2010–2019 (እ.አ.አ)
የቤተክርስቲያኗ ተወካዮች
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


15:22

የቤተክርስቲያኗ ተወካዮች

እንደ ቤት ለቤት አስተማሪነታችሁ ለልጆቹ መልእክተኞች እንድትሆኑ፣ የተመደባችሁትን ሰዎች እንድትወዱ እና እንድትንከባከቡ እና እንድትፀልዩ እየጠየቅናችሁ ነን።

ከጥቂት ጊዜ በፊት ሞሊ ብዬ የምጠራት ያላገባች ሴት፣ ከስራ ወደ ቤት ስትመለስ የምድር ቤት ወለሉ ሁለት ኢንች (5 ሴንቲ ሜትር) በሚሆን ውሀ ተሸፍኗል። ወዲያው የፍሳሽ መስመሩን የምትጋራቸው ጎረቤቶቿ ከመጠን በላይ የሆነ የልብስ እጥበት እና ሻወር እንደተጠቀሙ ተረዳች ምክንያቱም ያገኘችው እጣቢ ውሀ ስለነበረ።

ጓደኛዋ እንድትመጣ እና እንድትረዳት ከጠራቻት በኋላ፣ ሁለቱ ውሃውን ማድረቅ እና መወልወል ጀመሩ። ወዲያው የበሩ መጥሪያ ጮኅ። ጓደኛዋ ጮክ ብላ፣ “የቤት ለቤት አስተማሪዎችሽ ናቸው!” አለች።

ሞሊ ሳቀች። “የወሩ የመጨረሻ ቀን ነው ፣” ብላ መለሰችላት፣ “ግን የቤት ለቤት አስተማሪዎቼ እንዳልሆኑ አረጋግጥልሻለሁ።”

ባዶ እግሯን፣ በእርጥብ ሱሪ፣ ፀጉሯ በመያዣ ወደ ላይ ሆኖ፣ እና በጣም ዘመነኛ የሆኑ የላስቲክ ጓንቶች አድርጋ፣ ሞሊ ወደ በሩ አቀናች። ነገር ግን የእርሷ የአግርሞት አመጣጥ በአይኖቿ ፊት ካለው ገፅታ በላይ አስገራሚ አልነበረም። እነዚህም የቤት ለቤት አስተማሪዎቿ ነበሩ!

“በፓምፕ ብትመታኝ ትችል ነበር!” ብላ በኋላም ነገረችኝ። “ይሄ የቤት ለቤት ትምህርት ተአምር ነው፣ ወንድሞች በአጠቃላይ ጉባኤ ወቅት የሚያወሩለት አይነት!” እንዲህም ቀጠለች፥ “ከዛ ግን፣ ለመሳም ወይም መወልወያውን ላቀብላቸው እያመነታሁ ሳለሁ፣ እንዲህ አሉ፣ ‘ኦ ሞሊ፣ በጣም ይቅርታ። በስራ መጠመድሽን ማየት ችለናል። ልንረብሽሽ አንፈልግም፤ ስለዚህ ሌላ ጊዜ እንመጣለን።’ እናም ሄዱ።”

“ማን ነበር?” ብላ ጓደኛዋ ከታች ጠየቀች።

“‘በእርግጥም ሶስቱ ኔፋውያን አይደሉም፣’ ማለት ፈልጌ ነበር” ብላ ሞሊ አመነች፣ “ነገር ግን እራሴን ገታሁ እና ረጋ ባለ ድምፅ እንዲህ አልኩ፣ ‘የቤት ለቤት አስተማሪዎቼ ነበሩ፣ ግን መልእክታቸውን ለማስተላለፍ አመቺ ጊዜ መስሎ አልተሰማቸውም።’”1

