2010–2019 (እ.አ.አ)
ሁሉም ስለ ሰዎች ነው
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


2:3

ሁሉም ስለ ሰዎች ነው

ቤተክርስቲያኗ ስለእናንተ ናት፣ ስለ ጌታ ደቀመዛሙርት፣ እሱን የሚወዱ እና እርሱን የሚከተሉ እና ስሙን በላያቸው ለወሰዱ ነው።

በአስደናቂው የፓሪስ ፈረንሳይ ቤተመቅደስ ግንባታ በዝግጅት ጊዜ፣ ፈጽሞ የማልረሳው አንድ ተሞክሮ ነበረኝ። በ 2010(እ.ኤ.አ)፣ ለቤተ-መቅደስ መሬት እንደተገኘ፣ የከተማው ከንቲባ ስለ ቤተክርስቲያናችን የበለጠ ለማወቅ ከእኛ ጋር ተገናኘ። ይህም ስብሰባ የግንባታ ፈቃድ ለማግኛ ወሳኝ እርምጃ ነበር። በርካታ አስገራሚ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተ-መቅደሶችን ምስል ያካተተ ሀተታ በጥንቃቄ አዝርጋጀን። የእኔ ከፍተኛ ተስፋ የነበረው የፕሮጀክቱን መርሃግብር ለመደገፍ የስነ ሕንፃዎቹ ውበት የከተማ ከንቲባውን ለማሳመን ነበር።

የሚገርመው ነገር የከተማው ከንቲባው አቀራረባችንን ከመገምገም ይልቅ እርሱና ጓደኞቹ እኛ ምን አይነት ቤተክርስቲያን እንደሆንን ለማወቅ የራሳቸውን ምርመራ ለማድረግ እንደመረጡ ገለጸልኝ። በቀጣዩ ወር፣ የከተማው አማካሪ እንዲሁም የሃይማኖታዊ ታሪክ ፕሮፌሰር በሆነች ሪፖርት እንድንሰማ ተጋበዝን። እንዲህ አለች፣ “ከሁሉም በላይ የቤተክርስቲያናችሁ አባላት ማን እንደነበሩ መረዳት ፈልገን ነበር። መጀመሪያ፣ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎቻችሁ ውስጥ ተካፍለናል። ከስብሰባው በስተጀርባ ተቀምጠን በጉባኤ ውስጥ ያሉትን ሰዎች እና ምን እያደረጉ እንደነበር በጥንቃቄ ተመለከትን። ከዚያም ከካስማችሁ ዙሪያ የሚኖሩትን ጎረቤቶች ሰዎች ጋር ተገናኘን፣ ከዚያም ሞርሞኖች ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆናችሁ ጠየቅን።

“ስለዚህ መደምደሚያችሁ ምንድነው?” ትንሽ በመጨነቅ ስሜት ጠየኩኝ። እሷም እንዲህ መለሰች፣ “የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከምናውቃቸው ከሌሎች ቤተክርስቲያናት ሁሉ በበለጠ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዋናው ቤተክርስቲያን ጋር እጅግ በጣም በቅርብ የተገናኘ መሆኑን ነው።” “ይህ ሙሉ በሙሉ ትክክለኛ አይደለም!” በማለት ለመቃወም ቀርቤ ነበር። “በጣም ቅርብ የሆነችው ቤተክርስቲያን አይደለችም፤ ግን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናት፣ አንድ አይነት ቤተክርስቲያን፣ እናም እውነተኛው ቤተክርስቲያን ናት! “ግን እራሴን በመግታት እናም በፀጥታ የምስጋና ጸሎት አቀረብኩኝ። ባቀረቡት ግኝት መሰረት እርሱ እና ጓደኞቹ በአካባቢያቸው ውስጥ ቤተመቅደስ ለመገንባት ምንም ተቃውሞ እንደሌላቸው ከንቲባው ገለጸ።

ዛሬ ስለዛ ተአምራዊ ተሞክሮ ሳስብ፣ ለከንቲባው ጥበብ እና የማስተዋል መንፈስ አመስጋኝ ነኝ። ቤተክርስቲያኗን ለመረዳት ቁልፉ በውጫዊው ሕንፃዎቹ ወይም ጥሩ በደንብ የተደራጀ ተቋም መሆኑን በማየት እንዳልሆነ ያውቅ ነበር ነገር ግን በየቀኑ የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ ለመከተል የሚጥሩ በሚልዮን በሚቆጠሩ ታማኝ አባላት በኩል ነው።

