክብር እንሰጣለን። በቅርብ ጊዜ የነበረን ይህንን የመሰለን መሰጠት የሚያሳይ ምሳሌን ህዝቦች የጌታን ትእዛዝ የበለጠ የሚረዱት10 ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ጋር “አብሮ ስለመሆን እና ስለማጠናከር” ከሆነ ነው።
ባለፈው ጥር 14፣ እሁድ 11 ሰአት ጥቂት እንዳለፈ፣ ብሬት እና ክሪስቲን ሃምበሊን የተባሉት ወጣት ጓደኞቼ፣ ብረት በኤጲስ ቆጶስ አመራር ውስጥ የአገልግሎት ቀን በኋላ እና ክሪስቲን አምስት ልጆቻቸውን በትጋት ከተንከባከበች በኋላ በቴምፔ አሪዞና ውስጥ በሚገኘው ቤታቸው እየተወያዩ ነበር።
ክሪስቲን በካንሰር ነቀርሳ ባለፈው አመት በውጤታማነት የተረፋችው በድንገት ምልሽ ሳትሰጥ ወደቀች። የ 911 የስልክ ጥሪ እሷን ለመመለስ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጥሩ የአስቸኳይ ቡድን ሰዎችን አመጣ። ብሬት በመማጸን ሲጸልይ እና ሲለምን፣ በፍጥነት ሁለት የስልክ ጥሪዎችን አደረገ፤ አንዱ ለእናቱ ልጆቹን እንድትንከባከብ እንድትረዳ ለመጠየቅ ሌላውን ደግሞ ኤድወን ፖተር ለተባለው የቤት ለቤት አስተማሪው አደረገ። የሁለተኛው ንግግር ሙሉ በሙሉ እንደሚከተለው ነበር፤
ኤድዊን፣ የደዋይ ማንነትን በማየት እንዲህ አለ፣ “ታዲያስ፣ ብሬት፣ እንደምን ነህ?”
ብሬት በመኦህ የመለሰውም፣ “በዚህ አፈልግሀለሁ—አሁን!”
ብሬት መቁጠር ከሚችለው ደቂቃዎች ባነሰ፣ የክህነት አጋሩ፣ ልጆቹን በማገዝ እና ባለቤቱን ከያዘው አምቡላንስ ከኋላ በመከተል ወንድም ሃምብሊን ይዞ ወደ ሆስፒታል ሄደ። ዓይኖቿን ከዘጋች ከ 40 ደቂቃዎች ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሐኪሞቹ ክሪስቲን መሞቷን ተናገሩ።
ብሬት ሲያነባ፣ ኤድዊን በእቅፉ ውስጥ ያዘውና ለረጅም ጊዜ ከእርሱ ጋር አለቀሰ። ከዛም ብሬትን ከሌሎች የቤተሰቡ አባላት ጋር እንዲያዝን በመተው፣ ኤድዊን ምን እንደተከሰተ ለመንገር ወደ ኤጲስ ቆጶሱ ቤት ሄደ። አስደናቂው ኤጲስ ቆጶሱ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ሲያመራ፣ ኤድዊን ወደ ሃምቡሊን ቤት ሄደ። እርሱ እና ባለቤቱ፣ ሻርለት፣ በፍጥነት መጥተው፣ ከ12 እስከ 3 አመት ከሆናቸው ከአምስት እናት ከሌላቸው ከሀምብሊን ልጆች ጋር ይጫወቱ ነበር። እነርሱን የምሽት ምግብ መገቡ፣ የሙዚቃ ዝግጅትን አቀረቡ፣ እናም ለመኝታ አዘጋጇቸው።
