የፅዮን እህቶች፣ በጥንካሬ ተነሱ
ያንን ለማድረግ፣ የወንጌልን ወሳኝ አስተምሮቶች የምናጠና እና ስለ እነርሱ እውነታነት የማይነቃነቅ ምስክርነት ያለን ሴቶች መሆን ያስፈልገናል።
በዚህ የጉባኤ ማእከል ከቤተክርስቲያን ሴት ልጆች፣ ወጣት ሴቶቸ፣ እና ትልቅ ሴቶች መሰባሰብ እጅግ አስደሳች ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ልላ የእህቶች ቡድኖች በመላው አለም እነዚህን ስርአቶች እንደሚመለከቱም በደምብ እናውቃለን፣ እናም በዚህ ምሽት በአንድነት እና አላማ አንድ እንድንሆን ላደረጉት እድሎች እና ምክንያቶች አመስጋኝ ነኝ።
በጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)፣ ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ በ1911 (እ.አ.አ) ከተጻፈ መዝሙር የተወሰደ “ተነሱ፣ እናንተ የእግዚአብሔር ወንዶች፣” የሚል ርዕስ ያለው ንግግር አቀረቡ።1 ይህም የቤተክርስቲያኗ ወንዶች እንዲነሱና ራሳቸውን እንዲያሻሽሉ የሚጠራ ነበር። ከእናንተ ጋር ምን እንደማካፍል ለማወቅ ስፀልይ ያ ንግግር በአእምሮዬ አስተጋባ።
እህቶች፣ “በአደገኛ ጊዜ” ነው የምንኖረው።2 የጊዜያችን ሁኔታዎች ሊያስገርመን አይገባም። የተዘጋጀን መሆን እንችል ዘንድ እንደማስጠንቀቂያ እና ተግሳፅ ቀድመው ተተንብየው ነበር። በሞርሞን 8ኛው ምዕራፍ ላይ በሚያስፈራ መልኩ የእኛ ጊዜ ሁኔታዎችን በትክክል ያብራራል። በዛ ምዕራፍ ውስጥ፣ ሞሮኒ የእኛን ጊዜ እንደተመለከተ ይናገራል፣ እና ጦርነቶች እና የጦርነቶች ወሬዎችን፣ ታላቅ ብክለቶችን፣ ግድያዎችን፣ ዝርፊያዎችን፣ እና በእግዚአብሔር እይታ ትክክል ወይም ስህተት የለም ዪሉ ሰዎችን ያካትታል። እርሱ በኩራት የተሞሉ፣ ወድ ልብስ በመልበስ የሚታዩ፣ እና በሀይማኖት ላይ የሚያሾፉ ሰዎችን ያብራራል። በምድራዊ ነገሮች በመጠመዳቸው የተነሳ “የተቸገሩ፣ እናም የታረዙ፣ እናም የታመሙ እና የተሰቃዩትን”3 ባለማስተዋል እንዲያልፉ የሚያደርጉ ሰዎችንም ተመልክቷል።
በዚህ ጊዜ ለምንኖረው ሞሮኒ እስከ ነብስ የሚዘልቅ ጥያቄን ይጠይቀናል። እንዲህ ይላል፣ “የክርስቶስን ስም በላያችሁ ለመውሰድ ለምን ታፍራላችሁ?”4 ይሄ ተግሳፅ ምድራዊ በመሆን እየጨመረ የመጣውን አለማችንን ይገልፀል።
የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ላይ በመጨረሻው ቀናት “በቃልኪዳን መሰረት የተመረጡት”5 እንኳን ሳይቀሩ እንደሚታለሉ ማቴዎስ ይጠቁማል። የቃልኪዳን የተባሉት የተጠመቁ እና ከሰማይ አባት ጋር ቃልኪዳን የገቡትን ሴት ልጆች፣ ወጣት ሴቶች፣ እና እህቶችን ያካትታል። እኛም እራሱ በሀሰት ትምህርቶች የመታለል አደጋ ውስጥ ነን።.
