2010–2019 (እ.አ.አ)
ታላቁ የመዳን ዕቅድ
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


11:8

ታላቁ የመዳን ዕቅድ

I know that when we sincerely repent of our sins, they are truly gone—without a trace!

ፕሬዘደንት ቦይድ ኬ. ፓከር ከመሞታቸው ከጥቂት ወራት በፊት ጠቅላላ የክህነት ባለስልጣን እና መሪዎች ለእኛ እንዲናገር ድንቅ እድል ነበራቸው። ስለተናገረው ነገር ማሰቤን ማቆም አልቻልኩም። እሱ ወደኃላ በህይወት ጊዜው በመመልት የሰራቸውን ሀጢያቶች እና ንሰሀ የገባባቸውን እናም የነሱን ኮቴ ማግኘት የማይችላቸውን ሲፈልግ እንደነበረ አካፈለን። በተወዳጁ አዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ አማካኝነት እና በእውነተኛ ንሰሀ አማካኝነት የእሱ ሀጢያቶች ልክ እንዳልተከሰቱ ሙሉ ለሙሉ አልነበሩም። ፕሬዘደንት ፓከር ከዚያም እንደ መሪዎች በልብ ንስሀ ለሚገቡ ይህ ህጉ እንደሆነ እንድንመሰክር በዚያ ቀን ሀላፊነት ሰጡን።

ከብዙ አመታት በፊት በአለማዊ መተላለፍ ውስጥ ስለነበር አንድ ሰው አውቃለሁ። ለተወሰነ ጊዜ ይህ ሰው ሚስቱን እና የክህነት ስልጣን መሪዎቹን ለማናገር የውርደት ስሜት ይሰማው ነበር። ሙሉ ለሙሉ ንሰሀ መግባት ይፈልግ ነበር ነገር ግን እሱ በመናዘዙ ምክንያት ባለቤቱን እና ልጆቹን በሰቀቀን፣ እፍረት እና ሌሎች መንስኤዎች ውስጥ ከሚያደርጋቸው ይልቅ የራሱን ዘላለማዊ ደህንነት ቢያጣ እንደሚሻለው እርግጡን ገለፀ።

ሀጢትን ስንሰራ ባብዛኛው ጊዜ ሴጣን እኛ እረስወዳድ ያልሆነ ነገር ማድረግ የምንችለው ሌሎች የኛን ሀጢያት አውቀው ከመደንገጥ መጠበቅ እና ለኤጲስ ቆጶስ፤ የእኛን ህይወት ካለው የክህነት ስልጣን ቁልፍ መባረክ ከሚችለው እንደ እስራኤል ፈራጅ ከመናዘዝ መቆብ እንደሆነ ሊሳምነን ይጥራል። ሆኖም ግን እውነታው እራስወዳድ ያልሆነው እና ክርስቶሳዊ ባህሪ ነገር ማድረግ ያብን መናዘዝ እና ንሰሀ መግባት ነው። ይህ የሰማይ አባት ታላቁ የመዳን እቅድ ነው።

በመጨረሻም፣ ይህ ውድ ሰው ታላቅ የሆነ ፀፀትን በመግለፅ ሀጢያቱን ለሚስቱና ለቤተክርስቲያን መሪዎቹ ተናዘዘ። ምንም እንኳ ከባድ ነገር ቢሆንም ያደረገው የመቅለል፣ የሰላም፣ የፍቅር እና ለአዳኛችን የማመስገን ስሜት እና ጌታ ከፍተኛውን ሸክሙን እንዳነሳለት እናም እሱን መሸከሙ መግለፅ ከሚቻለው በላይ ሀሴትን ይፈጥራል፤ ውጤቱ ወይም የወደፊት ህይወቱ ምንም እንኳ ቢሆን።

