2010–2019 (እ.አ.አ)
በአንድ ልብ
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


2:3

በአንድ ልብ

ልብ የሚማርክ እጣ ፈንታችንን ለመድረስ ለመቻል፣ እርስ በራስ እንፈላለጋለን፣ እናም አንድ መሆን ያስፈልገናል።

በምድር ልይ በጣም አስገራሚ ከሆኑት ፍጥረት መካከል ንጉሱ ቢራቢሮ ነው። የገናን በአል ከባለቤቴ ቤተሰብ ለማክበር ወደ ሜክስኮ ጉዞ ላይ የቢራቢሮዎችን መቀድስ ጎበኘን፥ በሚልዮን የሚቆጠሩ ነገስታት ቢራቢሮዎች ክረምትን የሚያሳልፉብት። የሚያስገርም ቦታን ማየትና የእግዚአብሔር ፍጥረታት የሚያሳዩትን የአንድነት ምሳሌና መለኮታዊ ታዛዥነት ማንጸባረቃችን አስዳናቂ ነበር።1

ነገስታት ቢራቢሮዎች
ቢራቢሮዎች ተሰብስበው

ነገስታት ቢራቢሮዎች ዋነኛ መሪዎች ናቸው። የጸሃይን አቀማምጥ በመጠቀም ወዴት መሄድ እንዳለባቸው ይውቃሉ። በጸደይ ወቅት ከሜክስኮ ብዙ ማይል በመጓዝ ወደ ካናዳ ይሄዳሉ እና በበልግ ሰአት ቅዱስ በሆነው ወደ ሜክስኮ ጫካ ይመለሳሉ።2 ይህንን ከአመት ወደ አመት ያደርጋሉ፣ አንድ ትንጥ ክንፍ በአንድ ጊዜ በማጠፍ። በጉዛቸው ወቅት፥ በምሽት እራሳቸውን ከብርድና ከጠላት ለመጠበቅ አንድ ላይ በዛፍ ላይ ይከማቻሉ ።3

ኬልዶስኮፕ ቢራቢሮዎች
ሁለተኛ ኬልዶስኮፕ ቢራቢሮዎች

የቢራቢሮዎች ቡድን ኬልዶስኮፕ በመባል ይታወቃል።4 የሚያምር ምስል አይደለምን? በኬልዶስኮፕ ውስጥ እያንዳንዱ ቢራቢሮ ልዩና የተለየ ነው፣ ሆኖም እነዚ ስስ ፍጥረቶች በተወዳጁ ፈጣሪ ተነድፈው የመኖርን አቅም፣ የመጓዝ፣ የመዋለድ፣ እናም ሲጓዙ ህይወትን በመዝራት ከአንድ አበባ ወደ ሌላ አበባ አንዲቀስሙ አቅም ተሰጥቷቸዋል። ምንም እንኳ እያንዳንዱ ቢራቢሮ ቢለያዩም አንድ ላይ አለምን ውብና ፍሬያማ ለማድረግ ይሰራሉ።

እንደነገስታት ቢራቢሮዎቹ እኛም ወደ ሰማዩ ቤታችን ጉዞ ላይ ነን ከሰማዩ ወላጆቻችን ጋራ ለመገናኘት።5 እንደቢራቢሮዎቹ መለኮታዊ የሆነ ባህሪ ተሰጥቶናል ህይወታችንን ለመምራት፥ የተፈጥሯችንን ልኬት ለመሙላት።6 እንደነሱ፥ ልባችንን አንድ ላይ ካቀናጀን፥7 ጌታ ይጠብቀናል “ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፏ እንደምትሰበስበው”8 እና ውብ ያደርገናል።

ሴትና ወንድ፣ ወጣት ሴትና ወጣት ወንድ፣ እህትና ወንድም፥ በዚህ ጉዞ ላይ አንድ ላይ ነን። አስደናቂ የሆነውን ግባችንን ለመድረስ አንዳችን ለሌላችን እናስፈልጋለን፥ እናም በአንድ መሆን ይስፈልገናል። ጌታ እንዳዘዝዘን፣ “አንድ ሁኑ፤ እናም አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም።”9

ኢየሱስ ክርስቶስ ከአባቱ ጋር ባለው አንድነት ዋነኛ ምሳሌ ነው። “የወልድ ፍቃድ በአብ ፍቃድ ውስጥ ተውጦ።” በአላማ ፣ በፍቅር፣ እናም በስራ አንድ ናቸው።10

ጌታ ከአባቱ ግር ያለውን የአንድንነት ፍጹም ምሳሌን በመከተል ከእነርሱ ጋርና እርስ በእርሳችን አንድነትን ማድረግ እንዴት እንችላለን?

