እንዳትረሳ
ወደ ኋላ ተመልሳችሁ እንድታስታውሱ አሁን እናንተን እንደማበረታታችሁ እነሱን አበረታትቻቸዋለሁ፣ በተለይም እምነታችሁ እየተመናመነ እንደመጣ በምታስቡበት ወቅቶች ላይ፣ መንፈስ በተሰማችሁ እና ምስክርነታችሁ ጠንካራ በነበረበት ጊዜ አስታውሱ፤
የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን ዋላችሁ። በዚህ የጉባኤ ወቅት በጣም ተባርከናል። የአስራ ሁለቱ ሀዋሪያት አባል ከሆንኩ አንደኛ አመቴ በጣም ትሁት የሚያደርግ ነው። የመወጠር፣ የእድገት፣ የቅንነት፣ እንዲሁም ለሰማይ አባቴ አቤቱታን ያቀረብኩበት አመት ነበር። የቤተሰብ፣ የጓደኛ፣ እናም በአለም ዙሪያ ያሉ ሁሉ አባላትን ደጋፋዊ ፀሎት ተሰምቶኛል። ለሀሳቦቻችሁ እና ለፀሎቶቻቻሁ አመሰግናለሁ።
እንዲሁም ከፍተኛ ዋጋ ከምሰጣቸውን ጓደኞች ጋር የመገናኘት እድል ነበረኝ፣ አንዳንዶቹ ካለፉት አመታት እና ብዙውን ደሞ በቅርቡ አግኝቻቸዋለሁ። የዛሬውንን ንግግሬን እንድዘጋጅ ግዴታ ያሰማኝ ለብዙ አመታት ከማውቀው እና ከምወደው ውድ ከሆነው ጓደኛዬ ጋር ከተገናኘው በኋላ ነበር።
ስናገኘው፣ ጓደኛዬ መንፈሳዊ ነገሮች ላይ ችግር እንደነበረበት በሚሥጢር ነገረኝ። የራሱን ቃል ለመጠቀም ያክል “እምነቴን ምናልባት አጥቻለሁ፣” ይህ በሱ ላይ እየተከሰተ እንደሆነ ተሰማው፣ እናም ምክሬን አሸ። ስሜቶቹን እና ጭንቀቶቹን ለእኔ በማካፈሉ አመስጋኝነት ተሰማኝ።
ከዚህ በፊት ተሰምቶት የነበረው እና አሁን አጥቼዋለሁ ብሎ ያሰበውን መንፈሳዊነት በድጋሚ እንዲሰማው ያለውን ጥልቅ ምኞት ገለፀ። እየተናገረ እያለ፣ ጌት ምን እንድናገር እንደሚያደርገኝ ለማወቅ በጥሞና ሰማሁት እናም በቅንነት ፀለይኩ።
ጓደኛዬ፣ ምናልባት እንደ አንዳንዳችሁ፣ በመጀመሪያ ክፍል እንደዚህ በደንብ የተጠየቀውን ጥያቄ ጠይቆ ነበር፥ “የሰማይ አባት አንተ በእርግጥም እዛ አለህ እንዴ?”1 ይህንን ተመሳሳይ ጥያቄ ልትጠይቁ ለምትችሉ፣ ለጓደኛዬ ዴቪድ የምሰጠውን ምክር ለእናንተ ማካፈል እፈልጋለሁ እናም እያንዳንዳችሁ እምነታችሁ ጠንክሮ እንድታገኙት እና የተሰጠ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ፅኑ ውሳኔያችሁ እንዲታደስ ተስፋ አደረርጋለሁ።
እናንተ የሰማይ አባት ወንድ እና ሴት ልጆች እንደሆናችሁ እና የእሱ ፍቅር በቋሚነት እንደሚቆይ በማስታወስ እጀምራለሁ። በግል ችግሮች እና ፈተናዎች፣ በብስጭ ወይም ባልተሳኩ ህልሞች መካከል ስትሆኑ አንደዚህ አይነት የፍቅር አፅናኝ መንፈስ ስሜቶችን ለማስታወስ ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ፣
እየሱስ ክርስቶስ ከባድ ሰለሆኑ ትግሎች እና ፈተናዎች ያውቃል። ህይወቱን ለእኛ ሰጠ። የሱ መጨረሻ ሰዓታት ጨካኝ ነበሬ፣ ማሰብ ከምንችለው ነገር በላይ፣ ነገር ግን ለእያንዳንዳችን የከፈለው መስዋትነት የሱ ንፁህ ፍቅር ታላቅ መገለጫ ነው።
