ኦሪት ዘዳግም
የብሉይ ኪዳን አምስተኛ መፅሐፍ።
ኦሪት ዘዳግም የሙሴን የመጨረሻ ሶስት ንግግሮችን ይይዛል፣ እነዚህንም የሰጣቸው በሞአብ ሜዳ ላይ ከመቀየሩ በፊት ነበር። የመጀመሪያው ንግግር (ምዕራፍ ፩–፬) ማስተዋወቂያ ነው። ሁለተኛው ንግግር (ምዕራፍ ፭–፳፮) ሁለት ክፍሎች አሏቸው፥ ምዕራፍ ፭–፲፩—አስሩ ትእዛዛትና በእነርሱ እንዴት በየቀኑ እንደሚጠቀሙባቸው፤ እናም ምዕራፍ ፲፪–፳፮። ሶስተኛው ንግግሮች (ምዕራፍ ፳፯–፴) በእስራኤልና በእግዚአብሔር መካከል የተገባው የክብር ቃል ኪዳን የታደሰበትን እና ታዛዥነትን የሚከተሉ በረከቶችንና ታዛዥ አለመሆንን የሚከተሉ እርግማንን ይይዛል። ምዕራፍ ፴፩–፴፬ ህጉ ለሌዋውያን የተሰጠበትን፣ የሙሴን መዝሙርና የመጨረሻ በረከት፣ እና የሙሴ መሄድን ይገልጻል።