እርሻ ደግሞም አለም; የጌታ የወይን አትክልት ስፍራ ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ለማሳደጊያ ወይም ለመጋጫ የሚጠቀሙበት ምድር። ብዙ ጊዜም ይህ አለምንና ህዝቦቿን ያመለክታል። እርሻውም ዓለም ነው, ማቴ. ፲፫፥፴፰. መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች, ማቴ. ፲፫፥፵፬. ትልቅና ሰፊ የሆነን ሜዳ ተመለከትኩ, ፩ ኔፊ ፰፥፱፣ ፳. እርሻው ተዘጋጅቷል, አልማ ፳፮፥፭. የእርሻው ስፍራ ነጭ ሆኖ ለመከር ዝግጁ ነው, ት. እና ቃ. ፬፥፬ (ት. እና ቃ. ፮፥፫; ፲፩፥፫; ፲፪፥፫; ፲፬፥፫; ፴፩፥፬; ፴፫፥፫፣ ፯). እርሻው አለም ነበር, ት. እና ቃ. ፹፮፥፩–፪. እነዚህን መንግስቶች መሬት እንዳለው ሰው አመሳስላለሁ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፶፩.