ኃጢያት ደግሞም ኃጢያተኛ፣ አመፃ; መበደል; አመጽ; አስጸያፊ፣ አስከፊ፣ አሰቃቂ፣ ርኩሰት; እድፍ፣ እድፍነት; እግዚአብሔርን የሚጠላ; ክፉ፣ ክፋት ተመልከቱ ለእግዚአብሔር ትእዛዛት በፈቃደኛነት ታዛዥ አለመሆን ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም, ምሳ. ፳፰፥፲፫. ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች, ኢሳ. ፩፥፲፰. ኃጢያተኞች ይሞታሉ፣ እናም ጻድቃን ይድናሉ, ሕዝ. ፲፰. የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት ያስወግዳል, ዮሐ. ፩፥፳፱. ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ, የሐዋ. ፳፪፥፲፮. የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው, ሮሜ ፮፥፳፫. በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው, ያዕ. ፬፥፲፯. ኃጢያትን በምመለከትበት ወቅት በጥላቻ ታንቀጠቅጠኛለህን, ፪ ኔፊ ፬፥፴፩. በኃጢአታቸው ለሚሞቱ ሁሉ ወዮላቸው, ፪ ኔፊ ፱፥፴፰. ኃጢያትን ከመጥላት በቀር ሊመለከቱትም አልቻሉም, አልማ ፲፫፥፲፪. ከኃጢያት ወደ ደስታ እመለሳለሁ ብለህ አትገምት, አልማ ፵፩፥፱–፲. ጌታ ኃጢያትን በትንሹም ቢሆን ሊቀበለው አይቻለውም, አልማ ፵፭፥፲፮ (ት. እና ቃ. ፩፥፴፩). ህፃናት ኃጢያትንም ለመፈፀም አይችሉም, ሞሮኒ ፰፥፰. ንስሀ ለመግባት፣ ሰዎች ይናዘዛሉ እናም ይተዋቸዋልም, ት. እና ቃ. ፶፰፥፵፪–፵፫. ይቅርታ የማይሰጠውም በእርሱ ታላቁ ኃጢያት ይቀራል, ት. እና ቃ. ፷፬፥፱. በታላቅ ብርሀን ላይ ኃጢያት የሚሰራው የባሰውን ፍርድ ይቀበላል, ት. እና ቃ. ፹፪፥፫. ኃጢያት ለሚሰራው ነፍስ የድሮው ኃጢያት ይመለስበታል, ት. እና ቃ. ፹፪፥፯. ኃጢያታችንን ለመሸፈን ስንሞክር፣ ሰማያት እራሳቸውን ይለያሉ, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፴፯.