ኔፋውያን ደግሞም ላማናውያን; መፅሐፈ ሞርሞን; ኔፊ፣ የሌሂ ልጅ ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ያሉ፣ ብዙዎቹ የሌሂ ልጅ የነቢዩ ኔፊ ትውልዶች የሆኑ ህዝብ። ከላማናውያን ጋር ተለያዩ እናም በአጠቃላይ ከላማናውያን በላይ ጻድቅ ነበሩ። ነገር ግን፣ በኋላም በኃጢያተኛነት ምክንያት በላማናውያን ተደመሰሱ። ኔፋውያን ከላማናውያን ተለያዩ, ፪ ኔፊ ፭፥፭–፲፯. ላማናውያን ያልነበሩት ህዝቦች ኔፋውያን ነበሩ, ያዕቆ. ፩፥፲፫. ኔፋውያን ከሁሉም በሚበልጥ ምክንያት ተነሳስተው ነበር, አልማ ፵፫፥፮–፱፣ ፵፭. ኔፋውያን በሞሮኒ ዘመን አይነት ያለ ደስታ አልነበራቸውም, አልማ ፶፥፳፫. ኔፋውያን በጻድቅ ጸሎቶች ምክንያት ድነው ነበር, አልማ ፷፪፥፵. ኔፋውያን ባለማመን መነመኑ, ሔለ. ፮፥፴፬–፴፭. ኢየሱስ በኔፋውያን መካከል አስተማረም አገለገለም, ፫ ኔፊ ፲፩፥፩–፳፰፥፲፪. ወደ ጌታ የተለወጡ ሁሉ፣ ሁሉም ነገሮች በጋራ ነበሩአቸው, ፬ ኔፊ ፩፥፪–፫. በህዝቡ ልብ ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር ፍቅር የተነሳ በምድሪቱ ፀብ አልነበረም፣ ከሁሉም በላይ ደስተኛ የሆኑ ህዝብ ነበሩ, ፬ ኔፊ ፩፥፲፭–፲፮. ኔፋውያን መኩራትና ከንቱ መሆን ጀመሩ, ፬ ኔፊ ፩፥፵፫. በምድሪቱ ገፅ ሁሉ ደም መፋሰስ እናም እልቂት ሆነ, ሞር. ፪፥፰. ነፋውያን በክፋት አደጉ እናም ሞርሞን እነርሱን ለመምራት እምቢ አለ, ሞር. ፫፥፱–፲፩. ከሀያ አራት በስተቀር፣ ኔፋውያን ሁሉ ተገደሉ, ሞር. ፮፥፯–፲፭. ክርስቶስን የማይክዱትን እያንዳንዱ ኔፋውያን ተገደሉ, ሞሮኒ ፩፥፪. ኔፋውያን በኃጢያታቸው እና በእርኩስነታቸው የተነሳ ጠፉ, ት. እና ቃ. ፫፥፲፰. ኩራትን ተጠንቀቁ፣ አለበለዚያም እንደ ኔፋውያን ትሆናላችሁ, ት. እና ቃ. ፴፰፥፴፱.