ድምፅ ደግሞም ራዕይ ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ እንደሚጠቀሙበት፣ አንዳንዴ በጌታ ወይም በመልእክተኞቹ በድምፅ የሚሰጥ በደንብ የሚሰማ መልእክት። የመንፈስ ድምፅ ደግሞም በደንብ አይሰማም እና በቀጥታ ወደ ልብ ወይም አዕምሮ የሚመጣ ሊሆንም ይችላል። አዳም እና ሔዋን የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ሰሙ, ዘፍጥ. ፫፥፰ (ሙሴ ፬፥፲፬). ጌታ ለኤልያስ በትንሽ የዝምታ ድምፅ አነጋገረው, ፩ ነገሥ. ፲፱፥፲፩–፲፫. ጻድቅ የመልካሙ እራኛ ድምፅን ይከተላሉ, ዮሐ. ፲፥፩–፲፮. ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል, ዮሐ. ፲፰፥፴፯. ለመንፈስም ድምፅ ታዘዝኩ, ፩ ኔፊ ፬፥፮–፲፰. ድምፅ ወደእኔ መጣ፣ እንዲህም አለኝ ኢኖስ ኃጢያትህ ይቅር ተብሎልሃል, ኢኖስ ፩፥፭. ለስላሳና ፍፁም የሆነ ድምፅ ነበር፣ እናም ነፍስንም እንኳን የሚወጋ ነበር, ሔለ. ፭፥፳፱–፴፫ (፫ ኔፊ ፲፩፥፫–፯). በእኔ ድምጽ ሆነ በአገልጋዮቼ ድምጽ፣ ያም አንድ ነው, ት. እና ቃ. ፩፥፴፰. በመንፈስ ቅዱስ ሲነሳሱ የሚናገሩት ማንኛውም ነገር ቅዱሣት መጻህፍት ይሆናሉ, ት. እና ቃ. ፷፰፥፪–፬. ድምጼን የሚያከብር ነፍስ ሁሉ ፊቴን ያያል እና እኔ እንደሆንኩም ያውቃል, ት. እና ቃ. ፺፫፥፩.