የክርስቶስ ትምህርት
ይህም አሁን ከምንገኝበት መንፈሳዊ ሁኔታ እንደ ክርስቶስ ፍጹም ለመሆን ወደምንችልበት ሁኔት ከፍ የሚያደርገን የመንፈስ ሀይልን ለማግኘት የሚፈቅድልን የክርስቶስ ትምህርት ነው።
ኢየሱስ ከትንሳኤው በኋላ ኔፋውያንን የጎበኘበት እኛን ታላቅ አስፈላነት ያላቸውን ነግሮች ለማስተማር በጥንቃቄ የተደራጀ ነበረር። ይህም የጀመረው አብ ለህዝቡ ኢየሱስ “በእርሱ ደስ የሚለኝ፤ ስሜንም የማከብርበት የምወደው ልጄ ይህ” ነው ብሎ በመሰከረበት ነበር።1 ከዚያም ኢየሱስ ራሱም ወረደ እናም2 ሰዎች እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ “በእርግጥ ለምዋወቅ” እንዲችሉ ዘንድ መጥተው እና የቁስሉን ምልክት በጎኑ እና የምስማር ምልክትን በእጆቹ እና በእግሮቹ እንዲነኩት በመጋበዝ3 ስለኃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ መሰከረ። እነዚህ ምስክሮች የኢየሱስ የኃጢያት ክፍያ እንደተፈጸመ እና አብ አዳኝ ለማቅረብ የገባውን ቃል እንዳሟላ ያለጥርጣሬ የሚመሰርቱ ናቸው። ከዚያም በአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ለእኛ እንዲገኙ የተደረጉትን የአብ የደስታ እቅድ በረከቶችን በሙሉ ኔፋውያን እንዴት እንደሚያገኙ የክርስቶስ ትምህርትን ኢየሱስ አስተማራቸው።4
ዛሬ መልእክቴ በክርስቶስ ትምህርት ላይ ያተኩራል። ቅዱሳት መጻህፍት የክርስቶስ ትምህርትን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያም እምነት መለማመድ፣ ንስሀ መግባት፣ መጠመቅ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን መቀበል፣ እና እስከመጨረሻ መፅናት እንደመሆን ትርጉም ይሰጡታል።5
የክርስቶስ ትምህርት የክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በረከቶችን እንድናገኝ ይፈቅድልናል።
የክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ “በቅዱሱ መሲህ መልካም ሥራ፣ እና ምህረትና ፀጋ፣”6 “[በክርስቶስ]፣ ፍጹም እንድንሆን፣”7 ሁሉንም መልካም ነገሮች እንድናገኝ፣ 8 እና የዘለአለም ህይወት እንድናገኝ9 የምንመካባቸውን ሁኔታዎች ይፈጥርልናል።
የክርስቶስ ትምህርት በሌላም በኩል በኢየሱስ የኃጢያት ክፍያ በኩል እንዲገኙልን የተደረጉትን በረከቶች በሙሉ ለማግኘት የምችልበት መንገድ–ብቸኛ መንገድ–ነው። ይህም አሁን ከምንገኝበት መንፈሳዊ ሁኔታ እንደ ክርስቶስ ፍጹም ለመሆን ወደምንችልበት ሁኔት ከፍ የሚያደርገን የመንፈስ ሀይልን ለማግኘት የሚፈቅድልን የክርስቶስ ትምህርት ነው።10 ስለዚህ በዳግም መወለድ፣ ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እንዲህ አስተምረዋል፥ “እንደገና መወለድ፣ ከአካላዊ መወለድ የተለየ ሆኖ፣ ከክስተት ይልቅ ሂደት ነው። በዚህ ሂደት መሰማራት የሟች ህይወት ማዕከላዊ አላማ ነው።”11
