2010–2019 (እ.አ.አ)
አዳኝ እንደሚያድርገው ማገልገል
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


2:3

አዳኝ እንደሚያድርገው ማገልገል

እኛም ለእግዚኣብሔር ምስጋናችንን እና ፍቅራችንን፡ ዘላለማዊ እህቶቻችንን እና ወንድሞቻችንን በፍቅር በማገልገል እናሳይ።

እንዴት ያለ ድንቅ በረከት ነው ከእግዚአብሕር በማያቋርጥ የራእይ ጊዝ መኖር! “የሁሉንም ነገሮች መመለስን”1 ወደፊት በመመልከት ስንጠባበቅ እና ስንቀበል፣ በትንቢት ተተንብዮ ስለመጣው እና ስለሚመጣው የጊዝያችንን ክስተቶችን ስንቀበል፤ ለኣዳኝ ዳግም ምጽኣት እየተዘጋጀን ነው።2

እናም ዕርሱን ለመቀበል ለመዘጋጀት በፍቅር እርስ በርስ በማገልገል እሱን ለመምሰል ከመጣር የተሻለ ምን መንገድ አለ! ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዘመን መጀመሪያ ላይ ለተከታዮቹ እንዳስተማረው ”ብትወዱኝ ታገለግሉኛላችሁ።” 3 የእኛ ሌሎችን ማገልገል፡ ደቀመዛሙርትነታችንን እና ምስጋናችንን እናም ፍቅራችንን ለእግዜአብሕር እና ለልጁ ለእየሱስ ክርስቶስ የሚያሳይ ነው።

እንዳንድ ጊዜ ጎረቤቶቻችንን ማገልገላችንን ለመቁጥር ትልቅና ጀግናዊ የሆነ ነገር ማድረግ ኣለብን ብለን እናስብ ይሆናል። ነገር ግነ ትንሽ የኣገልግሎት ስራ በእኛ ላይም ሆነ በልሎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል። አዳኝስ ምን አደረገ? በእርሱ መለኮታዊ የሃጢያት ክፍያ እና የ ትንሳኤ ስጦታው፤ በዚህ በሚያምር እሁድ ፋሲካ የምናከብረው ፤ “ማንም በዚህ ምድር ላይ በነበሩትም ላይ ሆነ ወደፊት በሚኖሩት ላይ እጅግ ከፍተኛ ተፀኖ እሳድሮ ኣያውቅም።”4 ነገር ግን እርሱ ፈገግ አለ፣ አብሮ አዋራ፣ አብሮ ተራመደ፣ አዳመጠም፣ ጊዜም ሰጠ፣ አበረታታም፣ አስተማረም፤ መገበ፣ እናም ይቅርታን አደረገ። ቤተሰብን እና ጓደኛን፣ ጎረበቶችን እና እንግዶችን በኣንድ ኣይነት አገለገለ፣ እናም የሚያውቃቸውን እና ወዳጆቹን ድንቅ የሆንውን የወንጌሉን በረከት እንዲቋደሱ ጋበዛቸው። እነዛ ትንንሽ የአገልግሎትና የፍቅር ድርጊቶች ለዛሬ እገልግሎታችን ምሳሌ ያቀርባሉ።

ለማገልገል ስትጥሩ አዳኝን ለመወከል እድል እንዳላችህ ሁሉ፤ እራሳቹሀን ጠይቁ፤ ”እንዴት ነው የወንገልን ብርሃን ለማካፈል የምችለው ከዚህ ግለሰብ ውይም ቤተሰብ ጋር? መንፈስ ምን እንዳደርግ እያነሳሳኝ ነው?”

እገልግሎት በተለያየ ግላዊ በሆኑ መንገዶች ሊደረግ ይችላል። እናስ ምን ይመስላል?