ምንም አይነት ስህተት፣ ሀጢያት፣ ወይም ምርጫ እግዚያብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አይቀይረውም። ያ ማለት ሀጢያታዊ ተግባር ተፈቅዷል ማለት አይደለም፣ ወይም ሀጥያት ሲፈፀም ንሰሀ የመግባታችን ገዴታንም አያስወግድም። የሰማይ አባት እያንዳንዳችሁን እንደሚያውቃችሁ እና እንደሚወዳችሁ፣ እናም ሁሌም እናንተን ለመርዳት ዝግጁ እንደሆነ እንዳትረሱ።
የጓደኛዬ ሁኔታ እያሰላሰልጁ እያለሁ፣ አእምሮዬ በመፅሀፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኘውን ታላቅ ጥበብ አሰበ። “እናም አሁን ልጆቼ አስታውሱ፣ የእግዚያብሐየር ልጅ በሆነው በክርስቶስ፣ አዳኝ በሆነው በዓለቱ መሰረታችሁን መገንባት እንዳለባችሁ፣ ዲያብሎስ ሀይሉን ንፋሱን፣ አዎን አውሎ ንፋስ እንደሚወረውር ዘንጉን፣ በላከ ጊዜ፣ አዎን ትክክለኛ መሰረት በሆነው ሰዎች ከገነቡበት ሊወድቁ በማይችሉበት አለት ላይ ስለገነባችሁ በረዶው፣ እናም ኋለኛው ውሽንፍር በሚመታችሁ ጊዜ እናንተ ወደ ስቃይና መጨረሻ ወደሌለው ባህረ ሰላጤ ጎትቶ ለመጣል ኃይል የለውም።”2
“የስቃይ ባህረ ሰላጤ እና ማለቂያ የሌለው ሀዘን” ማንም ሰው ለመሆን የሚፈልገው ቤታ እንዳልሆነ መሰክርላችኋለሁ። እናም ጓደኛዬ ተስፋ እየቆረጠ እንዳለ ትሰማው።
ልክ እንደ ጓደኛዬ፣ ያሉ ግለሰቦችን ምክር ስሰጥ፣ ቅዱስ የሆኑ ተሞክሮዎችን ወደ መርሳት፣ ወደ መድከም፣ ወደ መጠራጠር የሚያመራቸውን በአመታት ውስጥ የተደረጉ ውሳኔዎቻቸውን መርምሬያለሁ፣ ወደ ኋላ ተመልሳችሁ እንድታስታውሱ አሁን እናንተን እንደማበረታታችሁ እነሱን አበረታትቻቸዋለሁ፣ በተለይም እምነታችሁ እየተመናመነ እንደመጣ በምታስቡበት ወቅቶች ላይ፣ መንፈስ በተሰማችሁ እና ምስክርነታችሁ ጠንካራ በነበረበት ጊዜ አስታውሱ፤ የገነባችሁትን መንፈሳው መሰረት አስታውሱ። ምስክርነታችሁን የማይገነመቡ እና የማያጠነክሩ ነገሮችን ወይም እምነታችሁ ላይ ሚሳለቁ ነገሮችን ማስወገድ፣ ይህንን የምታደርጉ ከሆነ፣ እነኛ ምስክርነታችሁ በልፅጎ የነበበት ጊዜያት በትሁት ፀሎት እና ፆም አማካኝነት ወደ ትውስታችሁ እንደገና እንደሚመለሱ ቃል እገባላችኋለሁ። እንደገና የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን ደህንነት እና የሞቀ ስሜት እንደሚሰማችሁ አረጋግጥላችኋለሁ።
እያንዳንችን በመንፈሳዊ እራሳችንን መጀመሪያ ማጠንከር አለብን እናም ከዚያ በዙሪያችን ያሉትን ማጠንከር አለብን። ቅዱስ መፅሀፍትን ሁሌም አሰላስሏቸው፣ ስታነቧቸው የተሰማችሁን ሀሳቦች እና ስሜቶች አስታውሱ። እንዲሁም ሌሎች የእውነት ምንጮችንም እሹ፣ ነገር ግን ከቅዱሳን መፅሀፍ ውስጥ ይህንን ማስጠንቀቂያ መከተላችሁን እርግጠኛ ሁኑ፣ “ነገር ግን የእግዚያብሔርን ምክሮች የሚያዳምጡ ከሆነ መማር መልካም ነው።”3 የቤተ ክርስቲያን ስብሰባዎችን ተካፈሉ፣ በተለየ መልኩ ቅዱስ ቁርባን ስብሰባ፣ ቅዱስ ቁርባንን ውሰዱ እናም ቃልኪዳኖችን አድሱ፣ ሁሌም አዳኝን ለማስታወስ መንፈስ ቅዱስ ሁሌም ከእናንተ ጋር እንዲሆን የሚለውን ቃል የተገባልንንም ጨምሮ።
