የአዳም እና የሔዋን ውድቀት
የሰው ዘር በእዚህች ምድር ላይ ሟች የሆነበት ሁኔታ። አዳም እና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ በበሉበት ጊዜ፣ ሟች፣ የኃጢያት እና ሞት ተገዢ ሆኑ። አዳም በምድረም ላይ “የመጀመሪያ ስጋ” ሆነ (ሙሴ ፫፥፯)። የኋለኛው ቀን ራዕይ ውድቀት በረከት እንደሆነ እናም አዳምና ሔዋን እንደ ሰው ዘር ሁሉ የመጀምሪያ ወላጆች መከበር እንዳለባቸው ግልፅ አደረገ።
ውድቀት በሰው እድገት አስፈላጊ የሆነ እርምጃ ነበር። እግዚአብሔር ውድቀት እንደሚመጣ ስላወቀ፣ በቅድመ ምድራዊ ህይወት ለአዳኝ እቅድ አድርጎ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም ውድቀት ደግሞም በሰው ንስሀ መግባት በኩል ለሰው የግል ኃጢያቶች የኃጢያት ዋጋን ለመክፈል በመካከለኛው ዘመን መጣ።