ቀድሞ መመረጥ ደግሞም ቅድመ ምድራዊ ህይወት ተመልከቱ እግዚአብሔር የኃያል የመንፈስ ልጆቹ በስጋዊ ህይወታቸው አንዳንድ ሚስዮኖችን እንዲያሟሉ በቅድመ ምድር አስቀድሞ መምረጡ። እግዚአብሔር የአሕዛብን ድንበር አቆመ, ዘዳግ. ፴፪፥፰. በሆድ ሳልሠራህ ነቢይ አድርጌሃለሁ, ኤር. ፩፥፭. እግዚአብሔር የተወሰኑትን ዘመኖች መደበላቸው, የሐዋ. ፲፯፥፳፮. አስቀድሞ ያወቃቸው፣ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአል, ሮሜ ፰፥፳፰–፴. ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ እንሆን ዘንድ መረጠን, ኤፌ. ፩፥፫–፬. ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንዲሆን ቀድሞ ተመርጧል, ፩ ጴጥ. ፩፥፲፱–፳ (ራዕ. ፲፫፥፰). ከአለም መመስረት በፊት ተጠርተውና ተዘጋጅተው ነበር, አልማ ፲፫፥፩–፱. ተመረጡት በተከበሩትና በታላቆቹ መካከል እንደነበሩም አየሁ, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፶፭–፶፮. ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ የተመረጠው ተወዳጁ ልጄ, ሙሴ ፬፥፪. አብርሐም ከመወለዱ በፊት ተመርጦ ነበር, አብር. ፫፥፳፫.