የክርስቶስ ትምህርትን እያንዳንድ ክፍል እንመርምር።
መጀመሪያ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው ማመን። ነቢያት እምነት የሚጀምረው የክርስቶስ ቃልን በማዳመጥ ነው ብለው አስተምረዋል።12 የክርስቶስ ቃላት ስለኃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ ይመሰክራሉ እናም ንስሀ፣ በረከቶችን፣ እና ከፍተኛነትን ለማግኘት እንዴት እንደምንችል ይመሰክራሉ።13
የክርስቶስ ስምን በምንሰማበት ጊዜ፣ የአዳኝን ትምህርቶች እና ምሳሌ ለመከተል እምነትን እንለማመዳለን።14 ይህን ለማድረግ፣ “ለማዳን ኃያል በሆነው [ክርስቶስ]፣ በመልካም ስራው ሙሉ በሙሉ በመተማመን” መመካት እንደሚገባን ኔፊ አስተምሯል።15 ኢየሱስ በቅድመ ምድር ህይወት አምላክ ስለነበረ፣16 ኃጢያት በሌለው ህይወት ስለኖረ፣17 እና በኃጢያት ክፍያው ጊዜ የፍትህ ፍላጎትን ለእናንተ እና ለእኔ ስላሟላ፣18 የሰዎችን ሁሉ ትንሳኤ ለማምጣት ሀይል እና ቁልፎች አሉት፣19 እናም ምህረት ፍትህን በንስሀ በኩል ለማሸነፍ እንድትችል አድርጓል።20 ያን ከተረዳን በኋላ በክርስቶስ መልካም ስራ በኩል ምህረትን ለማግኘት እንችላለን፣ ”ለንስሀ እምነት”21 ለማግኘትም እንችላለን። በክርስቶስ መልካም ስራ ሙሉ ለሙሉ መተማመንም እኛን ለማዳን የሚያስፈልገውን እንዳደረገ ማመን እና ከዚያም በእምነታችን መስራት ነው።22
እምነት ሌሎች ስለእኛ ምን እንደሚያስቡ ግድ አንዳይኖረን እና እግዚአብሔር በሚያስብበን ላይ ተጨማሪ ግድ እንዲኖረን እንድንጀምር ያደርጋል።
ሁለተኛ፣ ንስሀ መግባት። ላማናውያን ሳሙኤል እንዳስተማረው፣ “በስሙ ካመናችሁ፣ ለኃጢአታችሁ ሁሉ ንስሃን [ትገባላችሁ]።”23 ንስሀ መግባት በአንድያ ልጁ መስዋዕት ለመሆን የቻለ በሰማይ አባታችን የተሰጠ ውድ ስጦታ ነው። ይህም ሀሳባችንን፣ ስራችንን፣ እና ራሳችንን በተጨማሪ እንደ አዳኝ ለመሆን የምቀየርበት ወይም የምናዞርበት አብ የሰጠን ሂደት ነው።24 ይህም ለትልቅ ኃጢያት ብቻ አይደለም፣ ግን ይህም ኃጢያታችንን፣ ደካማነታችንን፣ እና ብቁ አለመሆናችንን 25 የምናቸንፍበት በየቀኑ ራሳችንን የምንመዝንበት እና የምናሻሽልበት ሂደት ነው።26 ንስሀ መግባት የክርስቶስ “እውነተኛ ተከታዮች” እንድንሆን ያደርገናል፣ ይህም በፍቅር ይሞላናል፣27 እናም ፍርሀታችንን ያስወጣል።28 ንስሀ መግባት ፍጹም ህይወት ለመኖር ያለን አላማ የማይሳካ ከሆነ ተብሎ የሚደረግ ረዳት አላማ አይደለም።29 ሁልጊዜ ንስሀ መግባት የሚቀጥል ደስታ የሚያመጣልን እና ከሰማይ አባታችን ጋር ለመኖር ለመመለስ የሚያስችለን መንገድ ነው።