ወንድሞች፣ እንደ “ቤተክርስቲያኗ የእርዳታ የመጀመሪያ መንጭ”2 ተብሎ ስለሚታወቀው የክህነት ሀላፊነትን እንመርምር። ይህን ለማደራጀት እና በዳግም ለማደራጀት ብዙ ወረቀቶች በጥቅም ላይ ውለዋል። ያንን ለማበረታታት አንድ ሺ የሚሆን አነቃቂ ንግግሮች ተደርገዋል። በእርግጥም ይህ ርእስ ያነሳሳቸውን ፀፀታዊ ጉዞዎች የትኛውም የፍሬውድ የጉዞ ወኪል አያዘጋጀውም። ነገር ግን አሁንም በክህነት የቤት ለቤት ትምህርት “ሁሌም ቤተክርስቲያኑን ለመጠበቅ”3 የተሰጠውን የጌታ ትእዛዝ ተቀባይነት ባለው መልኩ ለመወጣት እየታገልን ነው።

ከሚያጋጥሙን ችግሮች አንዱ ክፍል የቤተክርስቲያኑ ተለዋዋጭ የቦታ አቀማመጥ ነው። አባላቶቻችን በ188 ሀገሮች እና መዳረሻዎች ውስጥ በሚገኙ፣ ወደ 30,000 አጥቢያዎች እና ቅርንጫፎች ተበትነው በመገኘታቸው፣ “ዝግ ትምህርት” በሚባለው ጎረቤት ጎረቤቱን ከሚያስተምርበት የቀድሞ የቤተክርስቲያን ሂደት፣ አሁን የወንድሞቻችንን እና የእህቶቻችንን ለመጎብኘት በበለጠ አስቸጋሪ እንደሆነ እናውቃለን።

በተጨማሪም፣ በቤተክርስቲያኑ አብዛኛው አጥቢያዎች ውስጥ፣ የቤት ለቤት ትምህርትን ለማካሄድ ጥቂት የክህነት ተሸካሚዎች ብቻ ይገኛሉ—ያም ማገልገል የሚችሉትን እስከ 18 ወይም 20 ቤተሰቦችን እንዲንከባከቡ ይተውላቸዋል። እረጅም ርቀት መጓዝ፣ የትራንስፖርት ውድ መሆን እና አለመገኘት፣ እናም የሚጨምረው የየአከባቢው የቀን እና የሳምንት የስራ ሰአት ተጨማሪ ችግሮች ሊሆኑ ይችላሉ። በዚህ ላይ ጨምረን ያለ ግብዣ የቤት ጉብኝትን የማይፈቅዱ ባህላት እና በአብዛኛው የአለም አከባቢዎች ያለውን የደህንነት ችግር ስናስብ—እንግዲህ፣ የችግሩን ውስብስብነት ማየት እንጀምራለን።

ወንድሞች፣ በአለም በተሻለ ሁኔታ ሁሉ እና ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ውስጥ፣ ወርሀዊ የቤት ለቤት ጉብኝት አሁንም ቤተክርስቲያኗ ለማድረግ የምትጥረው ተፈላጊው ነገር ነው። ነገር ግን በብዙ የአለም ቦታዎች ውስጥ እንደዛ አይነት ተፈላጊ ነገርን ማሳካት የማይቻል መሆኑን በማስተዋል እና በእውነት መከናወን የማይችልን ነገር እንዲያደርጉ ስንጠይቅ ወንድሞች ያለመቻል አይነት ስሜት እንዲሰማቸው ምክንየት እንሆናለን፣ የቀዳሚ አመራር ለክህነት መሪዎች በታህሳስ 2001 (እ.አ.አ) ይህንን የሚያነሳሳ፣ አጋዥ ምክር ፃፉ፤ “በአንዳንድ የቤተክርስቲያኗ ቦታዎች… በቂ ቁጥር ያላቸው የክህነት ተሸካሚዎች ስለሌሉ እና በብዙ የአከባቢ ችግሮች አማካኝነት የቤት ለቤት ትምህርት በየወሩ ማካሄድ የማይቻል ነው” ብለው ጽፈዋል። አንዳንዶቹን ጠቅሰናል። “እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ፣ መሪዎች እያንዳንዱን አባል ለመጠበቅ እና ለማጠንከር ያላቸውን ግብአት ለመጠቀም የተቻላቸውን ማድረግ አለባቸው”4 ብለው ቀጠሉ።

