የጥናት እርዳታዎች
ህሊና


ህሊና

በሁሉም ሰዎች ውስጥ ከሚገኘው የክርስቶስ ብርሀን የሚመጣው፣ በውስጥ የሚሰማ የትክክለኛነት ወይም ትክክል ያለመሆን ስሜት(ሞሮኒ ፯፥፲፮)። ትክክልን ወይም ትክክል ያልሆነን ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ችሎታ ለእያንዳንዱ ሰው በተሰጠው በክርስቶስ ብርሀን ምክንያት አለን(ት. እና ቃ. ፹፬፥፵፮)። ይህ ችሎታ ህሊና ይባላል። ይህም ሲኖረን ሀላፊነት ያላቸው ያደርገናል። እንደ ሌሎች አይነት ችሎታዎች፣ ህሊናዎቻችን በኃጢያት ወይም በትክክል ባለመጠቀም ምክንያት ሊደነድኑ ይችላሉ።