ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ይናገራሉ
ነቢያት መኖራቸው እግዚአብሔር ለልጆቹ ስላለው ፍቅር ምልክት ናቸው። የእግዚአብሔር እና የኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን ቃል ኪዳኖች እና ስለ እውነተኛ ማንነታቸው እንዲታወቁ ያደርጋሉ።
ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ እናንተ የትም ብትሆኑ፣ ትናልትና ለሰጣችሁት ደጋፊ ምርጫ በልብ እና በዝልቅ የሚሰማኝን ምስጋና አቀርባለሁ። ምንም እንኳን እንደ ሙሴ በደንብ ተናጋሪ እንዳልሆንኩኝ ቢሰማኝም፣ ጌታ ለእርሱ ባላቸው ቃላቶች እፅናናለሁ፥
“የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳስ ደንቆሮስ የሚያይስ ዕውርስ ያደረገ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
“እንግዲህ አሁን ሂድ፥ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፥ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ” (ዘጸአት 4፥11–12፤ ደግሞም ቁጥር 10 ተመልከቱ)።
ደግሞም በተወዳጇ ባለቤቴ ፍቅር እና ድጋፌም እፅናናለሁ። እርሷም የደግነት፣ የፍቅር፣ እናም ለጌታ እና ለእኔ እና ለቤተሰቤ የፍጹም አምላኪነት ምሳሌ ነች። በልቤ በሙሉ አፈቅራታለሁ፣ እናም በእኛ ላይ ስለነበራት መልካም ተፅዕኖ አመሰግናታለሁ።
ወንድሞች እና እህቶች፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በምድር ላይ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደሆኑ ለመመሥከር እፈልጋለሁ። እንደ እርሳቸው የሆነ ማንም ደግ እናአፍቃሪ ሰው መንም አይቼ አልነበረም። ለዚህ ቅዱስ ጥሪ ብቁ እንዳልሆንኩኝ ቢሰማኝም፣ ይህን ሀላፊነት ሲሰጡኝ የነበራቸው ቃላት እና በአይናቸው የሚታየው ደግነት በአዳኝ ፍቅር እንደታቀፍኩኝ እንዲሰማኝ አደረገኝ። አመሰግንሆታለሁ፣ፕሬዘደንት ኔልሰን። እደግፍዎታለሁ እናም አፈቅርዎታለሁ።
የጌታን ፍላጎት የሚያውቁና የሚከተሉ፣ ነቢያት፣ ባለራዕያት፣ እና ገላጮች በምንኖርባቸው በእነዚህ ቀናት በምድር ላይ መገኘታቸው በረከት አይደለምን? በህይወታችን በሚያጋጥሙን ፈተናዎችም በአለም ውስጥ በብቻችን አለመሆናችንን ማወቅ የሚያፅናና ነው። ነቢያት መኖራቸው እግዚአብሔር ለልጆቹ ስላለው ፍቅር ምልክት ናቸው። የእግዚአብሔር እና የኢየሱስ ክርስቶስ ለህዝቦቻቸው ያላቸውን ቃል ኪዳኖች እና ስለ እውነተኛ ማንነታቸው እንዲታወቁ ያደርጋሉ። ይህንንም በራሴ አጋጣሚዎች ተምሬአለሁ።
ከአስራ ስምንት አመት በፊት፣ ባለቤቴ እና እኔ፣ በዚያ ጊዜ የቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ ከነበሩት፣ ከፕሬዘደንት ጄምስ ኢ. ፋውስት የስልክ ጥሪ ተቀበልን። እንደ ሚስዮን ፕሬዘደንት እና ተባባሪ እንድናገለግል ጠሩን። የወንጌል አገልግሎታችንን ለመጀመር ስድስት ሳምንት እንዳለን ነገሩን። ምንም እንኳን ለዚህ የተዘጋጀሁ እና ብቁ እንዳልሆንን ቢሰማንም፣ ጥሪውን ተቀበልን። በዚያ ጊዜ በጣም የምናስብበት የነበረው ወደምናገለግልበት አገር ለመግባት ቪዛ ለማግኘት ነበር ምክንያቱም፣ በድሮ አጋጣሚዎች መሰረት፣ ይህን ለመፈጸም ከ6 እስከ 8 ወር እንደሚፈጅ እናውቅ ነበር።
ፕሬዘደንት ፋውስት ከዚያም ጌታ ታዕምራት እንደሚፈፅም እና የቪዛ ችግርን በፍጥነት መፍትሄ ለማግኘት እንደምንችልባቸው እምነት እንዳለን ጠየቁን። መልሳችንም አዎን ነበር እናም ወዲያው ነገሮችን ማዘጋጀት ጀመርን። ለቪዛ የሚያስፈልገውን መረጃዎች አዘጋጅን፣ ለሶስቱ ወጣት ልጆቻችን ወሰድን፣ እና በፍጥነት ወደ ቆንስላ ቢሮ ሄድን። በዚያም በጣም ደግ ሴት አገኘን። ወረቀቶቻችንን በመመልከት እና በፖርቱጋል ምን እንደምናደርግ በማወቅ፣ ወደ እኛ በመዞር እንዲህ ጠየቀችን፣ “የሀገሬን ህዝቦች በእርግጥም ለመርዳት ነው የምትሄዱትን?” እኛም በእርግጠኛ አዎን ብለን መለስን እናም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምንወክል እና ስለእርሱና በምድር ላይ ስለነበረው መለኮታዊ አገልግሎት እንደምንመሰክር ገለፅን። ከአራት ሳምንት በኋላ ተመለስን፣ ቪዛችንን ተቀበልን፣ እናም፣ የጌታ ነቢይ እንድናደርግ እንደጠየቀን፣ በስምንት ሳምንት ውስጥ በወንጌል በምናገለግልበት ቦታ ውስጥ ደረስን።
ወንድሞች እና እህቶች፣ በልቤ ሁሉ ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ሀይል እንደሚናገሩ አውቃለሁ። ስለክርስቶስ እና በምድር ላይ ስላለው መለኮታዊ ተልዕኮው ይመሰክራሉ። የጌታን አዕምሮ እና ልብ ይወክላሉ እናም እርሱን እንዲወክሉና በእግዚአብሔር እና በልጁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ ፊት ለመኖር ለመመለስ ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲያስተምሩን ተጠርተዋል። እምነታችንን ስንለማመድ እና የእነርሱን ትምህርት ስንከተል እንባረካለን። እነርሱን በመከተል፣ ህይወታችን ደስተኛ እና ውስብስብ ያልሆኑ ይሆናሉ፣ ችግሮቻችንም ለመሸከም ቀላል ይሆናሉ፣ እናም በቀናችን ጠላት ከሚያጠቃን ለመከላከል በመንፈስ ጥሩር እንሰራለን።
በዚህ በፋሲካ ቀን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተነሳ፣ ህያው እንደሆነ፣ እና በምድር ላይ ያለችውን ቤተክርስቲያኑን በነቢያቱ፣ ባለራዕዮቹ፣ እና በገላጮች እንደሚመራ እመሰክራለሁ። እርሱ የአለም አዳኝ እና ቤዛ እንደሆነ እናም በእርሱ በኩል ለመዳን እና በውዱ እግዚአብሔር ፊት ከፍ ከፍለማለት እንደምንችል ይመሰክራለሁ። እርሱን አፈቅራለሁ፣ እናም እወደዋለሁ። እርሱን ለመከተልና የእርሱን ፍላጎት ለማድረግ እናም እንደ እርሱ በተጨማሪም ለመሆን እፈልጋለሁ። ስለእነዚህ ነገሮች የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።