እገልግሎት ይህን ይመስላል፡ የሴቶች እና የወንዶች ኣጠቃላይ የመረዳጃ ኣመራሮች፡ በፅሎት ስለ ጥሪ ይመካከራሉ። መሪዎች ብጫቂ ወረቀት እያወጡ ከመስጠት ይልቅ፤ ስለግለሰብ እና ስለ ቤተሰቦች በኣካል ለሚያገለግሉት ለወንድሞች እና ለህቶች ጥሪ በሚሰጥበት መመካከርን ይመስላል። ኣንድ ላይ እብሮ መራመድን፣ ለጨዋታ ምሽት ኣንድ ላይ መገናኘትን፤ ኣገልግሎት ማቅረብን ወይም ኣንድ ላይ ማገልገልን ይመስላል። በኣካል መጎብኘትን ወይም በስልክ ማውራትን ይመስላል ወይም በቀጠታ መስመር ላይ ማውራትን ወይም መልክት መላላክን ይመስላል። የልደት ካርድ ማድረስን ወይም የእግር ካስ ጨዋታ መደገፍን ይመስላል። ለዛ ግለሰብ ትርጉም የሚኖረው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ወይም ከጉባኤ ስብከት ላይ ጥቅስ ማካፈልን ይመስላል። የወንግልን ጥያቄ መወያየት እንዲሁም መግለጽን እና ሰላምን ለማምጣት ምስክርነትን ማካፈልን ይመስላል። የኣንድ ሰው የህይወት ኣካል እየሆኑ ስለመምጣትና ስለሱ ወይም ስለሷ ማሰብን ይመስላል። እንዲሁም ፍላጎቶችን እና ጥንካሬዎች በኣግባቡ እና በሚስጥራዊነት የሚወያዩበት የኣገልግሎት ቃለመጠይቅ ማድረግን ይምስላል። የካስማው ምክር ቤት ተለቅ ላለ አስፈላጊ ጉዳይ መልስ ለመስጠት መደራጀትን ይመስላል።

እንደዚህ ኣይነት ኣገልግሎት ኣንድ ባሏ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት ሲጀምር ከቤቷ እርቃ የተጓዘችን እህትን ኣጠነከረ። ከማይሰራ ስልክ ጋር እና ከኣንድ ህጻን ልጇ ጋር በኣዲሱ ሰፈር ጉስቁልና፣ ፍጹም ግራመጋባት እና ብቸኝነት ተሰማት። ያለምንም ቅድመ ማስታወሻ የሴቶች መረዳጃ እህት፣ ለልጇ ትንሽ ጥንድ ጫማዎችን ይዛ፣ ሁለቱንም ወደ መኪናዋ ኣስገብታ፣ የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ ለመፈለግ ልትወስዳቸው መጣች። ኣመስጋኟ እህትም እለች፤ “እሷ የሂወቴ መስመር ነበረች”!

እውነተኛ ኣገልግሎት በኣፍሪካ ውስጥ ለረዥም ጊዜ የቤተክርስትያን ስብሰባን ያልተካፈለች እህትን ትፈልግ ዘንድ የቤትስራ ተሰጥቷት በነበርች ባንድ ትልቅ እህት ተገልጿል። ወደዚች እህት ቤት ስትሄድ፣ ሴትየዋ ተደብድባ እና ተሰርቃ፤ በጣም ትንሽ የምትበላው ኖሯት፤ እናም ለሁድ የቤተክርስትያን ስብሰባ ኣግባብ ያለው ልብስ ነው ብላ የሚሰማት ልብስ ሳይኖራት እገኘቻት። እንድታገለግላት የቤት ስራ የተሰጣት ሴት፤ የሚያዳምጥ ጆሮ፤ ኣታክልት ከጓሮዋ ፤ የሚነበቡ ቅዱሳን መጻህፍትን እና ጓደኝነትን ኣመጣችላት። ጠፍታ የነበረችውም እህት በቅርቡ ወደ ቤተክርስትያን ተመለሰች፤ እናም ኣሁን ጥሪ ይዛለች ምክንያቱም መወደዷን እና ዋጋ የተሰጣ መሆኗን በማወቋ።

ኣሁን እንደ ኣዲስ ከተዋቀረው የክህነት ሽማግሌ ቡድኖች ጋር፤ እንደዚህ ኣይነት የሴቶች መረዳጃ ህብረት ጥረትን ማስተባበር ፡ የሚያስደንቅ ፍሬን የሚያፈራ ኣንድነትን ያመጣል። ኣገልግሎት የክህነት ግዴታን ለሟሟላት፤ “የእያንዳንዱን ኣባል ቤት ለመጎብኘት”፤ እና “ቤተክርስትያኑን ሁልጊዜ ለመጠበቅ ፣ ኣብሮ ለመሆን እናም ለማጠንከር”5 እንዲሁም የሴቶች መረዳጃ ማህበር ኣላማ የሆነውን እርስ በእርስ በመረዳዳት ለዘለዓለም ሂወት በረከት መዘጋጀትን ለማሳካት ኣንድ የተቀናበረ ጥረት እየሆነ ይመጣል።6 በኤጲስ ቆጶሱ መመሪያ መሰረት እብሮ በመስራት፣ የወንዶች እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር መሪዎች፣ እያንዳንዱን ቤተሰብ እና ግለሰብ በምን እይነት ጥሩ ሁኔታ መንከባከብ እና መጠበቅ እንዳለባቸው ሲሹ ሊመሩ ይቸላሉ።