እህቶች፣ ወደፊት ሁኔታዎች ይሻሻላሉ ብዬ አላምንም። የአሁን እንቅስቃሴዎች ጠቋሚዎች ከሆኑ፣ ወደፊት ተዘርግተው ላሉት ማእበሎች መዘጋጀት ያስፈልገናል። በመሰላቸት እጃችንን ለመስጠት ቀላል ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን እንደ ቃልኪዳን ህዝቦች በፍፁም አንሰላችም። ሽማግሌ ጌሪ ስቲቨንሰን እንዳሉት፣ “በአስፈሪ ጊዜያት በመኖራችን የሰማይ አባት በደግነት የካሰን በሙሉነት ጊዜያት በመኖራችንም ነው።”6 የዛን አርፍተ ነገር መፅናኛ እወደዋለሁ።
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ካመት በፊት እንደነገሩን፥ “በቤተክርስቲያኑ፣ በአስተምሮቱ፣ እና በአኗኗራችን ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ይጨምራሉ። በዚህ ምክንያት፣ ስለ ክርስቶስ አስተምሮት ጥልቅ መረዳት ያላቸው እና መረዳታቸውን ለማስተማር እናም ሀጢያትን የሚቋቋም ትውልድን በማፍራት የሚረዱ ሴቶች ያስፈልጉናል። ማጭበርበርን በመላ ገፅታዎቹ የሚያጣሩ ሴቶች ያስፈልጉናል። ለቃልኪዳን ጠባቂዎች እና እምነቶቻቸውን በራስመተማመን እና ልግስና ለሚገልፁ እግዚአብሔር ያዘጋጀውን ሀይል እንዴት እንደሚያገኙ የሚያውቁ ሴቶች ያስፈልጉናል። የእናታችን ሔዋን ብርታት እና ራዕይ ያላቸው ሴቶች ያስፈልጉናል።”7
የጊዜአችን ሁኔታዎች ምንም ቢሆኑ፣ ለመደሰት እና አውንታዊ ለመሆን ብዙ ምክንያቶች እንዳሉን ይሄ መልዕክት ያረጋግጥልኛል። እኛ እህቶች ተፈጥሮአዊ ጥንካሬ እና በመጨረሻው ቀናት የመኖርን ፈተናዎች እንድንጋፈጥ የሚያበቃን እምነት እንዳለን በሙሉ ልቤ አምናለሁ። እህት ሼሪ ደው እንዲህ ፃፈች፣ “የቃልኪዳን ጠባቂ ሴቶችን፣ የመቀየር ሙሉ ተፅእኖ ነፃ ማድረግ በጀመርንበት ቅፅበት፣ የእግዚአብሔር መንግስት በአንድ ምሽት ይቀየራል።”8
ለመቀየር እና ቃልኪዳንን ለመጠበቅ ፅኑ ጥረትን ይጠይቃል። ያንን ለማድረግ፣ የወንጌልን ወሳኝ አስተምሮቶች የምናጠና እና ስለ እነርሱ እውነታነት የማይነቃነቅ ምስክርነት ያለን ሴቶች መሆን ያስፈልገናል። ለጠንካራ ምስክርነቶች መሰረታዊ የሆኑ እና ለመረዳታችን ወሳኝ ናቸው ብዬ የማምናቸው ሶስት ነገሮች አሉ።
አንዱ፣ ለእምነት እና ደህንነታችን የዘለአለማዊ አባታችን፣ እግዚአብሔር እና የልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ማእከላዊነት ማወቅ ያስፈልገናል። ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን እና ቤዛችን ነው። የእርሱን የሀጢአት ክፍያ እና እንዴት መተግበር እንደምንችል ማጥናት እና መረዳት ያስፈልገናል፤ በመንገዱ ላይ ለመቆየት እያንዳንዳችን ካሉን ታላቅ በረከቶች ውስጥ ንሰሀ አንዱ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ቀዳሚ አራአያችን መመልከት እና ምሳሌዎቹን ሆነን መገኘት አለብን። የክርስቶስን እስተምሮት ስለሚያካትተው፣ የአባታችን ታላቅ የደህንነት እቅድ ቤተሰቦቻችንን እና በክፍሎቻችን በቀጣይነት ማስተማር አለብን።
