መድኃኒት ደግሞም አዳኝ; ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ ሁሉንም ከሞት እስርና ንስሀ የሚገቡትን ከኃጢያት ቅጣቶች ስለሚያድን ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒት (ቤዛ) ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ዘር ታላቅ ቤዛ ነው፣ ምክንያቱም በኃጢያት ክፍያው በኩል እርሱ የሰው ዘር ኃጢያት ዋጋን ከፈለ እናም የሁሉንም ሰዎች ትንሳኤ ሊሆን እንዲቻል አደረገ። እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው, ፪ ሳሙ. ፳፪፥፪ (መዝ. ፲፰፥፪; ፻፵፬፥፪). የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ ያውቃል, ኢዮብ ፲፱፥፳፭. አንተ ረዳቴና መድኃኒቴ ነህ, መዝ. ፵፥፲፯ (መዝ. ፸፥፭). እረዳሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው, ኢሳ. ፵፩፥፲፬ (ኢሳ. ፵፫፥፲፬; ፵፰፥፲፯; ፶፬፥፭; ፶፱፥፳). እኔ እግዚአብሔር መድኃኒትሽና ታዳጊሽ ነኝ, ኢሳ. ፵፱፥፳፮ (ኢሳ. ፷፥፲፮). እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ, ማቴ. ፩፥፳፩. የሰው ልጅ ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ መጣ, ማቴ. ፳፥፳፰ (፩ ጢሞ. ፪፥፭–፮). የእስራኤል ጌታ አምላክ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአል, ሉቃ. ፩፥፷፰. ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ታረቅን, ሮሜ ፭፥፲. መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል, ሮሜ ፲፩፥፳፮. ኢየሱስ ክርስቶስ ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል, ቲቶ ፪፥፲፫–፲፬. ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢአታችንም በደሙ አጠበን, ራዕ. ፩፥፭. ቤዛነት የሚመጣው በቅዱስ መሲሕ በኩል ነው, ፪ ኔፊ ፪፥፮–፯፣ ፳፮. ወልድ በእራሱ ላይ የሰውን ኃጢያት እና መተላለፍ ወሰደ፣ አዳናቸው፣ እናም የፍትህን ፍላጎት አሟላ, ሞዛያ ፲፭፥፮–፱፣ ፲፰–፳፯. ክርስቶስ ወደ ንስሀ መግባት የሚጠመቁትን ሁሉ ለማዳን መጣ, አልማ ፱፥፳፮–፳፯. ህዝቡን ለማዳንና ወደ ዓለም ይመጣል, አልማ ፲፩፥፵–፵፩. ቤዛነት በንስሃ አማካይነት ይመጣል, አልማ ፵፪፥፲፫–፳፮. ኢየሱስ አለምን ለማዳን መጣ, ሔለ. ፭፥፱–፲፪. ክርስቶስ የሰው ዘርን ከስጋዊ እና ከመንፈሳዊ ሞት ለማዳን መጣ, ሔለ. ፲፬፥፲፪–፲፯. በክርስቶስ ቤዛነት ይመጣል, ፫ ኔፊ ፱፥፲፯. ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ህዝቤን ለማዳን የተዘጋጀሁ እኔ ነኝ, ኤተር ፫፥፲፬. ጌታ አዳኛችሁ የስጋ ሞትን ሞተ, ት. እና ቃ. ፲፰፥፲፩. ክርስቶስ ንስሀ ከገቡ ለሁሉም ተሰቃይቷል, ት. እና ቃ. ፲፱፥፩፣ ፲፮–፳. ህፃናት ከአለም መጀመሪያ ጀምሮ በአንድያ ልጄ ድነዋል, ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፮. አንድያ ልጄን ለአለም ቤዛነት ወደ አለም ልኬአለሁ, ት. እና ቃ. ፵፱፥፭. ክርስቶስ የአለም ብርሀን እና አዳኝ ነው, ት. እና ቃ. ፺፫፥፰–፱. ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ ስለሙታን ቤዛነት ራዕይ አዩ, ት. እና ቃ. ፻፴፰. ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ልጅ እንደ ቤዛቸውና እንደ መድሀኒታቸው እንደሆነ ተቀበሉ, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፳፫. የሰው ዘሮች ሁሉ በክርስቶስ ኃጢያት ክፍያ በኩል መዳን እንደሚችሉ እናምናለን, እ.አ. ፩፥፫.