2010–2019 (እ.አ.አ)
ጻድቁ ፈራጅ
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


10:24

ጻድቁ ፈራጅ

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያደርገው፣ በጻዲቅ ፍርድ ለመፍረድ አንድ ብቻ መንገድ አለ፣ ያም እርሱ እንደሆነው መሆን ነው።

በምድራዊ ህይወቱ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ አፍቃሪ ዳኛ፣ ባልተለመደ መልኩ ጠቢብ እና ታጋሽ ነበር። በቅዱሳት መጽሐፍት እንደ “ጻዲቅ ፈራጅ” ይታወቃል (2 ጢማቴዎስ 4፥8ሙሴ 6፥57)፣ እና የእርሱም ምክር እኛም “በጽድቅ ፍርድ እንድንፈርድ” ነው (የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማቴዎስ 7፥1–2 [በ ማቴዎስ 7፥1፣ የግርጌ ማስታወሻ ]) እናም “እምነታችሁን ወደ መልካም በሚመራው መንፈስ ቅዱስ ላይ እንድታደርጉ … [እና] በጽድቅ እንድትፈርዱ” (ት. እና ቃ. 11፥12)።

ለኔፋውያን አስራ ሁለት የተሰጠው ይህ ምክር እንደ ጌታ እንድንፈርድ ይረዳናል፥ “እናም ትክክል በሚሆነው ለእናንተ በሰጠኋችሁ ፍርድ መሰረት፣ በዚህ ህዝብ ላይ ፈራጅ ናችሁ። ስለዚህ፣ እናንተ ምን አይነት ሰዎች ትሆኑ ዘንድ ይገባችኋል? እውነት እላችኋለሁ እንደ እኔ ሁኑ” (3 ኔፊ 27፥27፤ አጽኖት ተጨምሮበት)። አንዳንድ ጊዜ የምንዘነጋው ነገር እንደእርሱ የመሆንን ምክር ሲሰጥ፣ በጽድቅ እንድንፈርድ በማስመልከት እንደነበር ነው።

ጻድቅ ያልሆነ ፍርድ

አዳኝ ከፈራሲዎች እና ከጸሀፊዎች ጋር

የጻድቅ ያልሆነ ፍርድ አሳፋሪ ምሳሌን የምናገኘው በጠፋው በግ ምሳሌ ውስጥ አዳኝን እና አብረውት እራት የበሉትን “ይህስ ሃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል”(ሉቃስ 15፥2)ብለው ፈሪሳውያን እና ጸሐፍቶች ተገቢ ያልሆነ ፍርድ የሰጡበት ነው—እነርሱ እራሳቸው ሀጢአተኞች እንደነበሩ እውነታው ያረጋግጥ ነብር። ልብን በማውገዝ ስለጠመዱ፣ ፈሪሳውያን እና ጸሐፍቶች የጠፋውን በግ የማዳን ደስታ በፍጹም አልገባቸውም ነበር።

አዳኝ በዝሙት ከተያዘች ሴት ጋር

“ፈሪሳውያን እና ጸሐፍቶች”ም ነበሩ (ዮሀነስ 8፥3) “በአመንዝራ የተያዘችን ሴት” በሙሴ ህግ እንደሚፈርድባት ለማየት ወደ አዳኝ ያመጧት (ቁጥር 5ተመልከቱ)። ቀሪውን ታሪክ ታውቁታላችሁ፣ ጻዲቅ ስላልሆነው ፍርዳቸው እንዴት ትሁት እንዳደረጋቸው፣ እና “ህሊናቸውወቀሳቸው” እና “አንድ በአንድ” ወጡ።(ቁጥር 9; አመጽኖት ተጨምሮበት)። ከዛ ሴቲቱን እንዲህ አላት፣ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ሀጢአት አትስሪ። እና ሴቲቱ ከዛ ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔርን አከበረች” (የዮሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዮሀነስ 8፥11 [በ ዮሀንስ 8፥11፣ የግርጌ ማስታወሻ ])።