ሁለተኛ፣ በዚህ በኋለኛው ቀን የአስተምሮቱ፣ አወቃቀሩ እናም የስልጣን ቁልፎቹ ዳግም መመለስ አስፈላጊነትን ልንረዳው ይገባል። ነብዩ ዮሴፍ ስሚዝ በመለኮት እንደተመረጠ እና ዳግም መመለስን እንዲፈፅም በጌታ የተጠራ እንደሆነ ምስክርነት ሊኖረን ያስፈልጋል እናም በጥንት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደነበረው አወቃቀር የቤተክርስቲያኑን ሴቶች እንዳዋቀረ ማስተዋል አለብን።9
እና ሶስተኛ፣ የቤተመቅደስ ስርአቶችን እና ቃልኪዳኖችን ማጥናት እና መረዳት አለብን። ቤተመቅደስ የአብዛኛው ቅዱስ እምነቶቻችን ማእከላዊ ቦታ ይይዛል፣ እና እንድንካፈል፣ እንድናሰላስል፣ እንድናጠና፣ እና የግል ትርጉም እና ግለሰባዊ አተገባበር እንዲኖረን ጌታ ይጠይቃል። በቤተመቅደስ ስርአቶች አማካኝነት የመለኮታዊ ሀይል በህይወቶቻችን ይንፀባረቃል፣10 እና በቤተመቅደስ ስርአቶች ምክንያት፣ የእግዚአብሔር ሀይል ጥሩራችን መሆን ይችላል እናም የእርሱ ስም በኛ ላይ ይሆናል፣ ክብሩ በእኛ ዙሪያ፣ እናም የእርሱ መላእክት በእኛ ላይ እንደሚሰማሩ እየተረዳን እንመጣለን።11 በእነዚያ ቃልኪዳኖች ላይ በሙሉ ምልከታ ያለን ስለመሆናችን ያሳስበኛል።
እህቶች፣ በዚህ ምእመን ውስጥ በጣም ትንሽዋ እንኳን ከፍ ማለት እና የእግዚአብሔርን መንግስት በመገንባቱ ጠቃሚ ሚና መጫወት ትችላለች። ልጆች ቅዱሳት መጽሐፍትን በማንበብ እና በመስማት፣ በየቀኑ በመፀለይ፣ እናም ትርጉም ባለው መንገድ ቅዱስ ቁርባንን በመካፈል የራሳቸውን ምስክርነት ማግኘት ይጀምራሉ። ሁሉም ልጆች እና ወጣት ሴቶች የቤተሰብ ምሽቶችን ማበረታታት እና ሙሉ ተሳታፊ መሆን ይችላሉ። ቤተሰበችሁ ለቤተሰብ ፀሎት ሲሰበሰቡ በመንበርከክ ቀዳሚ መሆን ትችላላችሁ። በቁጥር አናሳ ሊባል የሚችል ቤተሰብ ቢኖራችሁም፣ በእምነት ወንጌልን የመኖር የግል ምሳሌዎቻችሁ የቤተሰባችሁን እና የጓደኞቻችሁ ህይወት ላይ ተፅእኖ ማድረግ ይችላል።
የቤተክርስቲያን ወጣት ሴቶች በክህነት በሚመራው የደህንነት ስራ ውስጥ እንደ ተመልካቾች እና ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን እንደ ወሳኝ ተሳታፊዎች እራሳቸውን እንዲመለከቱ ያስፈልጋል። በዚህ ስራ ውስጥ እንደ መሪዎች በሀይል እና ስልጣን እንድትተገብሩ ጥሪዎችን ተሸክማችኋል እናም የክህነት ቁልፎችን በያዙት ሰዎች ተሰይማችኋል። በክፍል መሪነቶች ውስጥ ጥሪያችሁን ስታጎሉ እና በመንፈሳዊ ስትዘጋጁ፣ በዚህ ስራ ውስጥ ቦታችሁን እየወሰዳችሁ ነው እናም እናንተ እና እኩዮቻችሁ ይባረካሉ።