ንስሀ በመግባት ለእግዚአብሔር ፍላጎት ተገዢና ታዛዥ እንሆናለን። አሁን፣ ይህ የሚደረገው በብቻ አይደለም። የእግዚአብሔርን በጎነት እና ራሳችን የማንረባ መሆናችንን ማወቅ፣30 ጸባያችንን ከእግዚአብሔር ፍላጎት ጋር አንድ ለማድረግ ካለን ጥረት ጋር ማጣመር፣31 በህይወታችን ጸጋን ያመጣል።32 ጸጋ “በራሳችን ችሎታ ከተተውን ለመቀጠል የማንችለውን መልካም ስራዎችን ለማድረግ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የተትረፈረፈ ምህረት እና ፍቅር በኩል እርዳታ ወይም ጥንካሬ የሚሰጥበት መንገድ ነው።”33 ንስሀ መግባት፣ በራሳችን ለማድረግ ከባድ የሆነው፣ እንደ አዳኝ እንደ መሆን ስለሆነ፣ በህይወታችን አስፈላጊ የሆኑ ለውጦችን ለማድረግ የአዳኝን ጸጋ በጣም እንፈልገዋለን።
ንስሀ ስንገባ፣ የድሮውን፣ ጻድቅ ያልሆነ ጸባያትን፣ ደካማነቶችን፣ ፍጹም አለመሆንን፣ እና ፍርሀቶችን ወደ አዳኝ በሚያቀርቡን እና እንደ እርሱ ለመሆን በሚረዱን በአዲስ ጸባዮች እና እምነቶች እንተካቸዋለን።
ሶስተኛ፣ ጥምቀት እና ቅዱስ ቁርባን። ነቢዩ ሞርሞን “የንስሀ የመጀመሪያ ፍሬ ጥምቀት ነው” ብሎ አስተምሯል።34 የተፈጸመ ለመሆን፣ ንስሀ መግባት የእግዚአብሔር የክህነት ስልጣን በያዘ ሰው ከሚፈጸም ጥምቀት ስርዓት ጋር መጣመር አለበት። ለቤተክርስቲያኗ አባላት፣ በጥምቀት እና በሌላ ጉዳዮች የሚገቡ ቃል ኪዳኖች ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል ይታደሳሉ።35
በጥምቀት እና በቅዱስ ቁርባን ስርዓቶች፣ የአብ እና ወልድ ትእዛዛትን ለመጠበቅ፣ ክርስቶስን ሁልጊዜ፡ለማስታወስ፣ እና የክርስቶስን ስም (ወይም ስራውነና ጸባዩን36) በራሳችን ላይ ለመውሰድ ቃል እንገባለን።37 አዳኝም፣ በመልስ፣ የእኛን ኃጢያት ለመማር፣ ወይም ለመሰረይ፣38 እና “መንፈሱን በብዛት [በእኛ] ላይ ለማፍሰስ ቃል ኪዳን ይገባል።”39 ክርስቶስ ደግሞም እንደ እርሱ እንድንሆን በመርዳት ለዘለአለም ህይወት እንደሚያዘጋጀንም ቃል ገብቷል።40
የወጣት ወንዶች አጠቃላይ ፕሬዘዳንት ዳግላስ ዲ. ሆልምን እንዲህ ጽፈዋል፥ “የጥምቀት ስርዓት እና ቅዱስ ቁርባን እንደገና የመወለድ የመጨረሻ ውጤትን እና ሂደትን በምሳሌ የሚያሳዩ ናቸው። በጥምቀት፣ የስጋ ሽማግሌ ሰውን ነቀብራለን እናም ወደ ህይወት አዲስነት እንመለሳለን።41 በቅዱስ ቁርባን ውስጥ፣ ይህም ሂደት ትንሽ በትንሽ፣ ሳምንት በሳምንት፣ ንስሀ ስንገባ፣ እና በመንፈሳዊ ስጦታች መንፈስ ስናድግ (እንደ አዳኝ በመሆን] የምንለወጥበት፣ እርምጃ በእርምጃ የሚከናወን ለውጥ እንደሆነ እንማራለን።”42
ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች በክርስቶስ ትምህርት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ናቸው። የክህነት ስርዓቶችን በብቁነት በመቀበል እና ከነርሱ ጋር የተያያዙትን ቃል ኪዳኖች በመጠበቅ ነው ያ የአምላክነት ሀይል በህይወታችን ውስጥ የሚታየው።43 ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እንደገለጹት “ይህ ‘የአምላክነት ሀይል’ በግል እና በመንፈስ ቅዱስ ተፅእኖ በኩል ይመጣል።”44
