መመኘት ደግሞም ቅናት ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ እንደሚጠቀሙት፣ መመኘት በሰው መቅናት ወይም ለአንድ ነገር ከመጠን በላይ የሆነ ፍላጎት መኖር ነው። አትመኝ, ዘፀአ. ፳፥፲፯ (ዘዳግ. ፭፥፳፩; ሞዛያ ፲፫፥፳፬; ት. እና ቃ. ፲፱፥፳፭). ግፍን የሚጠላ ግን ብዙ ዘመን ይኖራል, ምሳ. ፳፰፥፲፮. በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ ይነጥቃሉ, ሚክ. ፪፥፪. ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ, ሉቃ. ፲፪፥፲፭. ህጉ አይመኝ አለ, ሮሜ ፯፥፯. በመጨረሻው ቀናት ሰዎች ትምክህተኞች ይሆናሉ, ፪ ጢሞ. ፫፥፩–፪. ላባን ንብረታችንን ሲያይ፣ ተመኘው, ፩ ኔፊ ፫፥፳፭. የራስህን ንብረት አትመኝ, ት. እና ቃ. ፲፱፥፳፮. ትምክህተኞች አትሁኑ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፳፫. የወንድማችሁ የሆነውን አትመኙ, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፳.