አዳኝ በዝሙት ከተያዘች ሴት ጋር ሲነጋገር

በእያንዳንዳችን ውስጥ ያለው ተፈጥሮአዊው ሰው ሌሎችን የማውገዝ እና ያለጽድቅ ወይም በግል ውሳኔ ወደ መፍርድ ያመዝናል። ይህም በሁለቱ የአዳኝ ሐዋርያት፣ ያቆብ እና ዮሀንስ ላይም ተከስቷል። እነርሱ የሰማሪያ መንደር ሰዎች አዳኝን በአክብሮት ባለማየታቸው ተቆጥተው ነበር (ሉቃስ 9፥51–54 ተመልከቱ)፥

አዳኝ ከሚከተሉት ጋር

“እናም [እነርሱ] ይህን አይተው፣ ጌታ ሆይ፣ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዝንድ ትወዳለህ አሉት?

“እርሱ ግን ዞር ገሰጻቸውና ምን አይነት መንፈስ እንደ ሆነላችሁ አታውቁም፤

“የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም አለ” (ቁጥር 54–56)።

የዛሬ “የተለመዱ ፈራጅ[ጆች]” (ት. እና ቃ. 107፥74) በዛ ሁኔታ ላይ ያቆብ እና ዮሀንስ እንዳድረጉት፣ ተመሳሳይ የማውገዝ ባህሪን ማስወገድ አለባቸው። ጻዲቅ ፈራጅ ኑዛዜዎችን በርህራሄ እና መረዳት ይመልሳል። ለምሳሌ፣ ያጠፋ ወጣት፣ ከኤጲስ ቆጶስ ቢሮ ሲወጣ ቤጲስ ቆጶሱ ውስጥ የአዳኝ ፍቅር ተሰምቶት እና በሀጢአት ክፍያው ደስታ እና የማዳን ሀይል ውስጥ ተካትቶ መሆን አለብት—በፍጹም በሀፍረት እና በንቀት ታይቶ መሆን የለበትም። ያለበለዚያ፣ ባለማወቅ ኤጲስ ቆጶሱ የጠፋውን በግ የባሰ ወደ ምድርበዳ ሊግፋው ይችላል (ሉቃስ 15፥4)።

ቅጣት

ሆኖም፣ ርህራሄ የቅጣት አስፍላጊነትን አይሽርም። መቅጣት የሚለው ቃል የመጣው discere፣ ከሚባለው የላቲን ቋንቋ ነው፣ ይህም “መማር፣” ወይም discipulus፣ “ተማሪ፣” ማለት ነው፣ ይህም ተማሪ እና ተከታይ ያደርገዋል።1 ጌታ እንደሚያደርገው መቅጣት በፍቅር እና በትዕግስት ማስተማር ነው። በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥመገሰጽ፣ የሚለውን ቃል ጌታ ስለመቅጣት ሲናገር በአብዛኛው ይጠቀማል (ለምሳሌ፣ ሞዛያ 23፥21ት. እና ቃ. 95፥1 ተመልከቱ)። መገሰጽ የሚለው ቃል castus ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ሲሆን፣ “ንጹህ” ማለት ነው እና ግሰጻ ደግሞ “ማንጻት” ነው።2

በአለም ውስጥ፣ ሰውን የሚያወግዘው እና እስር ቤት የሚያስገባው ምድራዊ ፈራጅ ነው። በተቃራኒው፣ መጸሐፈ ሞርሞን እንደሚያስተምረን እኛ በፍቃደኝነት ሀጢአት ስንሰራ፣ እኛ “የራሳችን ፈራጅ” እንሆናለን (አልማ 41፥7) እና እራሳችንን ወደ መንፈሳዊ እስር እንከታልን። በተምሳሌታዊ ንግግር፣ የተለመደው ፈራጅ የእስር ቤቱን ዋና በር የሚከፍተውን ቁልፍ ይይዛል፤ “በግሳጼ ውስጥ ከፈተና ሁሉ የሚወጡበትን መንገድ አዝጋጅላቸዋለሁ (ት. እና ቃ. 95፥1፤ አመጽኖት ተጨምሮበት)። የጻዲቅ ፈራጅ መገለጫዎች መሀሪነት፣ አፍቃሪነት፣ እና አውጋዠ ሳይሆን አዳኝንት ናቸው።