አራተኛ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ። ከጥምቀት በኋላ በመረጋገጥ ስርዓት በኩል የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ይሰጠናል።45 ይህም ስጦታ፣ ከተቀበልነው፣ የእግዚአብሔር የሚቀጥል ደጋፊነት እንዲኖረን46 እናም ከእርሱ ተፅዕኖ ጋር አብሮ ያለውንም ጸጋ እንድናገኝ ይፈቅድልናል።
ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንደሚገኝ ጓደኛ፣ መንፈስ ቅዱስ ተቃል ኪዳኖቻችንን ለመጠበቅ ተጨማሪ ሀይል ወይም ጥንካሬ ይሰጠናል።47 ደግሞም ይቀድሰናል፣48 ይህም ማለት፣ “በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ከኃጢያት ነጻ፣ ንጹህ እና ቅዱስ”49 ያደርገናል። የመቀደስ ሂደት የሚያጸዳን ብቻ ሳይሆን፣ ግን ይህም በሚያስፈልገው መንፈሳዊ ስጦታ ወይም መለኮታዊ በሆነው የአዳኝ ጸባይ ይባርከናል50 እናም ፍጥረታችንን ይቀይራል፣51 በዚህም “ከእንግዲህ ኃጢአት ለመፈፀም ምንም ፍላጎት የለንም።”52 በእምነት፣ በንስሀ፣ በስርዓቶች፣ በክርስቶስ አይነት አገልግሎት፣ እና ሌሎች ጻድቅ ጥረቶች መንፈስ ቅዱስን ወደ ህይወታችን በምንቀበልበት በእያንዳዱ ጊዜ፣ እርምጃ በእርምጃ፣ ትንሽ በትንሽ እንደ ክርስቶስ አይነት ለመሆን አንቀየራለን።53
አምስተኛ፣ እስከመጨረሻ መፅናት። ነቢዩ ኔፊ እንዳስተማረው፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ከተቀበልን በኋላ “የህያው እግዚአብሔርን ልጅ ምሳሌን በመከተል ሰው እስከመጨረሻው [መፅናት”54 አለብን። ሽማግሌ ዴል ጂ. ራንለንድ የመፅናት ሂደትነንዲሚቀጥለው ገልጸዋል፥ “[በክርስቶ] እምነትን በመለማመድ፣ ንስሀ በመግባት፣ ቃል ኪዳኖችን እና የጥምቀት በረከቶችን ለማሳደስ ቅዱስ ቁርባንን በመውሰድ፣ እና መንፈስ ቅዱስን ሁሌ እንደሚገኝ ጓደኛ በመቀበል፣ በተደጋጋሚ …ፍጹም ለመሆን እንችላለን። ይህን ስናደርግም፣ በተጨማሪም እንደ ክርስቶስ እንሆናለን እናም፣ ከዚህም ጋር በተያያዘው ሁሉ ጋር፣ እስከመጨረሻ ለመፅናት እንችላለን።”55
በሌላም አባባል፣ መንደስ ቅዱስን እና ያን በመቀበል በውስጣችን የሚፈጥረውን ለውጥ መቀበል እምነታችንን በተጨማሪ ይገነባል። ያደገም እምነት ወደ ተጨማሪ ንስሀ መግባት ይመራል። ልባችንን እና ኃጢያቶቻችንን በቅዱስ ቁርባን መሰዊያ ላይ በምሳሌ እንደ መስዋዕይ ስናቀርብ፣ መንፈስ ቅዱስን በታላቅ ደረጃ እንቀበላለን። መንፈስ ቅዱስን በታላቅ ደረጃ መቀበል እንደገና ወደመወለድ መንገድ ላይ ወደፊት ይገፋናል። በዚህ ሂደት ስንቀጥል እና የሚያድኑ የወንጌል ስርዓቶችን እና ቃል ኪዳኖችን ስናገኝ፣ ሙላትን እስከምንቀበል ድረስ “ጸጋ ለጸጋ” እንቀበላለን።56