እንድ ምሳሌ ልስጣችሁ። ኣንድ እናት የነቀርሳ በሽታ ተገኘባት። ወዲያውኑ መድሃኒቱን ጀመረች፣ ወዲያውኑም የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች፤ እንዴት በምግብ ፣ ለህክምና ቀጠሮዎች መጓጓዣ ፣ እናም ሌሎች እርዳታዎች በደንብ እንደሚረዱ በማቀድ ወደ ስራ ሄዱ። በመደበኛነት፣ ኣስደሳች ኣጋርነትን በመለገስ ጎበኟት። በተመሳሳይ ጊዜም የመልከፀዴቅ የክህነት ስልጣን ማህበር በፍጥነት እርምጃ ወሰዱ። የታመመችውን እህት ለመንከባከብ ይቀል ዘንድ የታደሰ መኝታ ቤት እና ሽንት ቤት ለመጨመር ጉልበታቸውን ዓቀረቡ። ወጣት ወንዶች በዚህ ኣስፈላጊ ጥረት ውስጥ ለመሳተፍ እጃቸውን እና ጀርባቸውን ኣዋሱ። ወጣት ሴቶችም ተሳተፉ፤ በደስተኝነት እና በታማኝነት ውሻዋን በየቀኑ ለማናፈስ ተደራጁ። ጊዜ ባለፈ ቁጥር፣ በሚያስፈልግበት በመጨመር እና ማስተካከያ በማድረግ አጥቢያው፣ ማገልገላቸውን ቀጠሉ። በግልፅም የፍቅር ልፋት ነበር፤ እያንዳንዱ አባል እራሱን ወይም እራሷን በመስጠት፤ በአንድነት በተለያየ መልኩ እንክብካቤን በማሳየት የምትሰቃየውን እህት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን እያንዳንዱን የቤተሰቧን አባል ባረከ።

ከብርቱ ጥረት በኋላ ይች እህት በነቀርሳው በሽታ ተሸነፈች እናም ታርፍ ዘንድ ተቀበረች። አጥቢያው በእፎይታ በመተንፈስ እና ስራው በተገቢው እንዳለቀ አሰቡን እንዴ? አላሰቡም፤ ወጣት ሴቶቹ ውሻውን በየቀኑ ማናፈሳቸውን ቀጠሉ፤ የክህነት ስልጣን ማህበርም አባትየውን እና ቤተሰቡን ማገልገላቸውን ቀጠሉ፤ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶችም ጥንካሬን እና ፍላጎቶችን ለማረጋገጥ በፍቅር መድረሳቸውን ቀጠሉ። ወንድሞች እና እህቶች፤ ይሄ ማገልገል ነው፤ ይሄ ኣዳኝ እንደሚወድ መውደድ ነው!

ሌላው የእነዚ በመንፈስ የተነሳሱ ማስታውቂያዎች በረከት፣ ለወጣት ሴቶች እድሚያቸው ከ14–18 ከሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች ጋር ኣጋር ሆኖ ለማገልገል እድል ማግኘታቸው ነው፣ ልክ በተመሳሳይ እድሜ ያሉ ወጣት ወንዶችም ከመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን ወድሞች ጋር አጋር ሆነው ያገለግላሉ። ወጣቶች በማዳን ሰራ ውስጥ ከኣዋቂዎች ጋር ኣንድ ላይ ሲያገለግሉ ልዩ ስጦታቸውን ያካፍላሉ እናም በመንፈስ ያድጋሉ። ወጣቶችን በኣገልግሎት ስራ ላይ ማሳተፍ፣ የተሳታፊን ቁጥር በመጨመር፣ የሴቶች እና የወንዶች፣ መረዳጃ ማህብር ሌሎችን የመንከባከብ ጥረታችውን እንዲጨምሩ ያደርጋል።

