የጥናት እርዳታዎች
ወደ ፊልጵስዮስ መልእክት


ወደ ፊልጵስዮስ መልእክት

ጳውሎስ በፊልጵስዮስ ውስጥ ላሉት ቅዱሳን ለመጀመሪያ ጊዜ በሮሜ ውስጥ በእስር ቤት እያለ የጻፈው ደብዳቤ ነበር። አሁን ይህም በአዲስ ኪዳን ውስጥ ወደ ኢልጵስዮስ መልእክት የሚባል መፅሐፍ ነው።

ምዕራፍ ፩ የጳውሎስን ሰላምታ እና ስለአንድነት፣ ትሁትነት፣ እና ስለመፅናት የሚሰጠው መመሪያን የያዘ ነው። ምዕራፍ ፪ ሁሉም ለክርስቶስ እንደሚሰግዱ እና እያንዳንዱ ሰው የእራሱን ደህናነት ለመፈጸም እንደሚገባቸው ትኩረት ይሰጣል። በምዕራፍ ፫ ውስጥ፣ ጳውሎስ ሁሉንም ነገሮች ለክርስቶስ መስዋዕት እንዳደረገ ይገልጻል። በምዕራፍ ፬ ውስጥ፣ ጳውሎስ የፊልጵስዮስ ቅዱሳንን ለእርዳታቸው ያመሰግናል።