የሰራነው ስህተት ምንም ቢሆንም ወይም ፍፁም አለመሆናችን ቢሰማንም፣ ሌሎችን ሁሌም በባረክ እና ከፍ ማድረግ እንችላለን። ክርስቶሳዊ በሆነ አገልግሎት ለእነሱ መድረስ በልቦቻችን ውስጥ የእግዚያብሄር ፍቅር እንዲሰማን መርዳት ይችላል።
በዘዳግም ላይ ያለውን ኃይለኛ ምክር ማስታወስ ጠቃሚ ነው፣ “አይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፣ በህይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይወድቅ ተጠንቀቅ፣ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፣ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አስታውቀው።4
በምንመርጣቸው ምርጫዎች ትውልዶች ተጠቂዎች ናቸው። ምስክረነታችሁን ለቤተሰባችሁ አካፍሉ፤ በህይወታቸው ውስጥ መንፈስ ቅዱስን ሲረዱ እንዴት ተሰምቷቸው እንደነበር እንዲያስታውሱ አበረታቷቸው እናም እነኛ ስሜቶችን በግል ለማስታወሻ ደብተር እና የግል ታሪካቸው ላይ መዝግበው አስፈላጊ በሆነ ጊዜ የራሳቸው ቃላቶች ጌታ እንዴት ለእነሱ መልካም እንደነበር ወደ ትውስታቸው ያመጣላቸዋል።
ያለፈው ታሪካቸውን እንዳይረሱ፣ የህዝባቸውን ታሪክ የያዘውን መዝገብ የነሀስ ሰሌዳዎቹን ለማምጣት ኔፊ እና ወንድሞቹ ወደ እየሩሳሌም ተመልሰው እንደሄዱ. ታስታውሳላችሁ።
እንዲሁም፣ በመፅሀፈ ሞርሞን ውስጥ፣ የእግዚያብሐየርን መልካምነት እንዳይረሱ ዘንድ ሄለማን የልጆቹን ስም በመጀመሪያ አባቶቹ ስም ሰየማቸው።
“እነሆ ልጆቼ የእግዚያብሐየርን ትእዛዛት ለመጠበቅእንዲታስታውሱት እፈልጋለሁ፣ እናም እነዚህን ቃላት ለህዝቡ እንድትናገሩ እፈልጋለሁ። እነሆ ከእየሩሳሌም ምድር ለቀው ለቀው የወጡትን የመጀመሪያ ወላጆቻችንን ሰም ሰጠኋችሁ እናም ይህንን ያደረኩት ስማችሁን ስታስቡ እነርሱን ታስታውሱ ዘንድ፣ እናም እነሱን ስታስታውሱ ስራቸውን ታስታውሱ ዘንድ፣ እናም ደግሞ መልካም በመሆንም እንደተፃፉ ታውቃላችሁ።”
”ስለዚህ፣ ልጆች ስለእናንተ የተነገሩትን እናም ደግሞ የተፃፉትንም መልካም ነገሮች የሆኑትን እንደተነገሩት እና እንደተፃፉት እንድታደርጉ እፈልጋለሁ።”5
ብዙ ሰዎች አሁን ላይ፣ ቅርሳቸውን እንዳይረሱ በሚያበረታታ መንገድ ከቅዱሳን መፅሀፍት ላይ ባሉት ጀግኖች ወይም በታማኝ ቅድመ አያቶቻቸውን ስም ለልጆቻቸው የመሰየም ባህል አለ።
እኔ ስወለድ፣ ሮናለድ ኤ. ራዝባንድ የሚል ስም ተሰጥቶኝ ነበር። የመጨረሻ ስሜ ለአባቴን ቅድመ አያት የዘር መስመር ክብር ነው። መሀክል የለው በምፃረ ቃል ያለው ኤ ስም የእናቴን ዳኒሽ አንደርሰን ቅድመ አያቶች እንዳስታውስ ለእኔ የተሰጠ ስም ነው።