አዳኝ ሲያፅናና

ሚስቱ እና ልጆቹ እንደሚጎዱ እርግጠኛ ነበረ—እናም ነበሩ፤ እናም ማረሚያ ይኖራል እንዲሁም ከጥሪው መውረድ—እናም ነበረ። ባለቤቱ ልቧ እንደሚሰበር፣ እንደምትጎዳ፣ እንደምትበሳጭ እርግጠኛ ነበር—እናም ነበረች። ልጆቹን ከሷ ጋር ይዛ እንደምትሔድ እርግጠኛ ነበር —ነገር ግን አልሄደችም።

አንዳንዴ ጠንካራ መተላለፎች ወደ ፍቺ ይመራሉ እና እንደሁኔታው ያ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ለዚህ ሰው ግርምት ባለቤቱ ተቀበለችው እንዲሁም መድረግ ባለባት መንገዶች ሁሉ እሱን ለመርዳት እራሷን ሰጠች። ከጊዘያት በኃላ ሙሉ ለሙሉ ይቅር ልትለው ቻለች። ለእርሷ ያለው የአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ፈዋሽ ሀይል ተሰማት። ከአመቶች በኃላ እነዚህ ጥንዶች እና ልጆቻቸው ጠንካራ እና ታማኝ ናቸው። ባልና ሚስት በቤተመቅደስ ያገለግላሉ እና ድንቅ ተወዳጅ ትዳር አላቸው። የዚህ ሰውዬ ምስክርነቱ እና ለአዳኙ ያለው ምስጋና ለህይወቱ እርግጥ ነው።

አሙሌክ ሲመሰክር “እንድትመጡ እና ልባችሁን ከዚበላይ አታጠጥሩ እላለሁ፤ …ጊዜው እና የመዳኛችሁ ቀን አሁን ነው … ስለዚህ ንሰሀ ከገባችሁ እና ልባችሁን ካላጠጠራችሁ ታላቁ የመዳን ዕቅድ ወዲያውኑ በናንተ ላይ ይመጣል።”1

አንድ ጠዋት በሚሽን ላይ የበላይ ሆኖ ባለቤቴ በመራ ጊዜ ሳገለግል ትልቅ የሚሲሆናዊያን ቡድን ለመቀበል ወደ አየር ማረፊያ ሄድ። አንድ ወጣት ልጅ ላይ አይናችን አረፈ። ያዘነ ይመስላል፣ ሸክም ያለበት የተጨነቀ ነበር። ያን እለት ከሰዓት በጥንቃቄ ተመለከትነው። ምሽት ላይ ይህ ወጣት የዘገየ ኑዛዜን ሰጠ እና የሱ መሪዎች ወደ ቤት መመለስ እንዳለበት ወሰኑ። ምንም እንኳ ታማኝ ባለመሆኑ እና ሚሽን ከመምጣቱ በፊት ንሰሀ ባለመግባቱ ብናዝንም ወደ አየር መንገድ ስንሔድ በእውነት እና በመውደድ እውነቱን ለመናገር ስለነበረው ብርታት አመሰገነው እና ከእሱ ጋር ግንኙነታችንን እንደምንቀጥል ቃል ገባልነት።

ይህ ትልቅ ወጣት ድንቅ ወላጆች፣ ታላቅ የክህነት ስልጣን መሪዎች እና ደጋፊና አፍቃሪ የሆነ ቅርንጫፍ ስላለው ተባርኳል። ለአንድ አመት ሙሉ ለሙሉ ንሰሀ ለመግባት እና የአዳኙን የሀጢያት ክፍያ ለመካፈል ጠንክሮ ከሰራ በኃላ ወደ እኛ ሚሽን ተመለሰ። ከአየር መንገድ ይህንን ወጣት ልጅ ስንቀበለው የነበረንን ደስታ መግለፅ አልችልም። በመንፈስ የተሞላ፣ ደስተኛ እና በጌታ ፊት በራስ መተማመን የነበረው እና ታማኝ የሆነ ተልዕኮውን ለማማላ የጓጓ ነበር። ድንቅ ሚሽነሪ ነበር እናም ቆየት ብሎም የሱን የቤተመቅደስ ጋብቻ መካፈል ቻልን።