ወጣቱ ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ከማግኘቱ በፊት በአራት አመታት የመቀየሪያ ጊዜ ተቀጥቶ ነበር፣ “የጌታን ትእዛዛት ባለመጠበቅህ የተነሳ።”3 በኋላም፣ ጆሴፍ የ116 ያልታተሙ ገጾችን ባጣበት ጊዜ፣ እንደገና ተገስጾ ነበር። እርሱ በእውነት ቢጸጸትም፣ ለጥቂት ጊዜ ጌታ እድሎቹን አንስቶበት ነበር፣ ምክንያቱም “ሀጢአቱ ይቅር ይባል ዘንድ የምወደውን ደግሞም እቀጣለሁ” (D&C 95፥1)።

ጆሴፍ እንዲህ አለ፣ “መልአኩ ዩረም እና ቱመሙን መልሶ ሲሰጠኝ ተደስቶ ነበር እናም እግዚአብሔር በታማኝነቴ እና በትሁትነቴ እንደተደሰተ፣ እና ንስሀ በመግባቴ እና በትጋት ጸሎቴም ምክንያት እንደሚያፈቅረኝ ነገረኝ።”4 ጌታ ጆኤፍን ልብ የሚቀይር ትምህርት ለማስተማር ስለፈለገ፣ ልብ የሚሰነጥቅ መስዋዕት ፈለገበት–መስዋዕትም የቅጣት አስፈላጊ ክፍል ነውና።

መስዋእት

“በጥንት ጊዜያት፣ መስዋእትማለት አንድን ነገር ወይም ሰው ቅዱስ ማድረግ ነበር፣”5 በተናጠል መልኩ፣ ያን መገሰጽ—“ማንጻት” ከሚለው ቃል ጋር ማያያዝ ይቻላል።” እንደዚህም፣ በጥንት እስራኤል ውስጥ፣ ምህረት የሚመጣው በንስሀ ወይም በመተላለፍ መስዋዕት ነው።6 መስዋዕትም “ወደ ታላቅ እና የመጨረሻ መስዋዕት ያጠቁማል” (አልማ 34፥14) ግን ደግሞም ለአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ዝልቅ ምስጋና እንዲሰማም ያደርጋል። የመጸጸታችን አካል ሆኖ መስዋት ለማድረግ የፍላጎት አለመኖር ለተመሳሳይ ሀጢአት ያደረገውን ታላቅ መስዋእት ላይ መሳልቅ ወይም ማንቋሸሽ ነው እናም የክርስቶስን ስቃይ ከንቱ ያደርገዋል—ርህራሄ የሌለው አመስጋኝ ያለመሆን ምልክት ነው።

በሌላ በኩልም፣ በመስዋዕት ምክንያት፣ እኛም በእርግጥ የዘለአለም ዋጋ ያለውን–የእርሱን ምህረት እና በመጨረሻም “አብ ያለውን በሙሉ” እንድናገኝ ያደርጋል (ት. እና ቃ. 84፥38)። እንደ የንስሀ ሂደቱ አካል፣ “የህሊና ጸጸትን” (አልማ 42፥18) “በህሊና ሰላም” (ሞዛያ 4፥3) በመተካቱ እንዲረዳ መስዋእት እንደ የማዳኛ ማስታገሻም ይሰራል። ያለመስዋእት፣ እራሱን ይቅር ለማለት ሰው ሊከብደው ይችላል፣ ምክንያቱም በተገደበ ነገር ህሊና ስለሚያመነታ ነው።7