የወንድ ቅም ቅድመ አያቴ ጄንስ አንደርሰን ከዴንማርክ ነበር። እናም በ1861 (እ.አ.አ) ጌታ ሁለት የሞርሞን ምስዮናውያንን ወደ እነ ጄንስ እና አኔ ካትሪን አንደርሰን ቤት መራቸው፣ ምስዮናውያው እነሱ እና የ16 አመት ወንድ ልጃቸው ወደ ተመለሰው ወንጌል መሯቸው። እኔ እና ቤተሰቤ ተጠቃሚዎች የሆንበት የእምነት ውርስ እንዲህ ነበር የጀመረው። እነ አንደርሰን መፅሀፈ ሞርሞንን አነበቡ አና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ተጠመቁ። በቀጣዩ አመት፣ አትላንቲክን አቋረጠው በሰሜን አሜሪካ የነበሩትን ቅዱሳን እንዲቀላቀሉ በመጣላቸው የነብይ ጥሪ መሰረት ሄዱ።
በአሳዛኝ ሁኔታ፣ ጄንስ በውቂያኖስ ጉዞ ላይ ህይወቱ አለፈ፣ ነገር ግን ሚስቱ እና ወንድ ልጁ ወደ ሶልት ሌክ ቫሊይ ቀጠሉ፣ እ.አ.አ መስከረም 3፣ 1862 ላይ ደረሱ። መከራ እና ሀዘን የነበረ ቢሆንም አባታቸው በጭራሽ አመንትቶ አያውቅም፣ የእነሱ ብዙ ትውልዶች እምነትም እንደዛው ነበር።
በቢሮዌ ውስጥ በቅድመ አባቶቼ እና በመጀመሪያው ትሁት ሚስዮኖች ጋር ስለነበረው የመጀመሪያ ግንኙነት በወብት የተሳለ ስዕል6 ይገኛል። ውርሴን ላለመርሳት የልብ ውሳኔ አለኝ፣ እናም በስሜም ምክንያት የእነርሱን የታማኝነትና መስዋዕት ቅርስ ለዘለአለም አስታውሳለሁ።
ጥያቄን፣ በጭራሽ አትርሱ፣ ወይም ግለሰብን፣ ቅዱስ የሆኑ መንፈሳዊ ተሞከሮዎችን ችላ አትበሉ። የመከራ እቅድ ከመንፈሳዊ ምስክርነት የኛን ሀሳብ ሊሰርቅ ነው፣ ነገር ግን የጌታ መሻት በእሱ ስራ ውስጥ እንዲገለፅልን እና እንድንሳተፍ ነው።
የዚህን እውነት የግል መሳሌን ላካፍላችሁ እስቲ፣ ለኃይለኛ ፀሎት መልስ መነሻሻ የተቀበልኩበትን ትክክለኛ ጊዜ ማስታወስ አልችልም። መልሱ ግልፅ እና ኃይለኛ ነበር። እንደዛ ቢሆንም፣ በመነሳሳቱ ላይ ለመተግበር አልቻልኩም ነበር፣ እናም ከጊዜ በኋላ፣ ተሰምቶኝ የነበረው ነገር ትክክል ነው አይደለም ብዬ መጠየቅ ጀመርኩ። አንዳንዶቻችሁ ልክ እነደዚሁ ለመከራ ማጭበርበር ወድቃችሁ ሊሆን ይችላል።
ከተወሰኑ ቀናት በኋላ፣ ኃይለኛ ጥቅስ በአእምሮዬ ይዤ ከእንቅልፌ ተነሳሁ።
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ተጨማሪ ምስክር ከፈለክ፣በልብህ ወደ እኔ ትጮህ ዘንድ አእምሮህን በምሽት ላይ አድርግ …
“ጉዳዩን በተመለከተ በአእምሮስ ለላምን አላወራሁህምን? ከእግዚያብሔር የበለጠ ምን አይነት ምስክር ሊኖርህ ይችላልን።7
ጌታ እንዲህ እያለኝ እንደነበር ነው ”አሁን፣ ሮናልድ፣ ምን ማድረግ እዳለብህ አስቀድሜ ነግሬካለሁ፣ አሁን አድርገው“ ለዛ በፍቅር የተሞላ እርማት እና ምሬት በጣም አመስጋኝ ነበርኩ። ፀሎቴ እንደተመለሰ በማወቅ በመነሳሻው ወዲያው ተፅናናው እና ወደፊት ለመሄድ ቻልኩ።
ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ ይህንን ተሞክሮ ያካፈልኩት አእሞሮአችን እንዴት በፍጥነት እንደሚረሳ ለማሳየት እና መንፈሳው ተሞክሮአችን እንዴት እንደሚመሩን ለማሳየት ነው። ለእንደዚህ አይነቶቸወ ጊዜያት ዋጋ መስጠትን “እንዳረሳ” ተማርኩኝ“።