ስለማቃቸው ድንቅ ወጣት ሴቶች ሳስብ፤ ለእነዛ ጎን ለ ጎን ለሚያገለግሉ ወይም በእነሱ ለሚገለገሉ በወጣት ሴት ጉጉት፣ ስጦታ፣ እና የመንፈስ ንቁነት፣ ለመባረክ እድል ላላቸው የመረዳጃ ማህበር እህቶች እጅግ ደስ ይለኛል። በተመሳሳይ መልኩ በሴቶች መረዳጃ እሀቶች ለመሰልጠን፣ ለመማር እና ለመጠንከር ወጣት ሴቶች ስለሚኖራቸው እድል እጅግ ደሥተኛ ነኝ። ይህ የእግዜብሔርን መንግስት ለመገንባት መሳተፊያ ዕድል ለወጣት ሴቶች በሀብረተሰቡ ወስጥ እና በቤተክርስትያን ወስጥ በመሪነት ሰለሚኖራቸው ሚና በደንብ ለመዘጋጀት እና እንዲሁም እንደተሳታፊ ኣጋርነት በቤተሰባቸው ውስጥ ለመርዳት ከፍተኛ ጠቀሜታ ኣለው። ለክ እህት ቦኒ  ኤል ኦስካርሰን ትናንትና እንዳካፈለችው፤ ወጣት ሴቶች “ማገልገል ይፈልጋሉ። ዋጋ እንዳላችው እና በማዳን ስራ ውስጥም አስፈላጊ እንደሆኑ ማወቅ ያስፈልጋቸዋል።”7

በእርግጥም፣ ወጣት ሴቶች፣ ያለምንም የስራ ድርሻ ወይም ኣጫፋሪ ሌሎችን እያገለገሉ ናችው። የማውቃቸው ቤተሰብ በብዙ መቶዎች ማይል ርቀት ማንንም ከማያውቁበት ስፍራ ተጓዙ። በመጀመሪያው ሳምንት የ 14 ዓመት ሴት ልጅ ከኣዲሱ አጥቢያቸው ብስኩቶች ይዛ ወደ ኣክባቢው እንኳን ደህና መጣችሁ እያለች ደጃፋቸው ላይ ነበረች። እናቷ ከኋላዋ የልጇን የማገልገል ፍላጎት ለመደገፍ ልክ እንደ ፍቃደኛ ሹፌር ፈገግ ብላ ቆማ ነበር።

ኣንድ ሌላ እናት የ 16 ዓመት ልጇ በተለመደው ሰዓት እቤት ባለመሆኗ ሃሳብ ገብቷት ነበር። በመጨረሻም ልጅቷ ስትደርስ፡ እናቷ የት እንደነበረች ትንሽ በመበሳጨት ጠየቀቻት። የ16 ዓመቷም ልጅ ሰበር ብላ ባሏ ለሞተባት በቅርብ ለምትኖር ባልቴት ኣበባ ልታድርስ እንድሄደች መለሰች። ባልቴቷ ብቸኛ እንደሆነች ኣየች እናም ትጎበኛት ዘንድ ተንሳስታ ነበር። በእናቷ ሙሉ ፍቃድ፤ ወጣቷ ሴት ባልቴቷን መጎብኘቷን ቀጠለች። ጥሩ ጓደኞችም ሆኑ እናም ጣፋጭ ግንኙነታቸውም ለብዙ ዓመት ቀጠለ።

እነዚህ እያንዳንዳችው ወጣት ሴቶች፤ እና እነሱን የመሳሰሉ ብዙዎች ፣ የሌሎችን ፍላጎት ያያሉ እናም ያሟሉት ዘንድ ይሰራሉ። ወጣት ሴቶች ከኣዋቂ እህቶች ጋር በማስተባበር ሊያገለግሉበት ይሚችሉ ተፈጥሮኣዊ የሆነ የመንከባከብ እና የማካፈል ፍላጎት ኣላቸው።

እድሚያችን ምንም ይሁን፤ እንዴት በውጤታማነት ማገልገል እንዳለብን ስናስብ፣ ”እሱ ወይም እሷ ምን ትፈልጋለች ብለን?” እንጠይቅ ያንንም ጥያቄ ከልብ ከመነጨ የማገልገል ፍላጎት ጋር በማቀናበር፤ ከዛም ያንን ግለሰብ የሚያጠነክር እና ይሚያበረታታ ነገር ለማድረግ በመንፈስ እንመራለን። በቀላል የማካተት እና እንኳን ወደ ቤተክርስትያን ደህና መጣችሁ፤ የታሰበበት ኢሜል እና የፁህፍ መልዕክት፣ በኣስቸጋሪ ጊዜ የግል መረጃ ፤ በቡድን ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ግብዣን፤ በሚያስቸግር ሁኔታ ውስጥ እርዳታ በመሰንዘር የተባረኩ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የወንድሞች እና የእህቶች ታሪክን ሰምቻለሁ። ብቸኛ ወላጆች፣ ኣዲስ ተጠማቂዎች፣ በንቁ በቤተክርስትያን ውስጥ የማይሳተፉ ኣባሎች፣ ባለቤታቸው የሞተባችው ባልቴቶች እና ኣባወራዎች ፣ ወይም እየታገሉ ያሉ ወጣቶች ፡ ከኣገልጋዮች ወንድሞች እና እህቶች የበለጠ ትኩረት እና ቅድመ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። የወንዶች እና የሴቶች መረዳጃ ማህብር መሪዎች መተባበር ተገቢ ስራዎች እንዲሰሩ ያደርጋል።