የቤተክርስቲያኗ ፍቺ ከመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ እንዲህ ከሚለው አንቀፅ ሊወሰድ ይችላል፣ “እና እነርሱም [የጌታን ደቀ መዛሙርት ] በኢየሱስ ስም የተጠመቁ፣ የክርስቶስ ክርስቲያናት ተብለው ተጠርተዋል።”1

በሌላ አነጋገር፣ ቤተክርስቲያኑ ስለ ሰዎች ነው። ስለእናንተ ነው፣ ስለ ጌታ ደቀመዛሙርት፣ እሱን የሚወዱ እና እርሱን የሚከተሉ እና ስሙን በቃልኪዳን በላያቸው ለወሰዱ ነው።

ፕሬዘደንት ራስል  ኤም ኔልሰን አንድ ጊዜ ቤተክርስቲያኗን ከጥሩ መኪና ጋር አመሳስለውታል። ሁላችንም መኪናችን ንጹህና የሚያንጸባርቅ ሲሆን እንወዳለን። ይሁን እንጂ የመኪናው ዋናው አላማ ማራኪ ማሽን መሆን አይደለም፣ ሰዎችን በመኪናው ውስጥ ማንቀሳቀስ ነው።2 በተመሳሳይ ሁኔታ፣ እኛ፣ እንደ ቤተክርስቲያኗ አባላት፣ ንፁህ እና በጥሩ ሁኔታ የተያዙ የሚያምሩ የአምልኮ ቦታዎች መኖራቸውን እናደንቅአለን እንዲሁም በጥሩ ሁኔታ የሚተገብር ፕሮግራም አለን። ነገር ግን እነዚህ ድጋፍ ሰጪ ስርዓቶች ናቸው። ዋናው አላማ የእያንዳንዱ ወንድ እና ሴት ልጅ ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ከመጋበዝ እና ወደ ቃል ኪዳኑ መንገድ ለመምራት ነው። ምንም የተሻለ አስፈላጊ ነገር የለም። ስራችን ስለ ሰዎች እና ቃል ኪዳኖች ነው።

በዳግም ከተመለሰችው ቤተክርስቲያን በተገለጠው ራእይ ውስጥ የተሰጠው ስም በእያንዳንዱ የወንጌል ኪዳን ውስጥ ያሉትን ሁለት ዋና ዋና ነገሮች አንድ ላይ ማዋሃዱ አያስደንቅምን? የመጀመሪያው የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው። እርሱ የቤተክርስቲያኑ አናት ነው እና የተቀደሰው የኃጢያት ክፍያውና ቃል ኪዳኑ ለመዳን እና ከፍ ከፍ ለመደረግ ብቸኛው መንገድ ናቸው። ሁለተኛው ስም እኛን የእርሱን ምሥክሮች እና የእርሱን ደቀ-መዛሙርቶች ያመለክታል።

በፈረንሳይ እንደ ካስማ ፕሬዘዳንት ሳገልለግል በሰዎች ላይ የማተኮርን አስፈላጊነት ተማርኩ። በአገልግሎቴ መጀመሪያ ላይ፣ በጣም በተስፋ የተሞሉ ግቦች ለካስማው ነበረኝ፣ አዳዲስ አጥቢያዎችን መክፈት፣ አዳዲስ የመሰብሰቢያ ቤቶችን መገንባትንና በአካባቢያችን ቤተመቅደስን እንኳን መገንባት ነበር። ከስድስት ዓመታት በኋላ ከሃላፊነቴ ከወረድኩኝ በኋላ ከእነዚህ ዓላማዎች መካከል አንዱም አልተሟላም። ይህም ያለመሳካት ስሜት ሊሰማ ይችላል፣ ነገር ግን በስድስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የእኔ ዓላማዎች በጣም የተቀየሩ ነበሩ።

ከጥሪዬ የወረድኩኝ ቀን ከመናገሪያው ቆሜ ሳለሁ ጥልቅ የምስጋናና ስኬታማነት ስሜት ተሰማኝ። በስብሰባው ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላትን ፊትን ተመለከትኩኝ። ከእያንዳንዳቸው ጋር የተቆራኘን የመንፈሳዊ ተሞክሮን ማስታወስ እችላለሁ።