ወንድሞች፣ በእኔ አጥቢያ ወይም ቅርንጫፍ ይህን መሰል አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙኝ፣ የእኔ የአሮናዊ ክህነት አጋሬ እና እኔ የቀዳሚ አመራር ምክርን (አሁን የሀንድቡክ መመሪያ የሆነውን) በዚህ መልኩ እንተገብረዋለን፤ መጀመሪያ፣ ለማከናወን ምንም ያህል ብዙ ወራት ቢፈጅ፣ “የእያንዳንዱን አባል ቤት ጎብኙ፣”5 የሚለውን የቅዱስ መፅሐፍ መመሪያ እንገፋበታለን፣ በሚቻለው እና በሚተገበር መልኩ የጊዜ መዋቅን በማዘጋጀት። በዛ ሂደት ውስጥ፣ እኛ በይበልጥ ለምናስፈልጋቸው ለመድረስ ያለውን ሰአት እና የመከታተል ጊዜ ለመጠቀም በከፍተኛ ደረጃ ቅድሚያ እንሰጣለን—ሚስኦናውያን እያስተማሯቸው ያሉትን አዲስ ሰዎች፣ በቅርቡ የተጠመቁ አባላትን፣ የታመሙትን፣ ብቸኛ የሆኑትን፣ ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑትን፣ በቤታቸው አሁንም ልጆች ያላቸው የብቸኛ ወላጅ ቤተሰቦች፣ እና የመሳሰሉት።

ቤቶችን በመጎብኘት የጊዜ መዋቅራችንን ስንሰራበት፣ ለማሳካት ጥቂት ሳምንታትን ሊወስድ ይችላል፣ ጌታ ያዘጋጀልንን የትኛውንም ግብአቶች በመጠቀም ግለሰቦችን እናም ቤተሰቦችን በሌላ የመገናኛ መንገዶች እንደርሳለን። በእርግጥም ቤተሰቦቻችንን በቤተክርስቲያን እንጠብቃለን፣ እናም ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚሉት፣ “ስለነፍሳቸው ደህንነት አንዱ ከሌላ ጋር ይነጋገራሉ።”6 በተጨማሪም፣ በስልክ እንደወላለን፣ ኢሜል እና የስልክ መልእክት እንልካለን፣ እንዲሁም በህብረተሰብ መተላለፊያዎች መልእክት እንልክላቸዋለን። ልዩ ፍላጎቶችን ለማሟላት፣ የቅዱስ መፅሐፍ ጥቅስ ወይም ከአጠቃላይ ጉባኤ ንግግር አንድ መስመር ወይም በ LDS.org ከሚገኘው የተትረፈረፉ መረጃዎች የሞርሞን መልእክት እንልክላቸው ይሆናል። በቀዳሚ አመራር አነጋገር፣ በሚያጋጥሙን ሁኔታዎች ውስጥ ያሉንን ግብአቶች በመጠቀም የምንችለውን እናደርጋለን።