ሁሉም ነገር ከተባለ እና ከተደረገ በኋላ፡ እውነተኛ ኣገልግሎት ኣንድ በኣንድ የሚፈጸመው ፍቅር እንደመነሳሻ ሲሆን ነው። ከልብ የማገልገል የላቀ ዋጋው እና ድንቅነቱ፣ ፍፁም ሂወትን ይቀይራል! ልቦቻችን ለመውደድ እና ለማካተት፤ ለማበረታት ፤ ለማፅናናት ክፍት እና ፍቃደኛ ሲሆኑ የማገልገላችንን ሃይል የማንቋቋመው ይሆናል። ፍቅር እንደመነሳሻ ሲሆን ፡ ታምራቶች እና የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ይከሰታሉ። “የጠፉ” እህቶቻችንን እና ወንድሞቻችንን ሁሉን ወደሚያካትተው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እቅፍ እናመጣለን።

በሁሉም ነገር ውስጥ ኣዳኝ የእኛ ምሳሌ ነው፤ ምን ማደረግ እንዳለብን ብቻ ሳይሆን ለምን ማድረግ እንዳለብንም ጭምር።8 “የእርሱ የምድር ላይ ሂወት ለእኛ ግብዣችን ነበረ፤ እይታችንን ትንሽ ከፍ ለማድረግ፤ የራሳችንን ችግሮች ለመርሳት እና ለሌሎች ለመድረስ።”9 በሙሉ ልብ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የማገልገል እድሉን ስንቀበል፤ የበለጠ በመንፈስ እንጠራ ዘንድ፤ የእግዚኣብሔር ፍቃድ እናዳምጥ ዘንድ፤ እንዲሁም የበለጠ የእርሱን እያንዳንዱን ወደሱ እንዲመለሱ የመርዳት እቅዱን በመረዳት እንባረካለን። የበለጠ የእርሱን በረከቱን እናስተውላለን እናም ያን በረከት ለሌሎች ለማካፈል እንጓጓለን። ለባችንም ከድምፃችን ጋር በኣንድነት ይዘምራል፤

አዳኝ፣ ወንድሜን ልውደድ

አንተ እንደምትወደኝ እንደማውቀው፣

በአንተ ጥንካሬዬን፣ ምልክቴን ላግኝ፣

የአንተ አገልጋይ እሆናለሁ።

አዳኝ፣ ወንድሜን ልውደድ—

ጌታ፣ እከተልሀለሁ።10

የዘለአለም እህቶቻችንን እና ወንድሞቻችንን በማገልገል ለእግዚአብሔር ያለንን ምስጋና እና ፍቅረናሳይ።11 ውጤትም በጥንት አሜሪካ ውስጥ አዳኝ በምድራቸው ከመጣ በኋላ ለ100 አመታት ሰዎች ይደሰቱባቸው እንደነበረ አይነት የአንድነት ስሜት ይሆናል።

“እናም እንዲህ ሆነ በህዝቡ ልብ ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር ፍቅር የተነሳ፣ … ፀብ አልነበረም።

“… እናም በእርግጥ በእግዚያብሄር እጅ ከተፈጠሩት ሰዎች መካከል እንደ እነዚህ ያለ ደስተኛ ሊሆን የቻለ ህዝብ አልነበረም።”12

እነኚህ የተገለፁት ለውጦች በእግዜኣብሔር የተነሳሱ እንደሆነ እና ፤ በፍፁም ልቦች ከተቀበልናቸው፤ ልጁ እየሱስ ክርስቶስን በዳግም ምጽአቱ ለመቀበል በደንብ የተዘጋጀን እንደምንሆን በደስተኝነት የግል ምስክሬን እሰጣለሁ። የፂዎን ሰዎች ለመሆን እየቀረብን እንመጣለን፤ እናም የሚደንቅ ደስታ ከእነኛ በደቀመዛሙር መንገድ ላይ ከረዳናቸው ጋር ይሰማናል። ይሰማናል። ያን እናረግ ዘንድ ትጉህ እና ትሁት ፀሎቴ ነው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ኣሜን።