ወደ ቤተክርስቲያኑ ቅዱስ ስነስርዓቶችን ለመቀበል ወደ እነዚያ የጥምቀት ውሀ የገቡ፣ ወደ ቤተመቅደስ እንዲገቡ የመጀመሪያ ፍቃዳቸውን የፈረምኩላቸው፣ እናም እነዚያን ወጣት እና ባለትዳር ለሙሉ ጊዜ ሚሲዮን የለየኋቸው እናም ሲጨርሱ ያሰናበትኳቸው ወንድሞች እና እህቶች ነበሩ። በሕይወታቸው ውስጥ ፈተናዎችንና መከራዎችን ሲያጋጥሟቸው ያገለገልኳቸው ብዙ ሌሎች ነበሩ። ለእያንዳንዳቸው ከፍተኛ ወንድማዊ ፍቅር ተሰማኝ። እነሱን በማገልገል ንጹህ ደስታን አግኝቻለሁ እናም ወደ አዳኝ ባሳዩት ታማኝነት እና እምነት ተደሰትሁ።

ፕሬዘደንት ኤም  ራስል ባላርድ እንዳስተማሩት “በቤተክርስቲያናችን ሃላፊነቶች ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነው ነገር ሪፖርት የተደረጉ አኃዞች ወይም የምናደርጋቸው ስብሰባዎች አይደሉም ነገር ግን አዳኝ እንዳደረገው አንድ በአንድ የተገለገሉ፣ ከፍ የተደረጉትን እና ተበረታተው በመጨረሻም የተቀየሩትን ግለሰቦችን ነው።”3

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በወንጌል ውስጥ ንቁ ተሳትፊ ነን፣ ወይስ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ በስራ ብቻ የተጠመድን ነን? ቁልፉ በሁሉም ነገሮች የአዳኝን ምሳሌ መከተል ነው። እንዲህ ካደረግን፣ ተግባራትን ከማከናወንና መርሃግብሮችን ከማስቀደም ይልቅ ግለሰቦችን በመርዳት ላይ እናተኩራለን።

አዳኝ በቀጣዩ እሁድ የእናንተን አጥቢያ ወይም ቅርንጫፍ ቢጎበኝ ምን ሊሆን እንደሚችል እራሳችሁን ጠይቃችኋል? ታዲያ ምን ያደርግ ይሆን? የምስል እቃዎቹ ጥሩ እንደሆኑ ወይም ወንበሮቹ በክፍል ውስጥ በትክክል መቀመጣቸውን ለማወቅ ይጨነቅ ይሆን? ወይስ ሊወደው፣ ሊያስተምረው እና ሊባርከው የሚችል ሰውን ይፈልጋል? ምናልባት ሊያመጣው የሚችለውን አዲስ አባል ወይም ጓደኛ፣ መጽናኛ የሚያስፈልገውን የታመመ ወንድም ወይም እህት፣ ወይም ከፍ ሊደረግ የሚችል እና ሊበረታታ የሚችልን የሚወላውል ወጣት ልጅን ይፈልጋል።

ኢየሱስ የሚጎበኘው ክፍልስ የትኛው ነው? የህጻናት ልጆች ክፍልን በመጀመሪያ ለመጎብኘት ቢመጣ አይገርመኝም። ምናልባትም ተንበርክኮ ዓይን ለዓይን ያነጋግራቸዋል። ለእነሱ ፍቅሩን ይገልጽላቸዋል፣ ታሪኮችን ይነግራቸዋል፣ በሳሉት ስዕሎቹ ላይ ማበረታቻን ይሰጣቸዋል፣ እና ስለሰማይ አባቱ ይመሠክራል። የእርሱ አመለካከት ቀላል፣ እውነተኛ እና ስሜታዊ ያልሆነ ይሆናል። እኛስ እንዲህ ማድረግ እንችላለን?

በጌታ አጀንዳ ላይ ለመሳተፍ በምትሞክሩበት ጊዜ፣ ልታግዟቸው እና ልትረዷቸው የምትችሏቸውን ሰዎች ከማግኘት የበለጠ ምንም ነገር አይኖራችሁም ብዬ ቃል እገባላችኋለሁ። በቤተክርስቲያንም ውስጥ ግለሰቦችን በማስተማር እና ልባቸውን በመንካት ላይ ታተኩራላችሁ። የሚያሳስባችሁ ነገር፣ እናንተ ያደረጋችሁትን ጉብኝቶች ቁጥር ሳጥኑ ላይ ምልክት ከማድረግ ይልቅ አባላትን ማገልገል፣ ፍጹም የሆነ ዝግጅቶችን ከማቀናጀት ይልቅ መንፈሳዊ ተሞክሮን ማሳደግ ይሆናል። ስለ እራሳችሁ ሳይሆንነገር ግን ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ብለን ስለምንጠራቸው ስለእነርሱ ይሆናል።