የሚያስገርም አሰራር ሐዋሪያት ስራ1፥14 ውስጥ ይገኛል። እናነባለን፣ “[ወንዶቹ] በጸሎትና በጽሞና በአንድ ልብ ሆነው ከሴቶቹ ይተጉ ነበር።”11

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ስያርግ ደቀ መዛሙሮች ወድያውኑ በትጋታቸው ምክንያት ስለተቀበሉት በረከት በሃዋርያት ስራ ላይ “በአንድ ልብ” የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ መጠቀሱ አስፈላጊ ይመስለኛል። በአሜሪካ አህጉር ውስጥ ጌታ በጐበኛቸውና በአገለገላቸው ሰአትም ተመሳሳይ ምሳሌን እናያለን። “በአንድ ልብ” ማለት በስምምነት፣ በህብረት፣ እናም በአንድ ላይ ማለት ነው።

ታማኞቹ ቅዱሳን ካደረጉት አንዳንድ ነገሮች ውስጥ በሁሉቱም ቦታ በአንድነት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መስክረዋል፥ የእግዛብሄርን ቃል በአንድነት አጥንተዋል፣ እናም በፍቅር እርስ በእርሳቸው ተረዳድተዋል።12

የጌታ ተከታዮች በአላማ፣ በፍቅር፣ እና በስራ ላይ አንድ ነበሩ። ማን እንደነበሩ ያውቁ ነበር፣ ምን ማድረግ እንደነበረባቸው ያውቁ ነበር፣ እናም ያደርጉ የነበሩት በእግዛብሔርና በእርስ በእርሳቸው ባላቸው ፍቅር ነው። እጹብ ድንቅ በሆነውን በኬልዶስኮፕ አንድነት ወደፊት ጎዞ ያቀኑ ነበሩ።

ከተቀበሏቸው በረከቶች መካከል በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር፣ ተኣምራት በመካከላቸው ተደርጎ ነበር፣ ቤተ-ክርስትያኗም አደገች፣ በመካከላቸውም ጠብ አልነበረም፣ እናም ጌታም በሁሉም ነገር ባርኳቸው ነበር።13

በእርግጥ አንድነት የነበራቸው ምክንያት ጌታን በበኩላቸው ስላውቁት ነው ብለን መገመት እንችላለን። ከአጠገቡም ነበሩ፣ የመለኮታዊ ተልኮውም ምስክሮች ነበሩ፣ ታኣምራትንም ሲያደርግ እናም ትንሳኤውም። የእጆንና የእግሮቹንም ምልክት አይተዋልም ዳስሰዋልም። በርግጠኝነት ቃል የተገባለት መሲህ መሆኑኑን እንዲሁም የአለም መድሃኒት መሆኑን አውቀው ነበር። “የመዳን፣ የሰላምና፣ የዘላለማዊ እድገት ምንጭ” መሆኑን አውቀው ነበር።14

ምንም ያህል አዳኝችንን በእውን አይናችን ባናየው እንኳን ህያው እንደሆነ ማወቅ እንችላልን። ወደ እርሱም ስንጠጋ፣ ስል ትልእኮው ግላዊ ምስክርነት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እንዲኖረን ስንሻ፥ የበለጠ ስለአአላማው እንረዳለን፥ የእግዛብሔር ፍቅር በልባችን ያድራል፤15 እንደኬሊደስኮፕ ቤተሰብ፣ በዋርዳችን፣ በማህበረተሰባችን ውስጥ አንድ እንድንሆን ወኔ ይኖረናል። እርስ በእርሳችንም “በአዲስና በተሻለ መንገድ” እንረዳዳለን።16

የእግዛብሔር ልጆች በመንፈስ ተመርተው ለተቸገሩ ሲደርሱ ታኣምራቶች ይከሰታሉ።

አዳኞች የሚገኝበት በጎርፍ የተሞላ መንገድ

ብዙ ታሪኮችን እንሰማለን በመቅሰፍት ጊዜ በሰዎች መካከል ስላለ ጎረቤታዊ ፍቅር። ለምሳሌ ባለፈው አመት የህዩስተን ከተማ በጥልቅ ጎርፍ ስትሰቃይ ሰዎች የራሳቸውን ፍላጎት ትተው ለማዳን ሲሄዱ። የሽማግሌ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ለእርዳታ ተጣራ፥ እናም ሰባሰባት ታንኳዎች በፍጥነት ተዘጋጁ። የአደጋ ጊዜ አዳኞች ወደ ተጠቂ ጎረቤቶች በመሄድ ቤተሰቦችን ወደ ስብስባ አዳራሽ ኣጓጓዟቸው፥ መጠለያም ተቀበሉ እናም ብዙዎችም እርዳታን ፈለጉ። ኣባላትም ሆነ ኣባላት ያልሆኑ በአንድ አላማ በህብረት ሰሩ።

