የጥናት እርዳታዎች
ከነዓን፣ ከነዓናውያን


ከነዓን፣ ከነዓናውያን

በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የካም አራተኛ ልጅ (ዘፍጥ. ፱፥፳፪፲፥፩፣ ፮) እና የኖኅ የልጅ ልጅ። ከነዓናውያን ከነዓን በመጀመሪያ ከኖረበት ምድር የመጣ ሰው እና የእርሱ ትውልዶች የሚጠሩበት ነው። ከነዓናውያንም በፍልስጥኤም በሜዲትሬንያን ባህር ዳር አካባቢ ቆላ ውስጥ ለሚኖሩት ህዝቦች የተሰጠ ስም ነው። ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ባለ ሀገር፣ ግሪኮች ፊኖሺያን ብለው የሚጠሩአቸውን እስራኤላውያን ያልሆኑ ነዋሪዎችን አንዳንዴ ለመግለፅ የሚጠቀሙበት ስም ነበር።