ወንድሞች፣ በዚህ ምሽት የምለምነው ስለቤት ለቤት ትምህርት ያላችሁ እይት ከፍ እንዲል ነው። እባካችሁ በአዲስ በተሻሻለ መንገድ ለልጆቹ እንደተላካችሁ የጌታ መልእክተኞች ራሳችሁን ተመልከቱ። ያም ማለት እንደ ሙሴ ህግ፣ ልክ የወሩ መጨረሻ ላይ በችኮላ ቤተሰቡ ቀድመው ካነበቡት የቤተክርስቲያን መፅሔት ላይ መልክት የምትሰጡን፣ ወጣ ያለውን ባህል ወደኋላ መተው ነው። በምትኩ ቀና የሆነ፣ በወንጌል ላይ ባተኮረ መልኩ ለአባላት በማሰብ፣ በርህራሄ መንገዶች አንዱ እንዱን በመጠበቅ እና በመንከባከብ፣ በተቻለው መንገድ ሁሉ የመንፈሳዊውን እና ጊዜአዊ ፍላጎቶች የሚሟሉበትን ወቅት እንደምትመሰርቱ ተስፋ እናደርጋለን።

አሁን፣ እንደ የቤት ለቤት ትምህርት “የሚቆጠረውን” አስመልክቶ፣ የምታደርጓቸው መልካም ነገሮች ሁሉ “ይቆጠራሉ”፣ ስለዚህ የሁሉንም ሀተታ አቅርቡ! በእርግጥም፣ የበለጠ ትርጉም ያለው በወኪልነታችሁ ውስጥ ያሉትን ምን ያህል እንደባረካችሁ እና መንከባከባችሁ ነው፣ ያ ደግሞ ከጊዜ መቁጠሪያ እና ከተለየ ቦታ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። በይበልጥ ትርጉም ያለው ሰዎቹን መውደዳችሁ እና “ሁሌም ቤተክርስቲያኗን ጠብቁ”7 የሚለውን ትእዛዝ ማሟላታችሁ ነው።

ባለፈው አመት ግንቦት 30 ላይ፣ ጓደኛዬ ትሮይ ሩሴል በአቅራቢያው ለሚገኙ የዴዘረት ድርጅቶች እቃዎችን ለመለገስ ከኋላ መጫኛ ያላት መኪናውን ከጋራዥ ውስጥ በዝግታ አወጣት። የኋለኛው ጎማ ጉብታ ላይ እንደወጣ ተሰማው። ከመጫኘው ላይ የሆነ እቃ ወድቋል ብሎ በማሰብ፣ ሲወጣ ያገኘው የዘጠኝ አመት ልጁ ኦስትን የድንጋይ ንጣፉ መንገድ ላይ ፊቱ ተዘቅዝቆ ወድቆ ነበር። ጩኸቶቹ፣ የክህነት ቡራኬው፣ የህክምና እርዳታ ቡድኑ፣ እና የሆስፒታል ሰራተኞቹ በዚህ ሁኔታ አልጠቀሙም። ኦስትን ህይወቱ አልፏል።

መተኛት ወይም ሰላም ማግኘት ሳይችል፣ ትሮይ ከልቡ አዝኖ ነበር። መሸከም ከሚችለው በላይ እንደነበር እና መቀጠል እንደማይችል ተናገረ። ነገር ግን በዛ መሪር ጊዜ ሶስት አዳኝ ሀይሎ መጡ።

መጀመሪያ የሰማይ አባታችን አፍቃሪ አፅናኝ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ነበር፣ በመንፈስ ቅዱስ መኖር አማካኝነት ትሮይ ተጽናና፣ የሚያምር እና ፍፁም ልጅን ስለማጣት ሁሉንም ነገር እግዚአብሔር እንደሚያውቅ አስተማረው፣ እናም አፈቀረው። ሁለተኛ ደግሞ ሚስቱ ነበረች፣ ዲድራ፣ ተሮይን በእጆቿ ይዛ እና በፍቅር እሷም ልጇን እንዳጣች በማስታወስ እና ባሏንም ማጣት እንደሌለባት በቁርጠኝነት አሳወቀችው። በዚህ ታሪክ ውስት ሶስተኛው፣ ድንቅ የሆነው ቤት ለቤት አስተማሪው ጆን ማኒንግ ነው።

