አሮን፣ የሙሴ ወንድም ደግሞም ሙሴ; አሮናዊ ክህነት ተመልከቱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የሌዊ ነገር የእንበረምና የዮካብድ ወንድ ልጅ (ዘፀአ. ፮፥፲፮–፳)፤ የሙሴ ታላቅ ወንድም (ዘፀአ. ፯፥፯)። የእስራኤል ልጆችን ከግብፅ ለማምጣት ሙሴን እንዲረዳ እና የእርሱ ቃል ተቀባይ እንዲሆን በጌታ ተመድቦ ነበር, ዘፀአ. ፬፥፲–፲፮፣ ፳፯–፴፩፤ ፭፥፩–፲፪፥፶፩. በሲና ተራራ ላይ፣ ሙሴ ስለአሮንና አራት ወንዶች ልጆቹ ወደ አሮናዊ ክህነት መመደብ መመሪያ ተቀበለ, ዘፀአ. ፳፰፥፩–፬. ህዝቦች ስለጠየቁት የወርቅ ጥጃ ሰራ, ዘፀአ. ፴፪፥፩–፮፣ ፳፩፣ ፳፬፣ ፴፭. በ፻፳፫ አመቱ በሆር ተራራ ላይ ሞተ, ዘኁል. ፳፥፳፪–፳፱ (ዘኁል. ፴፫፥፴፰–፴፱). ጌታ ክህነትን በአሮን እና በዘሩ ላይ አረጋገጠ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፲፰፣ ፳፮–፳፯፣ ፴. የክህነት ጥሪያቸውን የሚያጎሉ የሙሴ እና የአሮን ልጆች ይሆናሉ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፴፫–፴፬.