ሴት፣ ሴቶች ደግሞም ሰው፣ ሰዎች; እህት; ወንድሞች፣ ወንድም ተመልከቱ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ የሆነች ጎልማሳ ሴት። ሴትን አንዳንድ ጊዜ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ እንደ ክብር ርዕስ ይጠቀሙበታል (ዮሐ. ፲፱፥፳፮፤ አልማ ፲፱፥፲)። እግዚአብሔርም ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው, ዘፍጥ. ፩፥፳፯ (ሙሴ ፪፥፳፯; ፮፥፱; አብር. ፬፥፳፯). የምግባረ ጥሩ ሴት ዋጋ ከቀይ ዕንቁ በላይ ታላቅ ነው, ምሳ. ፴፩፥፲–፴፩. ሴት የወንድ ክብር ናት, ፩ ቆሮ. ፲፩፥፯. ነገር ግን በጌታ ዘንድ ሴት ያለ ወንድ ወንድም ያለ ሴት አይሆንም, ፩ ቆሮ. ፲፩፥፲፩. ሴቶች በሚገባ ልብስ ሰውነታቸውን ይሸልሙ, ፩ ጢሞ. ፪፥፱–፲. እኔ ጌታ እግዚአብሔር በሴቶች ንፅህና እደሰታለሁ, ያዕቆ. ፪፥፳፰. ኃጢያትሽ ተሰርዮልሻል፣ እናም አንቺ የተመርጥሽ ሴት ነሽ, ት. እና ቃ. ፳፭፥፫. ሴቶች፣ በባሎቻቸው የመደገፍ መብት አላቸው, ት. እና ቃ. ፹፫፥፪.