ወላጅ እንደ ጻድቅ ፈራጅ

ጥቂቶቻችን የተለመዱ ፈራጆች እንድንሆን እንጠራለን፣ የጻዲቅ ፍርድ መርሆዎች በሁላችንም ላይ ይሰራሉ፣ በተለይም ይንን በየቀኑ ከልጆቻቸው ጋር የመጠቀም እድል ላላቸው ወላጆች። ልጅን በውጤታማነት ማስተማር የመልካም ወላጅነት ውሳኙ ክፍል ነው፣ እናም በፍቅር መቅጣት የጻድቅ ፈራጅ የመሆን ወሳኙ ክፍል ነው።

ፕሬዘዳንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ እንዲህ አስተማረ፣ “ለቁጥጥር ልጆች እምቢተኛ እና አስቸጋሪ ከሆኑ፣ በፍቀር እስክታሸንፉ ድረስ ታጋሽ ሁኑ፣ … እና ከዛ እንደፈለጋችሁ ባህሪያቸውን።”8

ስለ መቅጣት ሲያስተምሩ፣ ነብያት ሁሌም የክርስቶስ መሰል ባህሪያትን ምጥቀሳችው አስተዋይነታቸው ነው። በመቅጣት ዙሪያ ትምህርት እና ቃልኪዳን በጣም ታዋቂ ምክርን ይሰጠናል፤

“በማሳመን፣ በትእግስት፣ በደግነት፣ እና በትህትና፣ እና ግብዝነት በሌለው ፍቅር ካልሆነ በስተቀር፣ ምንም ሀይል ወይም ተጽዕኖ በክህነት ስልጣን ዘዴ ሊደገፍ አይቻልም ወይም አይገባውም፤

“ይህም በርህራሄ፣ እና ያለግብዝነትና ያለተንኮል መንፈስን በታላቅ በሚያሳድግ ንጹህ እውቀት ብቻ ነው ሊደገፍ የሚችለው፤—

“ሳይረፍድ በቀጥተኛነት መገሰጽ፣ በመንፈስ ቅዱስ በመገፋፋት፤ እና ከዛም የፍቅር ጭማሬን በተከታይነት ማሳየት” (ት. እና ቃ. 121፥41–43)።

ይህ ጥቅስ በንዴት ስንገፋፋ ሳይሆን፣ “በመንፈስ ቅዱስ ስንገፋፋ” እንድንገስጽ ያስተምረናል። መንፈስ ቅዱስ እና ንዴት አንድ ላይ አይሄዱም፣ ምክንያቱም “የጸብ መንፈስ ያለበት ከእኔ አይደለም፣ ከዲያቢሎስ እንጂ፣ እርሱም የጸብ አባት የሆነ እናም የሰዎችን ልብ እርስ በእርስ እንዲጣሉ በቁጣ የሚያነሳሳ ነው።”(3 ኔፊ 11፥29)። ፕሬዘደንት ጆርጅ አልበርት ስሚዝ እንዳስተማሩት “መልካም ያልሆኑ ነገሮች ሁሌም በጌታ መነሳሳት አይደለም የሚነገሩት። የጌታ መንፈስ የቀናነት መንፈስ ነው፤ የታጋሽነት መንፈስ ነው፤ የልግስና እና የፍቅር እና ችሎ የማሳለፍ እና የመታገስ መንፈስ ነው። …

“… ነገር ግን ጥፋት የማግኘት መንፈስ ከሆነ ያለን …በሚያሳስት መልኩ፣ ያ በፍጹም ከሰማይ አባታችን መንፈስ አጋርነት የሚመጣ አይደለም እና ሁሌም ጎጂ ነው።

“…ቀናነት ጠጣር ልቦችን እንድንከፍት እና አስቸጋሪ ነብሶችን እንድንገራ የእግዚአብሔር የሰጠን ሀይል ነው።”9

የልጆቻችን እውነተኛ ማንነት

አዳኝ ኔፋውያንን ሲጎበኝ፣ በልጆች ላይ ለየት ያለ ነገር አድርጎ ነበር፤

አዳኝ ከኔፋውያን ልጆች ጋር

“እናም እንዲህ ሆነ የተነገረላቸውን ሰዎች ልጆችም ኢየሱስ አስተማራቸው… ፣ እናም አንደበታቸውን ፈታላቸው፣ እና ለህዝቡ ኢየሱስ ከገለጸላቸው የበለጡትን ለአባቶቻቸው ታላቅና አስገራሚ የሆኑ ነገሮችን ተናገሩ። …