ለጓደኛዬ፣ እና እምነታቸውን ማጠንከር ለሚሹ ሁሉ፣ ይህንን ቃል ገባላችኋለሁ፤ በታማኝነት የእየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስትከተሉ እና ከትምህርቶቹ ጋር ስትጣበቁ፣ ምስክርነታችሁ ይጠበቃል እናም ያድጋልም። በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ተግባር ቢኖርም የገባችሁትን ቃልኪዳን ጠብቁ፣ በግል ምስክርነት በኩል የምትወዷቸውን ሰዎች የምታጠነክሩ እና የቅዱሳን መፅሀፍት ተሞክሮዋችሁን የምታካፍሉ ትጉህ የሆናችሁ ወላጆች፣ ወንድሞች፣ እና እህቶች፣ አያቶች፣ አክስቶች፣ አጎቶች፣ እና ጓደኞች ሁኑ። በሌሎች ሰዎች ተግባረ አማካኝነት የጥርጣሬ ወጀብ ወደ ህይወታችሁ ቢመጣም ታማኝ ሆናቹ ቆዩ እና ፅኑ። በመንፈሳዊ የሚያነቃቃችሁን እና የሚያጠነክራችሁን እሹ። በቀላሉ የሚሰፉት እውነት ተብለው የሚጠሩትን አስወግዱ፣ “የፍቅር፣ የሰላም፣ የትእግስት፣ የቸርነት፣ የበጎነት፣ የእምነት፣ የዋህነት አና እራስ መግዛት።” ስሜቶቻችሁን መመዝገብ አስታውሱ።8
በህይወት ታላቅ ወጀብ ውስጥ፣ እንደ እግዚያብሔር ወንድ እና ሴት ያላችሁን መለኮታው ውርስ ወይም አለም መስጠት ከሚችለው ነገሮች ሁሉ የበለጠውን፣ አንድ ቀን ከእሱ ጋር አብሮ ተመልሶ ለመኖር ያላችሁን ዘላለማዊ እጣ ፈንታ አትርሱ። የአልማን ትሁት እና አስደሳች ፍቅር አስታውሱ፣ “እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞች እንዲህ እላችኋለሁ፣ የልብ መለወጥን የተለማመዳችሁ ከሆነ፣ እናም የአዳኛችሁን የፍቅር ዜማ ለመዘመር ከተሰማችሁ፣ አሁንም ሊሰማችሁ ይችላልን? ብዬ እጠይቃችኋለሁ።9
እምነታቸው መጠንከር አለበት ብለው ለሚሰማቸው ሁሉ፣ አትርሱ! በማለት እማፀናችኋለሁ። እባካችሁ አትርሱ።
ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚያብሔር ነብይ እንደነበር እመሰክራለሁ። እግዚያብሔር አብን እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ እንዳየ እና እንዳናገረ አውቃለሁ። በራሱ ቃል እንደመዘገበው፣ ሁላችንም እናውቅ ዘንድ የራሱን ተሞክሮ መፃፍን ባለመርሳቱ በጣም አመስጋኝ ነኝ።
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስን የረጋ ምስክርነቴን እሰጣለሁ። ህያው እንደሆነ እና ከቤተክርስቲያኑ ራስ ላይ እንደቆመ አውቃለሁ። እነኚህን ነገሮች ለራሴ አውቃቸዋለሁ፣ የሌላ ሰው ድምፅ ወይም ምስክር ጥገኝነት ሳያስፈልገኝ፣ እናም እናንተ እና እኔ ቅዱስ የሆኑትን ዘላለማዊ እውነታዎች በጭራሽ እንዳንረሳ እፀልያለሁ። በጣም የሚጠቅመው ዘላለማዊ ደስታን ብቻ የሚመኙልን ህያው እና አፍቃሪ የሆኑ የሰማይ ወላጆች ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ነን። እነኚህን እውነቶች በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለሁ፣ አሜን።