ሙሌቅ ደግሞም ሴዴቅያስ ተመልከቱ የብሉይ ኪዳን ንጉስ ሴዴቅያስ ልጅ (በ፭፻፹፱ ም.ዓ. አካባቢ)። መፅሐፍ ቅዱስ የሴዴቅያስ ልጆች በሙሉ እንደተገደሉ ይመዘግባል (፪ ነገሥ. ፳፭፥፯)፣ ነገር ግን መፅሐፈ ሞርሞን ሙሌቅ እንደዳነ ይገልጻል (ሔለ. ፰፥፳፩)። ዛራሔምላ የሙሌቅ ትውልድ ነበር, ሞዛያ ፳፭፥፪. የሙሌቅ ህዝቦች ከኔፋውያን ጋር አንድ ሆኑ, ሞዛያ ፳፭፥፲፫. ጌታ ሙሌቅን በምድሪቱ በሰሜን በኩል አምጥቷቸዋልና, ሔለ. ፮፥፲. ከሙሌቅ በስተቅር የሴዴቅያስ ወንድ ልጆች ሁሉ ተገድለው ነበር, ሔለ. ፰፥፳፩.