ወንጌል ሰባኪዎች በስፓኒሽ ሲያስተምሩ

በሳንቲያጎ ቺሌ የሴቶች ማደራጃ ፕሬዝዳንት በማህበረሰቧ ውስጥ የሚግኙ የሄቲ ስደተኞችን መርዳት ፍላጎት ነበራት። ክህነት ስልጣን ካላቸው አመራሮችዋ ጋር በመወያየት እሷና ሌሎች ለስደተኞቹ የስፓኒሽ ቋንቋ ለማስተማር ሃሳብ አመጡ፥ ወደ አዲሱ ቤታቸው በተሻለ መንገድ እንዲቀላቀሉ። ሁሌ ቅዳሜ ማለዳ ከሚጓጉ ተማሪዎቻቸው ጋር ሚሲናዊያን ይሰበሰባሉ ። በህንጻው ውስጥ ሰዎች ከተለያይ መነሻ በአንድነት ሲያገለግሉ ያለው አንድነት የሚያነሳሳ ምሳሌ ነው

በሜክሲኮ ያሉ ወዶ ዘማቾች

በሜክስኮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላት በምሬት መንቅጥቀጥ የተጎዱትን ለመርዳት ለብዙ ሰኣት ተጓዙ። የእጅ መሳርያ፣ ማሽኖችና፣ ለጎረቤቶቻቸው ፍቅርን ይዘው መጡ። በስብሰባ አዳርሽ ውስጥ ፍቃደኞች መመርያን ለመቀበል በተሰበሰቡ ጊዜ የዛሁታን ከተማ ከንቲባ “የኢየሱስን ንጹህ ፍቅር” ንጽብርቅን ባየ ጌዜ በእንባ ተፍነቀነቀ17

ጌታ ለኛም እድል እየሰጠን ነው በየወሩ በክህንት ስልጣን ጉባኤና በሴቶች ማደራጃ እንድንማከር፥ በአውራጃችንና በቅርንጫፎቻችን ካሊዶስኮፕ የነቁ ተሳታፊዎች እንድንሆን- ሁላችንም የምነግጥምበትና የምንፈለግበት ቦታ።

የሁላችንም መንገዶች የተለዩ ናቸው ሆኖም ሁላችንም እንሄዳችዋለን። መንገዳችን በፊት ስላደረግነው ወይም በፊት ስለነበርንብት ሳይሆን በአንድነት አሁን ስለምንሄደው፣ አሁን ስለምንሆነው ነው። በመንፈስ ቅዱስ ተመርተን ስንማከር የት እንደሆንን ማየትና የት መሆን እንዳለበን ማየት እንችላለን። ተፈጥሯዊ አይናችን ማየት የማይችለውን መንፈስ ቅዱስ እይታን ይስጣናል፥ ምክንያቱም “ራእይ በመካከላችን ስለተበተነ”18 እና ረእዮችን አንድ ላይ ስንደርግ የበለጠ ማየት እንችላለን።

በአንድነት ስንሰራ አላማችን በጌታ ፍቃድ መሆን አለበት፥ ብርታታችን ለእግዛብሔርና ለጎረቤታችን የሚሰማን ፍቅር ላይ መሆን አለበት፤19 እናም ታላቁ ፍላጎታችን “በትጋት መስራት”20 መሆን አለበት በዚህም ታላቅ ለሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ መመለሻ መንገድ እናዘጋጃለን። ይህንን ነገር የምናደርግበት ብቸኛ መንገድ “በአንድነት ብቻ” ነው።

እንደቢራቢሮዎቹ፣ እያንዳንዳችን በባህርያችንና በተውእጾችን፣ አለምን ይበልጥ ውብና ፍሬያማ ለማድረግ በመስራት፣ አንድ ትንሽ እርምጃ በተራና ከእግዚአብሔር ትእዛዛት ጋር ፍጹም በሆነ ስምምነት፣ በስምምነትና በአላም በጉዟችን እንቀጥል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ገብቶልናል በእርሱ ስም በአንድ ላይ ስንሆን በማህከላችን እንደሚሆን።21 ህያው እንደሆን እመሰክራለሁ እናም ዛሬ ጠዋትን እንደሚመስለው ጸደይ ትንሳኤን እንዳረገ። የነግስተ ነገስት ሁሉ ንጉስ ነው፥ “የንጉሶች ሁሉ ንጉስ፣ እናም የጌቶች ሁሉ ጌታ”። የነግስተ ነገስት ሁሉ ንጉስ ነው፥ “የንጉሶች ሁሉ ንጉስ፣ እናም የጌቶች ሁሉ ጌታ”።22

በመንፈስ ቅዱስ እየተመራን ከአባታችን እና ከተወዳጁ ልጁ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ ትሁቱ ጸሎቴ ነው፥ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው አሜን።