ብሬት በኋላ ላይ እንዲህ አለኝ፤ ”የዚህ ታሪክ አስደናቂው ነገር ኤድዊን በጠራሁት ጊዜ መምጣቱ አይደለም። በድንገተኛ ግዜ፣ ለማገዝ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ሁልጊዜም አሉ። አይደለም፣ ግን የታሪኩ አስገራሚው ክፍል በመጀመሪያ ያሰብኩት እርሱን መሆኑ ነው። በአካባቢው ሌሎች ሰዎች ነበሩ። ክርስቲን ከሦስት ማይሎች ባነሰ ርቀት የሚኖሩ ወንድሞች እና እህቶች አላት። ከሁሉም በላይ የሆነ፣ ግሩም የሆነ ኤጲስ ቆጶስ አለን። ነገር ግን በኤድዊንና እኔ ጋር ያለው ግንኙነት ጠንካራ በመሆኑ እርዳታ በሚያስፈልገኝ ጊዜ በቅጽበት እርሱን ለመጥራት ተሰማኝ። ቤተክርስቲያኗ ሁለተኛውን ትዕዛዝ በተሻለ እንድንኖር ለመርዳት፣ ከወዳሞቻችን እና ከእህቶቻችን ጋር ወደ እግዚአብሔር ለመቀራረብ የሚያግዙንን ትዕዛዝ በተሻለ መንገድ እንድንኖር ታደርገናለች።”11
ኤድዊን ፖተር ስለዚህ ተሞክሮ እንዲህ ሲል ተናገረ “ሽማግሌ ሆላንድ፣ በዚህ ሁሉ ውስጥ የሚገርመው ብሬት፣ እኔ የነሱ የቤት አስተማሪ ከሆንኩ ረጅም ጊዜ በላይ የቤተሰባችን አስተማሪ ነበር። በዚያው ጊዜ ውስጥ፣ ከተመደበበት ሃላፊነት ይበልጥ እኛን እንደ ጓደኛ መቶ ጎብኝቷል። አንድ ንቁ እና ተሳታፊ የክህነት ተሸካሚ ምን መሆን እንዳለበት የሚያሳይ ታላቅ ምሳሌ ነው። ባለቤቴ፣ ልጆቻችን እና እኔ በእያንዳንዱ ወር መጨረሻ መልዕክት እንዲልክልን በግዴታ የመጣ መስሎ አይታየንም። እኛን ለመባረክ በዚህ ዓለም ውስጥ ማንኛውንም ነገር የሚያደርግ በመንገዱ ጫፍ ላይ የሚኖረው ጓደኛችን እንደሆነ ነው የምናስበው። የእርዳታ እዳውን ትንሽ ብድር እንኳ ብከፍለው ደስ ይለኛል።”12
ወንድሞች እና እህቶች፣ በታማኝነት በታሪክ ዘመቻችን በዚህ መንገድ የወደደን እና ያገለገለን እያንዳንዱን የአካባቢ አስተማሪን እና የአጥቢያ አስተማሪን እና የቤት ለቤት አስተማሪ እና የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎችን ከእናንተ ጋር ሰላምታዬን እሰነዝራለሁ። ዛሬ የምናቀርበው ጸሎት ሁሉም ወንድ እና ሴት፣ እናም በእድሜ የገፉ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች፣ ይህንን አጠቃላይ ጉባኤ ጨርሰን ስንሄድ፣ በጥልቅ ሁኔታ ከልብ በሆነ ስሜት፣ በክርስቶስ ንጹህ ፍቅር ብቻ በመነጨ እርስ በእርሳችን ለመንከባከብ እንድንችል የልብ ውሳኔን እንድንወስድ ነው። የእኛ ግድብ እና ድካማ ነው ብለን ብናስብባቸውም—ሁላችንም ፈተናዎች አሉን—ይህም ቢሆን፣ ጎን በጎን በጌታ የአትክልት ስፍራ እንስራ፣ 13 ጸሎቶችን በመመለስ፣ መፅናኛን በመስጠት፣ እምባዎችን በማድረቅ፣ እና የተዳከሙትን ጉልበቶች በማጠናከር እግዚአብሔር እና የሁላችንም አባትን ታላቅ ስራ የሚረዱ እጆችን እንሰጠዋለን።14 ይህን ካደረግን፣ ልንሆን እንደሚገባን እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንሆናለን። በዚህ የትንሳኤ ሰንበት፣ እርስ በርሳችን እንዋደድ፣ እሱ እንደወደደን ሁሉ፣15 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እጸልያለሁ፣ አሜን።