በተቃራኒው ስሌላ ሚሽነሪ አውቃለሁ ከሚሽን አገልግሎታ በፊት ያልተናዘዘቻቸው ሀጢያቶች ወደ ቤቷ እንደሚመልሳት ያወቀችው በጣም ጠንክራ ሚሽኗን በማገልገል ልክ ሚሽኗን ልትጨርስ ጥቂት ቀናት ሲቀራት ለሚሽን ፕሬዝዳንቷ ለመናዘዝ አቀደች። እሷ እግዚአብሔራዊ ፀጸት አጣች እናም አፍቃሪ አዳኛችን ለእያንዳንዳችን የሰጠውን እቅድ አከሸፈችው።

በሚሽን አገልግሎታችን ጊዜ ባለቤቴ አንድ የሚጠመቅ ሰው ቃለ መጠይቅ ሊያደርግ ሲሄድ አብሬው ሄድኩ። ባለቤቴ ቃለመጠይቁን ሲያደርግ እኔ ሰውየውን ካስተማሩት ሴቶች ሚሺነሪዎች ጋር ውጪ ቆየሁ። ቃለ መጠይቁ ሲያልቅ ባለቤት ሰውየው መጠመቅ እንደሚችል ለሚሽነሪዎቹ ነገራቸው። ይህ ውድ ሰው በህይወቱ ውስጥ ያደረጋቸው ከባድ ኃጢያቶችን ከመጠመቅ እንደሚያስቆሙት ሲያብራራ በለቅሶ ላይ ለቅሶ ያለቅስ ነበር። አንድ ሰው ከጨለማ ወደ ብርሀን ሲመጣ ያለውን ሀሴት እና ደስታ እንደዛ ቀን የሚስተካከለው እንብዛም ነው።

አዳኝ ተስፋ ሲሰጥ

ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እንደመሰከሩት፥

“በቤዛችን ምህረት እና በሀይሉ በማመን፣ ተስፋ መቁረጥ ለመሆን የሚችለው ወደ ተስፋ ይቀየራል። የሰው ልብና የመቀየር ፍላጎት፣ እናም የሚያጓጓ የሚመስለው ኃጢያት የሚያስቀይም ይሆናል። …

“… የንስሀ መግባት ዋጋ ምንም ቢሆን፣ የምህረት ደስታ ይውጠዋል።”2

ይህ ተሞክሮ በመፀሀፈ ሞርሞን ውስጥ “በታለቅ ፀሎት ወደ ጌታው የጮኸውን” ኢኖስን ያስታውሰኛል ከዛም ድምፅን ሰማ ኢኖስ ሀጢያት ይቅር ተብሎልሀል። …

“እኔ ኢኖስ እግዚአብሔር ሊዋሽ አንደማይች አውቃለሁ ስለሆነም በደሌ ተወግዶልኛል።

እኔም አልኩት “እናም ጌታ ይህ እንዴት ሆነ?

“እናም እርሱም አለኝ፡- በክርስቶስ ባለህ እምነት ምክንያት ነው። … ሂድ እምነትህ አድኖሀል።”3

ይህንን ንግግር ሳዘጋጅ የልጅ ልጆቻችን ንሰሀን እንዴት እንደሚረዱት እና ስለአዳኛችን ምን እንደሚሰማቸው ማወቅ ፈለኩ፣ ስለዚህ ልጆቻችንን ተከታዩን ጥያቄዎች እንዲጠይቁልን ጠየኳቸሁ። በልጅ ለጆቻችን ምላሽ ተነክቼ ነበር።

ንስሀ መግባት ምንድን ነው? “አንድን ስትመቱ፣ ‘ይቅርታ’ ለማለት እና እንዲነሱ ለመርዳት ትችላላችሁ።”

ንሰሀ ስትገቡ ምን ይሰማችኃል? “ስለእርሱ ስሜት ይኖራችኋል፤ የእርሱ ሙቀት ይሰማችኋል፣ እናም መጥፎ ስሜቱ ይጠፋል።”

