በወሲብ የስነ ምግባር ጉድለት ደግሞም ማመንዘር; ስሜታዊ፣ ስሜታዊነት; ዝሙት መፈጸም ተመልከቱ ይህም በማመንዘር፣ ዝሙት በመፈጸም፣ በግብረ ሰዶማዊነት፣ በሴቶች ግብረ ሰዶማዊነት፣ በስጋ ዘመዶች መሀከል የግብረ ስጋ ግንኙነትን በመፈጸም፣ ወይም በሌላ ቅዱስ ባልሆኑ፣ በፍጥረት ተፈቃጅ ባልሆኑ፣ ወይም ንጹህ ባልሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት በፈቃደኝነት መሳተፍ ነው። አባታቻንንም የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ, ዘፍጥ. ፲፱፥፴–፴፮. ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት, ዘፍጥ. ፴፭፥፳፪ (ዘፍጥ. ፵፱፥፬; ፩ ዜና ፭፥፩). ግብረ ሰዶማዊነት እና ሌላ የፍትወተ ስጋ ጠማማነት የተኮነኑ ናቸው, ዘሌዋ. ፲፰፥፳፪–፳፫. ወንድ ሴትን በግድ አሸንፎም ቢደርስባት፥ ያ የደረሰባት ሰው በኃጢያት ወንጀለኛ ነው, ዘዳግ. ፳፪፥፳፭–፳፯. ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል, ማቴ. ፭፥፳፰ (፫ ኔፊ ፲፪፥፳፰). ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ የሆነ ነው, ቄላ. ፫፥፭. በኋለኛው ቀናት ሰዎች ትክክል ያልሆነ ፍቅር ያላቸው ይሆናሉ, ፪ ጢሞ. ፫፥፩–፫. ወሲባዊ ኃጢያት እርኩሰት ነው, አልማ ፴፱፥፫–፭.