ኖኅ፣ የመፅሐፍ ቅዱስ የአባቶች አለቃ
በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የላሜሕ ልጅ እና ከአዳም ጀምሮ አስረኛው የአባቶች አለቃ (ዘፍጥ. ፭፥፳፱–፴፪)። ስለክርስቶስ መሰከረ እናም ለኃጢያተኛ ትውልዶች ንስሀ መግባትን ሰበከ። ህዝቡ መልእክቱን ሲያስወግዱ፣ እግዚአብሔር ምድር ክፉዎችን ለማጥፋት በምትጥለቀለቅበት ጊዜ ቤተሰቡን እና የምድር ሁሉ እንስሳት እንዲኖሩበት መርከብ እንዲገነባ አዘዘው (ዘፍጥ. ፮፥፲፫–፳፪፤ ሙሴ ፰፥፲፮–፴)። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ኖኅ መላእኩ ገብርኤል እንደሆነ እና የደህንነትን ቁልፎች በመያዝ ከአዳም ተከታይ እንደሆነ አስተማረ።