ንሰሀ ስትገቡ ስለ ኢየሱስ እና ስለ ሰማይ አባት ምን ይሰማችኃል? “ኢየሱስ የሀጢያት ክፍያ ማድረጉ ተገቢ እንደሆነ እንደሚሰማው ይሰማኛል እናም ከእሱ ጋር ዳግም ለመኖር መቻላችን ያስደስተዋ።”

ኢየሱስ እና የሰማይ አባት ለምን ንስሀ እንድገባ ይፈልጉኛል? በወጣት የልጅ ልጄ ቃላትም፥ “ምክንያቱም ስለሚወዱኝ! ለማደግ እና እንደ እነርሱ ለመሆን፣ ንስሀ መግባት አለብኝ። መንፈስ ከእኔ ጋር እንዲሆን እፈልጋለም፣ ስለዚህ የእርሱን አስደናቂ ጓደኝነት ለማግኘት በየቀኑ ንስሀ መግባት ያስፈልገኛል። እነርሱን በብቁ ለማመስገን ግን በምንም አልችልም።”

የአራት አመቷ ብራይንሊ እነዚህን ጥያቄዎች ስትሰማ “አላውቅም አባዬ አንተ አስተምረኝ” አለች።

ብራይሊ እና አባቷ

ባለፈው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሽማግሌ ጌፍሪ አር. ሆላንት እንዳወጁት፥ ምንም ረፈደብኝ ብላችሁ ብታስቡ፣ ምንም እንኳ አጥቼዋለሁ ብላችሁ ብታስቡ፣ ምንም ያህል ስህተት እንደሰራችሁ ቢሰማችሁ… ፣ ወይም ምንም ያህል ከቤታችሂ ከቤተሰባችሁ እና ከእግዚአብሔር እርቃችሁ እንደተጓዛችሁ ቢሰማችሁ እመሰክርላችኃለሁ መለኮታዊው ፍቅር ከሚደርስበት ርቃችሁ አልሄዳችሁም። ስፍር ከሌለው ከክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ ብርሀን ከሚበራበት አልፋችሁ ልትሰምጡ አትችሉም።4

ኦ ምንያህል ልጆቼ፣ የልጅ ልጆቼ እና እያንዳንዳችሁ —የእኔ ወንድሞች እና እህቶቼ እለት ተእለት ሀጢያታችን እና ድክመታችን ንሰሀ ስንገባ የደስታ ስሜት እና ወደ ሰማይበታችን እና ወደ አዳኛችን መቅረብን እንዲሰማን እንዴት እንደምፈልግ። እያንዳንዱ ተጠያቂ የእግዚአብሔር ተጠያቂ ልጆች ንሰሀ ያስፈልጋቸዋል። ምን ሀጢያቶች ንሰሀ መግባት እንዳለብን አስቡበት? ምንድነው የሚይዘን? በምን አይነት መንገድ መሻሻል አለብን?

አውቃለሁ ልክ እንደ ፕሬዝዳንት ፓከር ተሞክሮ እና እንደመሰከሩት በእውነት ንሰሀ ስንገባ ሀጢያታችን ይወገዳሉ— ያለምንም አሻራ! እኔም በልብ ንስሀ ስገባ በጌታ ፊት ፍቅር፣ ደስታ፣ እረፍት፣ እና ልበ ሙሉነት ተሰምቶኛል።

ለእኔ በዚህ ህይወት ቀይ ባህር መከፈሉ፣ ተራራ መነሳቱ ወይም ሠውነት መፈወስ አይደለም ታላቁ ታእምር። ትልቁ ታአምር የሚከሰተው በትህትና የሰማይ አባታችን ስንቀርብ፣ ምህረት እንዲሰጠን በሀይል ስንለምን፣ እና ከዚያም በአዳኛችን የሀጢያት ክፍያ አማካኝነት ከሀጢያታችን ስንነፃ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።