በክህነት ስራ ውስጥ ሁሉም ሴቶች እራሳቸውን እንደ ወሳኝ ተሳታፊዎች መመልከት አለባቸው። በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሴቶች ፕሬዘዳንቶች፣ አማካሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ የመማክርት አባላቶች፣ እህቶች፣ እና እናቶች ናቸው፣ እናም ከፍ ካላልን እና ሀላፊነቶቻችንን በእምነት ካላሟላን በስተቀር የእግዚአብሔር መንግስት ሊንቀሳቀስ አይችልም። አንዳንዴ ስለሚቻለው ነገር ታላቅ ዕራእይ ሊኖረን ይገባል።
ጥሪዎቿን በእምነት ማጉላት ለእርሷ ምን ማለት እንደሆነ የምትረዳ እህትን በቅርቡ በሜክሲኮ ውስጥ አገኘሁ። ማርፊሳ ማልዶናዶ ከሶስት አመታት በፊት የወጣቶች የሰንበት ክፍልን እንድታስተምር ተጠርታ ነበር። ስትጠራ የሚካፈሉ 7 ተማሪዎች ነበሯት፣ ነገር ግን አሁን በቋሚነት የሚከታተሉ 20 ተማሪዎች አላት። በመደነቅ በቁጥር እንዲህ ያለ ጭማሬ ለማምጣት ምን እንዳደረገች ጠየኳት። በትህትና እንዲህ አለች፣ “ኦ፣ እኔ ብቻ አልነበርኩም። ሁሉም የክፍል አባላት እረድተዋል።” በአንድነት፣ በዝርዝር ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑትን ስሞች ተመለከቱ እናም በአንድ ላይ መሄድ እና ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመለሱ መጋበዝ ጀመሩ። በጥረታቸው አማካኝነት ጥምቀትንም አግኝተዋል።
እህት ማልዶናዶ ለክፍል አባላቶቿ ብቻ “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፣” የሚባል ማህበራዊ መገናኛ ዘዴ አዋቀረች፣ እናም በሳምንት ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚያነሳሱ ሀሳቦችን እና ጥቅሶችን ትለጥፋለች። በየወቅቱ ለተማሪዎቿ የቤት ስራዎችን እና ማበረታቻዎችን በመልእክት ትልካለች። እነርሱ በተሻለ በሚገለገሉት መልኩ መነጋገር አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማታል፣ እናም ያ እየሰራ ነው። በቀላሉ እንዲህ አለችኝ፣ “ተማሪዎቼን እወዳቸዋለሁ።” ስለ እነርሱ ጥረት ስትነግረኝ ያ ፍቅር ተሰምቶኛል፣ እና የእርሷ ምሳሌ አንድ የእምነት እና ተግባር ሰው በጌታ እርዳታ በዚህ ስራ ውስጥ ምን ያህል ማሳካት እንደሚችል አስታወሰኝ።
ወጣቶቻችን በየቀኑ ለከባድ ጥያቄዎች ተጋላጭ እየሆኑ ነው፣ እና አብዛኞቻችን መልሶችን ለማግኘት ትግል ላይ ያሉ የቅርብ ወዳጆች አሉን። መልካሙ ዜና እየተጠየቁ ላሉት ጥያቄዎች መልሶች መኖራቸው ነው። ከመሪዎቻችን የተሰጡ የቅርብ ጊዜ መልእክቶችን አዳምጡ። የሰማይ አባታችንን የደስታ እቅድ እንድናጠና እና እንድንረዳ የተገፋፋን ነው። የቤተሰብ አዋጅ መሰረታዊ መርሆችን እንድናስታውስ ተደርገናል።12 በቀጥተኛው እና ጠባቡ መንገድ ላይ ያቆዩን ዘንድ እነዚህን ግብአቶች እንደ መወሰኛ አድርገን እንድናስተምር እና እንድንጠቀምባቸው ተበረታተናል።
