የኤጲስ ቆጶስ አመራር በቤተክርስቲያኗ ውስጥ አጠቃላይ ባለስልጣን። በቤተክርስቲያኗ ምድራዊ ደህንነት ላይ አጠቃላይ ሀላፊነት አለው (ት. እና ቃ. ፻፯፥፷፰)። የአጠቃላይ ባለስልጣን የሆኑት የኤጲስ ቆጶስ አመራር እና አማካሪዎቹ በቤተክርስቲያኗ የአሮናዊ የክህነት ባለስልጣኖችን በሙሉ ይመራሉ (ት. እና ቃ. ፷፰፥፲፮–፲፯፤ ፻፯፥፸፮፣ ፹፯–፹፰)። ኤድዋርድ ፓርትሪጅ ኤጲስ ቆጶስነት ይሾም, ት. እና ቃ. ፵፩፥፱. ኤጲስ ቆጶሳት በቀዳሚ አመራር ይጠሩ እና ይለዩ, ት. እና ቃ. ፷፰፥፲፬–፲፭. በኩራት የሆኑ፣ የአሮን ተወላጅ የሆኑት በቀዳሚ አመራር ለመሪነት ለመጠራት፣ መለየት፣ እና ለመሾም መብት አላቸው, ት. እና ቃ. ፷፰፥፲፮፣ ፲፰–፳. በቀዳሚ አመራር ፊት ብቻ ነው ለፍርድ የሚቀርቡት, ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፪–፳፬ (ት. እና ቃ. ፻፯፥፹፪).