“… እናም እነዚህን ልጆች ተመለከቷቸው፣ እናም አዳመጧቸው፤ አዎን ህጻናቱም አፋቸውን ከፈቱ፣ እናም አስደናቂ ነገሮችን ተናግሩ” (3 ኔፊ 26፥14፣ 16)።

ስለሆነም የህጻናቱን አፎች ከመክፈት በላይ፣ ጌታ የተደነቁትን የወላጆች አይኖች እና ጆሮዎች እየከፈተ ነበር። እነዛ ወላጆች የዘለአለማዊነትን የምልከታ እና የልጆቻቸውን እውነተኛ ማንነት እና የቅድመ ምድር ገፅታ ልዩ ስጦታ ተሰጥቷቸው ነበር። ያ ወላጆች ልጆቻቸውን የሚያዩበት እና የሚንከባከቡበትን መንገድ ለዘለአለም አይቀይረውምን? ጎአት እንዳለው የተባለበትን ጥቅስ እወደዋለሁ፥ “[ልጅን] የምታዩበት እናንተ የምትንከባከቡበት ነው፣ እናም እናንተ የምንትንከባከቡባቸው መንገድም ማን እንደሚሆኑ ይወስናል።”10 የልጅን እውነተኛ ማንነት ማስታወስ የጻድቅ ዳኛን የሚያነሳሳ እይታን የሚሰጥ የወደፊት እይታ ስጦታ ነው።

ማጠቃለያ

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዳስተማሩን፣ “የሚፈታው ችግር ከሚወደደው ሰው በላይ አስፈላጊ አድርጋችሁ አትመልከቱት።”11 ይህ መሰረታዊ መርሆ ዳድቅ ዳኛዎች ለመሆን እንዴት አስፈላጊ ነው፣ በልዩም ለልጆቻችን።

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያደርገው፣ በጻዲቅ ፍርድ ለመፍረድ አንድ ብቻ መንገድ አለ፣ ያም እርሱ እንደሆነው መሆን ነው። ስለዚህ፣ “ምን አይነት ሰው መሆን ይገባችኋል? እውነት እላችኋለሁ እንደ እኔ ሁኑ” (3 ኔፊ 27፥27)። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “disciple,” etymonline.com-disciple ተመልክቱ።

  2. See Merriam-Webster’s Collegiate Dictionary, 11th ed. (2003), “chasten.”

  3. Karen Lynn Davidson and others, eds., Histories, Volume 1: Joseph Smith Histories, 1832–1844, vol. 1 of the Histories series of The Joseph Smith Papers (2012), 83.

  4. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (2007), 71; emphasis added.

  5. የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “መስዋዕት፣” scriptures.lds.org።

  6. Bible Dictionary፣ “ጸጋ።”

  7. በቅዱስ ቁርባን መሰዊያ ላይ በየሳምንቱ የምናቀርበው የተሰበረ ልብ እና መንፈስ ነው (2 ኔፊ 2፥73 ኔፊ 9፥20ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥8)። የተሰበረ ልብ ንስሀ የሚገባ ልብ ነው፤ የተሰበረ መንፈስ ታዛዥ መንፈስ ነው (ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን፣ “When Thou Art Converted፣” Liahona፣ ግንቦት 2004 (እ.አ.አ)፣ 12)።

  8. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (1998), 299.

  9. Teachings of Presidents of the Church: George Albert Smith (2011), 225226, 228; emphasis added.

  10. Attributed to Johann Wolfgang von Goethe, brainyquote.com.

  11. ቶማስ ኤስ ሞንሰን፣ “Finding Joy in the Journey፣”Liahona, ህዳር 2008 (እ.አ.አ.)፣ 86።