የክርስቶስ ትምህርቶችን በህይወታችን ውስጥ መቀበል አለብን።
ወንድሞች እና እህቶች፣ የክርስቶስ ትምህርቶችን በህይወታችን ውስጥ ስንቀበል፣ በፈተናዎቻን ውስጥም በጊዜአዊ እና መንፈሳዊ ሁኔታ እንባረካለን። በመጨረሻም “መልካም የሆኑትን ሁሉ ለመያዝ” እንችላለን።57 ይህ ሂደት በህይወቴ ውስጥ እርምጃ በእርምጃ፣ ትንሽ በትንሽ እንደደረሰ እንደ በመድረስ እንሚቀጥል እመሰክራለሁ።
ነገር ግን ከዚህም ይበልጥ፣ የክርስቶስን ትምህርት በህይወታችን ውስጥ መጠቀም አለብን ምክንያቱም ይህም ወደ ሰማይ አባታችን የሚመልስ ብቸኛ መንገድ ይሰጣልና። አዳኝን የምንቀበልበት እና የእርሱ ወንድና ሴት ልጆች ለመሆን የምንችልበት መንገድ ይህ ብቻ ነው።58 በእርግጥም፣ ከኃጢያት ቤዛ ለማግኘት እና በመንፈስ ለማደግ የሚቻልበት መንገድ የክርስቶስን ትምህርት በህይወታችን ውስጥ በመጠቀም ብቻ ነው።59 በምትኩም፣ ሐዋርያው ዮሀንስ “በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው …አምላክ የለውም” ብሎ አስተምሯል።60 እና ኢየሱስ ራሱም ለኔፍውያን አስራ ሁለት እንደነገረው፣ በክርስቶስ እምነትን ካልተለማመድን፣ ንስሀ ካልገባን፣ ካልተጠመቅን፣ እና እስከመጨረሻ ካልጸናን፣ እኛም “ መጨረሻ ወደሌለው፣ ወደእሳቱ [እንጣላለን]፣ ከዚህም ለመመለስ [አንችልም]።”61
ይህን የክርስቶስ ትምህርት እንዴት በሙላት በህይወታችን ውስጥ ለመጠቀም እንችላለን? አንደኛው መንገድ በየሳምንቱ በየትኛው ላይ በተጨማሪ ለመሻሻል እንደሚያስፈልገን በጸሎት በማሰብ ለቅዱስ ቁርባን ለመዘጋጀት የህሌና ጥረት ማድረግ ነው። ከዚያም እንደ ክርስቶስ ለመሆን የሚከለክለንን አንድም ነገር ወደ ቅዱስ ቁርባን መሰዊያ ላይ እንደ መስዋዕት ለማምጣት፣ ለእርዳታ በእምነት ለመለመን፣ አስፈላጊ የሆኑ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለመጠየቅ፣ እናም በሚቀጥለው ሳምንት ለመሻሻል ቃል ለመግባት እንችላለን።62 እንዲህም ስናደርግ፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ ህይወታችንበታላቅ ደረጃ ይመጣል፣ እናም ፍጹም ያልሆንንባቸውን ለማሸነፍ ተጨማሪ ጥንካሬ ይኖረናል።
ኢየሱስ የአለም አዳኝ እንደህነ እና ለመዳን የምንችልበት ስም የእርሱ ብቻ እንደሆነ እመሰክራለሁ።63 መልካም የሆኑ ነገሮች በሙሉ የሚገኙት በእርሱ በኩል ባቻ ናቸው።64 ነገር ግን “ሁሉንም መልካም ነገሮች ለመያዝ፣”65 በተጨማሪ የዘለአለም ህይወትንም፣ የክርስቶስ ትምህርትን ሁልጊዜ በህይወታችን ውስጥ መጠቀም ያስፈልገናል። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።