አንዳንድ ጊዜ ወደቤተክርስቲያን ስለመሄድ እናወራለን። ነገር ግን ቤተክርስቲያን ከሕንፃ ወይም ከተወሰነ ቦታ በላይ ነው። በሶልት ሌክ ሲቲ ባለው ቤተክርስትያኗ በዋናው ጽፈት ቤት እናዳለው ሁሉ በጣም ርቀው በሚገኙ የዓለማችን አካባቢዎችም ጭምር እውን እና ህያው ነው። ጌታ ራሱ እንዲህ አለ፤ “ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።”4

በምንሄድበት ሁሉ ወደ ስራ፣ ወደ ትምህርት ቤት፣ የእረፍት መዝናኛ እና በተለይም በቤታችን ቤተክርስቲያችንን አብረን እንወስዳለን። መገኘታችን እና ትፅዕኖአችን በምንሄድበት ቦታ ሁሉ ቅዱስ ለማድረግ በቂ ይሆናል።

አንድ የእምነታችን አባል ካልሆነ ጓደኛዬ ጋር የነበረንን ውይይት አስታውሳለሁ። በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ብቁ ወንድ ክህነትን ለመቀበል መቻሉ አስገረመው። እንዲህ ብሎ ጠየቀ፣ “በአጥቢያክ ውስጥ ስንት የክህነት ተሸካሚዎች አሉ?”

እኔም “ከ 30 እስከ 40 የሚጠጉ” ብዬ መለስኩለት።

በመደነቅ ቀጠለ፣ “በቤተክርስቲያናችን ውስጥ አንድ ቄስ ብቻ ነው ያለን። እሁድ ጠዋት ላይ ብዙ ቄሶች ለምን ያስፈልጓችኋል?“

በጥያቄው በመገረም፣ እንዲህ በማለት ለመመለስ ምሪት ተቀበልኩ “እኔ ካንተ ጋር እስማማለሁ። እሁድ በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ የክህነት ተሸካሚዎች ያስፈልጉናል ብዬ አላስብም። ነገር ግን በእያንዳንዱ ቤት የክህነት ተሸካሚ ያስፈልገናል። እና በአንድ ቤት ውስጥ ምንም ክህነት በማይኖርበት ጊዜ፣ ሌሎች የክህነት ተሸካሚዎች ይህን ቤተሰብ ለመጠበቅ እና ለማገልገል ይጠራሉ።”

ቤተክርስቲያናችም የሰንበት ብቻ አይደለም። አምልኳችን በሳምንቱ ውስጥ በየቀኑ ይቀጥላል፣ በየትኛውም ቦታ እና በምንሰራው ስራ ይቀጥላል። በተለይም ቤቶቻችን “የእምነታችን ዋነኛ መቅደሶች ናቸው።”5 ቤታችን ውስጥ በአብዛኛው የምንጸልየው፣ እንባርካለን፣ እናጠናለን፣ የእግዚአብሔርን ቃል እናስተምራለን፣ እና በንጹህ ፍቅር እናገለግላለን። ከግል ተሞክሮ በመነሳት ቤቶቻችን ልክ እንደ አምልኮ ቦታዎቻችን ፣ አንዳንዴም በተሻለ ሁኔታ የመንፈስ ማደሪያ መሆናቸውን መመስከር እችላለሁ።

ይህ ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደሆነች እመሰክራለሁ። ጥንካሬዋ እና ብርታቷ የሚመጣው በየቀኑ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ደቀመዛሙርቱ በሚወስዷቸው እርምጃዎች እና በየቀኑ ሌሎችን በመንከባከብ የእሱን የላቀ ምሳሌ በሚከተሉት ነው። ክርስቶስ ህያው ነው እናም ይህችን ቤተክርስቲያን ይመራል። ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በዘመኖቻችን እንዲመሩን የመረጣቸው ነቢይ ናቸው። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. 3 ኔፊ 26፥21

  2. ራስል  ኤም. ኔልሰን (general conference leadership meeting, Apr. 2012) ተመልከቱ።

  3. ሩሰል ኤም ኔልሰን፣ “እነሆ ጠቢብ ሁኑ ,” Liahona, ህዳር 2006 (እ.አ.አ.)፣ 20።

  4. ማቴዎስ 18፥20

  5. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “The Doctrinal Importance of Marriage and Children” (worldwide leadership training meeting, Feb. 2012), broadcasts.lds.org.