2010–2019 (እ.አ.አ)
ወደፊት እንግፋ
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


2:3

ወደፊት እንግፋ

በእነዚህ ሁለት ቀናት የተሰማችሁን ስታሰላስሉና ስታስታውሱ ታዛዥ ለመሆነ ያላችሁ ፍላጎትም ያድጋል።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ለዚህ ታሪካዊ ጉባኤ መጨረሻ ስንደርስ፣ ጌታን ለመመሪያው እና ለሚያነሳሳ ተፅዕኖው ከእናንተ ጋር አመሰግነዋለሁ። መዝሙሩ ወብታማና የሚያነሳሳ ነበር። መልእክቶቹ የሚያሻሽሉ ብቻ ሳይሆን፣ ህይወት የሚቀርሩ ነበሩ።

በአምልኮ ስብሰባ አዲስ ቀዳሚ አመራርን ደገፍን። ሁለት ታላቅ ሰዎች በአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ ውስጥ ገብተዋል። እናም ስምንት አጠቃላይ ባለስልጣኖች ሰባዎች ተጠርተዋል።

አሁን የሚወደድ መዝሙር የታደሰውን ጥብቅ ውሳኔአችንን፣ ሀላፊነታችንን፣ እና ወደፊት ለመግፋት ያለንን ስራ ያጠቃልላል፥

ሁላችንም በጌታ ስራ ወደፊት እንግፋ፣

ህይወት ሲያልቅ ሽልማትን እንድናገኝ፤

በልትትል ባለው ጦረት ጎራዴን እንምዘዝ፣

የእውነት ሀይለኛ ጎራዴ።

አትፍሩ፣ ጠላት ቢያፌዝባችሁም፤

ተበረታቱ፣ ጌታ በጎናችን ነውና።

ክፉው የሚለውን አንሰማም፣

በጌታ ብቻ ነው የምንታዘዘው።1

የዚህን ጉባኤ መልእክቶች በየጊዜው—እንዲሁም በተደጋጋሚ—በሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንድታጠኑ አበረታታችኋለሁ። በቤተሰብ የቤት ምሽታችሁ፣ በወንጌል ማስተማሪያዎቻችሁ፣ በቤተሰብ ኣ በጓደኛ ንግግሮቻችሁ፣ እና እንዲሁም የእምነታችሁ አባል ካልሆኑት ጋር ባላችሁ ውይይት እነዚህን መልእክቶች የምትጠቀሙባቸውን መንገዶች አስባችሁ ፈልጓቸው። በዚህ ጉባኤ የተማሩት እውነቶች በፍቅር ሲቀርቡላቸው ብዙ ጥሩ ሰዎች መልስ ይሰጡበታል። በእነዚህ ሁለት ቀናት የተሰማችሁን ስታሰላስሉና ስታስታውሱ ታዛዥ ለመሆነ ያላችሁ ፍላጎትም ያድጋል።

ይህ አጠቃላይ ጉባኤ የአገልግሎት አዲስ ዘመንን ይጀምራል። እርስ በራስ በምንንከባከብበት መንገድ ጌታ አስፈላጊ ለውጦችን አድርጓል። እህቶች እና ወንድሞች፣ ወጣቶች እና ሽማግሌዎች፣ በአዲስ እና በቅዱስ መንገድ ያገለግላሉ። የሽማግሌዎች ሸንጎዎች የወንዶችን፣ የሴቶችን፣ እና የልጆችን ህይወቶች በአለም አቀፍ ለመባረክ ይጠናከራሉ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶችም በልዩ እና አፍቃሪ መንገድ፣ ለወጣት እህቶች በትክክለኛው ምድባቸው ከእነርሱ ጋር በመተባበር ለማገልገል ይቀጥላሉ።

ለአለም ያለን መልእክት ቀላል እና ልባዊ ነው፥ በመጋረጃው ሁለት በኩል ያሉትን የእግዚአብሔር ልጆችን ሁሉ ወደ አዳኛቸው እንዲመጡ፣ የቤተመቅደስ በረከቶችን እንዲቀበሉ፣ በደስታ እንዲጸኑ፣ እናም ለዘለአለም ህይወት ብቁ እንዲሆኑ እንጋብዛለን።2

በመጨረሻም ከፍተኛነት በቃል ኪዳን በምንሰራቸው እና በጌታ ቤት ውስጥ በምንቀበላቸው ስርዓቶች ሙሉ ታማኝነትን ይጠይቃል። በዚህ ጊዜ፣ 159 የሚሰሩ ቤተመቅደሶች አሉን፣ እናም ተጨማሪዎችም እየተገነቡ ናቸው። ቤተመቅደሶን ወደሚስፋፉት የቤተክርስቲያን አባላት ለማቅረብ እንፈልጋለን። ስለዚህ አሁን የሚገነቡ ሰባት አዲስ ቤተመቅደሶች ለማስተዋወቅ እንፈልጋለን። እነዚያ ቤተመቅደሶች በሚቀጥሉት ቦታዎች ይገኛሉ፥ ሳልታ፣ አርጀንቲና፤ በንጋሉሩ፣ ህንድ፤ ማናጋ፣ ኒካራጓ፤ ቻጋያን ደ ኦሮ፣ ፍሊፒንስ፤ ሌይተን ዩታ፤ ሪችመንድ፣ ቨርጅኒያ፤ እናም ቦታው ያልታወቀበት የራሺያ ትልቅ ከተማ።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የእነዚህ ቤተመቅደሶች መገንባት ህይወታችሁን የሚቀይሩ አይሆኑም፣ ነገር ግን በቤተመቅደስ ውስጥ የምታሳልፉት ጊዜ ግን በእርግጥም ለውጥ ይኖረዋል። በቤተመቅደስ ውስጥ ተጨማሪ ጊዜ ለማሳለፍ እንድትችሉ ወደ ጎን ለማድርግ የምትችሏቸውን እነዚያን ነገሮች እንድታውቁ እባርካችኋለሁ። በቤቶቻችሁ ውስጥ ታላቅ ስምምነት እና ፍቅር እና ዘለአለማዊ የቤተሰብ ግንኙነቶቻችሁን ለምንከባከብ ጥልቅ ፍላጎት እንዲኖራችሁ እባርካችኋለሁ። በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያድግ እምነት እንዲኖራችሁ እና እንደ እርሱ ደቀ መዛሙርት እርሱን የመከተል ታላቅ ችሎታ እንዲኖራችሁም እባርካችኋለን።

ድምጻችሁን፣ እኔ አሁን እንደማደርገው፣ በምስክርነት ከፍ እንድታደርጉ፣ በዚያም በሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ስራ ተሳታፊ እንሆን ዘንድ እባርካችኋአለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህችም፣ በተቀቡት አገልጋዮቹ በኩል የሚመራት፣ ቤተክርስቲያኑ ናት። ለእያንዳንዱ ለእናንየ ፍቅሬን እየቀለፅኩ፣ ስለዚህ የምመሰክረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።