በየትኛው የጊዜ መዋቅር ጆን እና ታናሽ አጣማሪው የሩሴልን ቤት እንደጎበኙ ወይም እዛ ሲደርሱ መልእክታቸው ምን እንደነበር፣ ወይም ተሞክሯቸውን እንዴት እንዳሳወቁ አላውቅም። የማውቀው ነገር ባለፈው ፀደይ ልክ ትሮይ ሩሴል ትንሹን ኦስትንን እንዳነሳው፣ እርሱን ደግሞ ወንድም ማኒንግ ከመንገዱ አደጋ ደርሶ ከፍ እንዳደረገው ነው። መሆን እንደነበረበት የቤት ለቤት አስተማሪ ወይም ጠባቂ ወይም በወንጌል ውስጥ ወንድምነት፣ ጆን በቀላሉ የክህነት ድርሻውን ወሰደ እና ተሮይ ሩሴልን ተበቀው። እንዲህ በማለት ጀመረ፣ “ትሮይ፣ ኦስትን ዳግም እንድትቆም ይፈልጋል—የቅርጫት ኳስ ሜዳው ላይ ጨምሮ—ስለዚህ ሁሌ ጠዋት 11፡15 ላይ እዚህ እገኛለሁ። ተዘጋጅተህ ጠብቀኝ ምክንያቱም ወደ ውስጥ ገብቼ ላስነሳህ አልፈልግም— እናም ዲድራም ያንን እንደማትፈልግ አውቃለሁ

ከዛም ቆይቶ ትሮይ እንዲህ አለኝ፣ “መሄድ አልፈለኩም ነበር ምክንያቱም ሁሌ በእነዛ ጠዋቶች ኦስተንን ነበር ይዤ የምሄደው እና ትውስታዎቹ በጣም እንደሚያሙ አውቅ ነበር። ነገር ግን ጆን ግድ ነው አለ፣ ስለዚህ ሄድኩ። ከዛ የመጀመሪያ ቀን በኋላ፣ አወራን—ወይም እኔ አወራሁ—እናም ጆን አዳመጠኝ። ወደቤተክርስቲያን እስክንደርስ ያለውን መንገድ እናም ከዛ እስከቤት ድረስ እኔ ሳወራ ነበር። አንዳንዴ በመንገዱ ላይ አቁመን ፀሀይ በላስቬጋስ ላይ ስትወጣ እየተመለከትን አወራሁ። መጀመሪያ ላይ ከባድ ነበር፣ ነገር ግን ከጊዜ በኋላ በህይወቴ ዳግም ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ እኔን በወደደኝ እና ባዳመጠኝ፣ በጣም ዝግተኛ የሆነ 1.88 ሴቲ ሚትር ረጅምነት ያለው የቤተክርስቲያን ኳስ ተጫዋች እና ማራኪ ያልሆነ የዝላይ ውርወራዎች ባለው ሰው ጥንካሬዬን እንዳገኘው አስተዋልኩ።”8

የክህነት ወንድሞቼ፣ ስለ የቤት ለቤት ትምህርት ወይም እንክብካቤ ወይም የግል የክህነት አገልግሎት ስናወራ—ምንም ብላችሁ ጥሩት—እያወራነው ያለነው ይሄንን ነው። እንደ ቤት ለቤት አስተማሪነታችሁ ለልጆቹ የእግዚአብሔር መልእክተኞች እንድትሆኑ እየጠየቅናችሁ ነው፣ እኛ ለእናንተን እንደምንወድ፣ እንደምናስብላችሁ እና እንደምንፀልይላችሁ፣ እናንተም ሰዎቻችሁን እንድትወዱ እና እንድትንከባከቡ እና እንድትፀልዩ። በየሁኔታዎቻችሁ ቀጣይነት ባላቸው መንገዶች የእግዚአብሔር መንጋዎችን እንድትጠብቋቸው እናም እንድታጠንክሯቸው ፀሎቴ ነው፣ በሁላችንም መልካም እረኛ፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።