የጥናት እርዳታዎች
መንፈስ ቅዱስ


መንፈስ ቅዱስ

የአምላክ ሶስተኛው አባል (፩ ዮሐ. ፭፥፯ት. እና ቃ. ፳፥፳፰)። እርሱም የስጋ እና አጥንት ሰውነት የሌለው የመንፈስ ሰው ነው (ት. እና ቃ. ፻፴፥፳፪)። መንፈስ ቅዱስ በብዙ ጊዜ እንደ መንፈስ ወይም እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ይጠቆማል።

መንፈስ ቅዱስ በደህንነት አላማ ውስጥ የተለያዩ አስፈላጊ ሀላፊነቶች አለው። (፩) ስለአብ እና ወልድ ምስክር ይሰጣል (፩ ቆሮ. ፲፪፥፫፫ ኔፊ ፳፰፥፲፩ኤተር ፲፪፥፵፩)። (፪) ስለሁሉም ነገሮች እውነትን ይገልጻል (ዮሐ. ፲፬፥፳፮፲፮፥፲፫ሞሮኒ ፲፥፭ት. እና ቃ. ፴፱፥፮)። (፫) ንስሀ የገቡትን እና የተጠመቁትን ይቀድሳል (ዮሐ. ፫፥፭፫ ኔፊ ፳፯፥፳ሙሴ ፮፥፷፬–፷፰)። (፬) እርሱም ቅዱስ የተስፋ መንፈስ ነው (ት. እና ቃ. ፸፮፥፶–፶፫፻፴፪፥፯፣ ፲፰–፲፱፣ ፳፮)።

የመንፈስ ቅዱስ ሀይል ሰው ከመጠመቁ በፊት ለመምጣትና ወንጌሉ እውነት እንደሆነ ለመመስከር ይችላል። ነገር ግን ሰው ብቁ በሚሆንበት ጊዜ፣ የመንፈስ ቅዱስ የማያቋርጥ ጓደኝነት ሀይል ወደ እውነተኛዋ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፈቃድ ከተሰጠበት ጥምቀት በኋላ በመልከ ጼዴቅ የክህነት ባለስልጣን እጅ በመጫን በኩል ለመቀበል የሚቻል ስጦታ ነው።

መንፈስ ቅዱስን ከመስደብ በስተቀር ሁሉም ኃጢያቶች ለመሰረይ ይችላሉ ብሎ ኢየሱስ አስተምሯል (ማቴ. ፲፪፥፴፩–፴፪ማር. ፫፥፳፰–፳፱ሉቃ. ፲፪፥፲ዕብ. ፮፥፬–፰ት. እና ቃ. ፸፮፥፴፬–፴፭)