ደስታ ደግሞም ታዛዥነት፣ ታዛዥ፣ መታዘዝ ተመልከቱ በጻድቅ ህይወት የሚመጣ ታላቅ ደስታ። የስጋዊ ህይወት አላማ ሁሉም ሰዎች ደስታ እንዲኖራቸው ነው (፪ ኔፊ ፪፥፳፪–፳፭)። ሙሉ ደስታ የሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው (ዮሐ. ፲፭፥፲፩፤ ት. እና ቃ. ፺፫፥፴፫–፴፬፤ ፻፩፥፴፮)። የዋሃን ደስታቸውን በእግዚአብሔር ያበዛሉ, ኢሳ. ፳፱፥፲፱ (፪ ኔፊ ፳፯፥፴). ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ, ሉቃ. ፪፥፲. ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም, ዮሐ. ፲፮፥፳፪. የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም ነው, ገላ. ፭፥፳፪. ይህም ፍሬ ነፍሴን በደስታ ሞላው, ፩ ኔፊ ፰፥፲፪. ሰዎች የሚኖሩትም ደስታም እንዲኖራቸው ዘንድ ነው, ፪ ኔፊ ፪፥፳፭. የፃድቃን ደስታ ለዘለዓለም ሙሉ ይሆናል, ፪ ኔፊ ፱፥፲፰. ለዘለአለም በማያልቀው ደስታ ከእግዚአብሔር ጋር ይኖራሉ, ሞዛያ ፪፥፵፩. ያለኝን ሁሉ እተዋለሁ፣ … ይህን ታላቁን ደስታም እቀበል ዘንድ…, አልማ ፳፪፥፲፭. ምናልባት ጥቂት ነፍሳትን ወደ ንስሃው በማምጣት በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ እሆን ዘንድ በዚህ እመካለሁ፤ እናም ይህም የእኔ ደስታ ነው, አልማ ፳፱፥፱. እንዴት ያለ ደስታ ተሰማኝ፤ እናም ምን ዓይነት አስደናቂ ብርሃንን አይቻለሁ, አልማ ፴፮፥፳. ነፍስህን በደስታ የሚሞላ፣ ከመንፈሴ ለአንተ እሰጥሃለው, ት. እና ቃ. ፲፩፥፲፫. አንድም ነፍስም ቢሆን እንኳን ወደ እኔ ብታመጡ፣ በአባቴ መንግስት ከእርሱ ጋር ደስታችሁ እንዴት ታላቅ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፲፰፥፲፭–፲፮. በዚህ አለም ደስታችሁ ሙሉ አይደለምና፣ ነገር ግን በእኔ ደስታችሁ ሙላት አለው, ት. እና ቃ. ፻፩፥፴፮. በዚህ ህይወትም ደስታ ይኖረኛል, ሙሴ ፭፥፲–፲፩.