ከአንድ አመት በፊት፣ ልጆቿ ከተጋለጡበት የኢንተርኔት እና የትምህርት ቤት አሉታዊ ተፅእኖዎች ለመከላከል ስትል ተግባራዊ ምንግን ለመከተል የወሰነችን የወጣት ልጆች እናት ጎበኘሁ። በየሳምንቱ አዲስ ዕርእስ ትመርጣለች፣ በአብዛኘው ጊዜ በኢንተርኔት ብዙ ያነጋገረውን ርእስ፣ እናም በሳምንቱ ውስጥ ልጆቿ ጥያቄ በሚጠይቁበት ጊዜ ትርጉም ያለው ውይይትን ታነሳለች እና በአብዛኛው በሚከብዱ ጉዳዮች ላይ የተመጣጠነ እና ተገቢ አመለካከትን ማግኘታቸውን ታረጋግጣለች። ጥያቄዎችን ለማንሳት እና ትርጉም ያለው የወንጌል መመሪያ እንዲኖር ቤቷን ደህንነት ያለው ቦታ ታደርጋለች።
ንዴትን በማስወገድ ሁኔታ ውስጥ ከመኖራችን የተነሳ አንዳንዴ ትክክለኛ መርሆችንም ከማስተማር በአንድ ላይ እንቆጠባለን ብዬ እሰጋለሁ። ያላገቡትን ወይም ልጆች መውለድ የማይችሉትን፣ ወይም የወደፊት ምርጫዎችን ገዳቢ ሆነን በመታየት ሌሎችን ማናደድ ባለመፈለጋችን ምክንያት ወጣት ሴቶቻችንን እናት ለመሆን ስለመዘጋጀት አስፈላጊነት ከማስተማር እንቧዝናለን። በሌላ በኩል፣ የትምህርትን አስፈላጊነት ከማጉላት እንቆጠብም ይሆናል ምክንያቱም ከጋብቻ በላይ አስፈላጊ ነው የሚል መልእክት ማስተላለፍ ስለማንፈልግ። የተመሳሳይ ፆታ ፍላጎት ያላቸውን ማበሳጨት ባለመፈለጋችን ምክንያት የሰማይ አባት ጋብቻን የሚተረጉመው በወንድ እና በሴት መሀከል እንደሆነ ከማወጅ እንቆጠባለን። እናም ስለ ጾታ ጉዳዩች ወይም ስለ ጤናማ የጾታ ግንኙነት መወያየት ምቾት የሌለው ሆኖ እናገኘው ይሆናል።
በእርግጥም፣ እህቶች፣ ስሜትን መጠቀም አለብን፣ ነገር ግን በሚኖሩበት አለም ውስጥ ቀዝፎ ለመውጣት መረዳት ያለባቸውን ወሳኝ የወንጌል መርሆዎችን ለልጆቻችን እና ወጣቶች ወደ ማስተማር ስንመጣ በድፍረት እና ቀጥተኛ ለመሆን ማስተዋላችንን እና ስለ ደህንነት እቅድ ያለን መረዳታችንን መጠቀምም አለብን። ልጆቻችንን እና ወጣቶችን በግልፅ—እውነተኛ አስተምሮትን የማናስተምራቸው ከሆነ—የሴጣንን ውሸቶች አለም ያስተምራቸዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እወዳለሁ፣ እና የእግዚአብሔር የቃልኪዳን ሴት ልጅ እንደመሆኔ ስለማገኛቸው የምሬት፣ የሀይል፣ እና የየቀን እገዛ ለዘለአለም አመስጋኝ ነኝ። በዚህ አደገኛ ጊዜ የምንንኖር ሴቶች በመሆናችን፣ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅአት አለምን ለማዘጋጀት በሚያስፈልግ ሙሉ ሀይል፣ ስጦታዎች፣ እና ጥንካሬ ጌታ እኛን እንደባረከን እመሰክራለሁ። ሙሉ አቅማችንን ሁላችንም እንድንመለከት እና የሰማይ አባት እንድንሆን የሚፈልገውን የእምነት እና የብርታት ሴቶች ለመሆን ከፍ እንድንል ፀሎቴ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።